አደጋውና ማስጠንቀቂያው – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

አደጋውና ማስጠንቀቂያው

ጅብ ልጁን እየላጨ ነበር አሉ፡፡ ሰማ፡፡ ግን የድምጹን አቅጣጫ ለማወቅ አልቻለም፡፡ አህያም ብትጠብቅ ብትጠብቅ የመጣ ጅብ የለም፡፡ ውሻውንም ‹ባክህ ዝም ብለህ ሽብር ስትነዛ ነው እንጂ፤ ጅቡ ወይ ሞቷል፣ ወይ የለም፣ ወይ ተኝቷል› አለቺው፡፡ ‹አይደለም› አለ ውሻ፡፡ ‹አይደለም፤ ጅቡ ሰምቷል፡፡ አንቺ ግን መስማቱን ማወቅ አልቻልሽም፡፡ አሁንም በዚህ ቢበቃሽ ጥሩ ነው› አላት፡

፡ ‹ጥጋበኛ ሰው ሦስት ነገሩ ይወፍራል – ጆሮው፣ ዓይኑና ልቡ› ይላል መዝገበ ጠቢባን፡፡ ጆሮው ከራሱ በቀር እንዳይሰማ ሆኖ፣ ዓይኑም ከራሱ በቀር እንዳያይ ሆኖ፣ ልቡም ቢያይም ቢሰማም እንዳያስተውል ሆኖ ጥጋብ ይደፍነዋል፡፡ እነዚህ በጥጋብ ሲደፈኑ ደግሞ ‹ኩራትና ትዕቢት› ዓይንና ጆሮ ይሆናሉ፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሆድ ዕቃ የመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ አየር መንገዱ ያስመረቀውን ዘመናዊ ኮሌጅ በማስመልከት የአየር መንገዱን ነገረ ሥራ እንድንጎበኝ ተጋብዘን ነበር፡፡ የጥገና ቦታውን፣ የካርጎ ማዕከሉን፣ አዳዲስ እያስፋፋቸው የሚገኙ የካርጎና የጥገና ቦታዎችን አይተናል፡፡ የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ ለሚመለከት ሰው ከጥንት ጀምሮ እየካበተ፣ እየተሳለጠና እየሠለጠነ የመጣውን ይህን ታላቅ ሀገራዊ ድርጅት፤ እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ ለመረዳት ያስችለዋል፡፡ እንዲያውም እኛ ሀገር እንደ አበሻ መድኃኒት ሁሉም ነገር ምሥጢር ስለሚሆን ነው እንጂ ልጆቻችን በጉብኝት ፕሮግራሞች የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ የማየት ዕድሉ ቢኖራቸው ኖሮ አየር መንገዱንም እንዲወዱ፣ የፈጠራ ፍላጎታቸውም እንዲጨምር ያደርገው ነበር፡፡
በጥገና ክፍሉ የጀመረው ጉብኝት፣ በካርጎ ክፍሉ በኩል አድርጎ በአዳዲስ የማስፋፋያ ፕሮጀክቶቹ በኩል ሲጠናቀቅ ዓይኔ አንድ ነገር ላይ ዐረፈ፡፡ ነገሩ የተጻፈው በአየር መንገዱ የጥገና ክፍል ግድግዳ ላይ ነው፡፡ ለእኔ ከጥገና መሣሪያዎች፣ ከጠጋኞቹ ብቃትና ከጥገና ብቃቱ … የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ከሰጡት ዕውቅና ባልተናነሰ የሳበኝ በየግድግዳው የተለጠፉት የደኅንነት ማሳሰቢያዎቹ ናቸው፡፡
‹አደጋውን ሪፖርት ከማድረግህ በፊት ምልክቱን ቀድመህ ተናገር – “report a hazard before you have to report an accidents” ይላል፡፡ በዚያ ፈረስ በሚያስጋልብ የጥገና አዳራሽ ውስጥ የተለያዩ አደጋዎችን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ምልክቶች በመብራት አማካኝነት ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላልፉ ተደርገዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የማስጠንቀቂያ እሪታ (ሳይረን) ያሰማሉ፡፡ እነዚህን የአደጋ ምልክቶች ቀድሞ ማወቅና ለእነዚህ ምልክቶችም ተገቢውን ምላሽ መስጠት በኋላ ለአደጋው ምላሽ ከመስጠት ያድናል፡፡ ጎበዝ ባለሞያም የደረሰውን አደጋ ሳይሆን አደጋ እንደሚመጣ የሚገልጠውን ማስጠንቀቂያ ቀድሞ ይናገራል፡፡ ይኼ ነው የጥገና ክፍሉ ግድግዳ ላይ በትልቁ የተሰቀለው፡፡
በሀገራችን ‹በዕንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ›፣ ‹ጢሱን አይተህ እሳቱን፣ ቀንዱን አይተህ ከብቱን ተጠንቀቅ›፣ ‹በቅርቡ ያልመለሰ እረኛ፣ በሩቁ ሲባዝን ይኖራል›፣ ‹ውሻውን አይተህ ካልተደበቅክ አዳኙ አይቶ ይገድልሃል›፣ ‹አውው ሲል ዝም ካልክ ‹አሙሙ ብሎ ይገምጥሃል› የሚሉ የዚህ ምክር ጓደኞች ሞልተዋል፡፡ ውሻ ለአህያ ‹የመጀመሪያው መጥሪያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ነው› ብሎ የመከረው ምክር የዚህ ማስጠንቀቂያ አንድምታ ትርጓሜ ውስጥ ‹ታሪክ አንደ አህያ ነው› ተብሎ ተካትቷል፡፡ ታሪኩስ እንደምን ነው ቢሉ፣ አህያና ውሻ መንገድ ዘመቱ አሉ፡፡ ከዘመቻ ሲመለሱ መሸባቸውና ውሻ የሚበላ አጥቶ ተኮራምቶ ሲተኛ፣ አህያ ግን መስኩ ላይ ያገኘቺውን ሣር ግጣ ሆዷ ተነፋ፡፡ ‹ከተራበ ይልቅ ለጠገበ አዝናለሁ› እንዲል ሕዝቡ፡፡ ይህስ ስለምን ነው ቢሉ? የጠገበ ሰው ረሐብ ያለ አይመስለውም፡፡ የተራበ ተጠቅልሎ ሲተኛ፣ የጠገበ ግን የተጠቀለለውን እየፈታ እንደ አጤ ልብነ ድንግል ጦር አውርድ ይላል፡፡
እናም አህያ ከጥጋቧ ብዛት ‹ልጩህ› አለች፡፡ ውሻ ‹ለምን› ቢላት ‹ፎረሸኝ› አለች፡፡ ‹ፎረሸኝ ማለትስ ምን ማለት ነው ቢሉ፤ ጥጋቤ ቅጥ አሳጣኝ፤ ከትዕቢት አላግቶ ምን ይመጣል አስባለኝ፣ የጠገበ ሲጮኽ የተራበ እንደሚበላው እንዳላውቅ አደረገኝ› ማለት ነው፡፡ እናም አህያዋ ልትጮህ ስትል፤ ‹ተይ ይቅርብሽ ጅብ ይሰማሻል› አላት ውሻ፡፡ ከጠገቡ አያስቡ፣ ከወፈሩ ሰው አይፈሩ፣ ከተበቱ አይታይ ሥጋቱ፣ እንዲል መጽሐፈ ባልቴት፡፡ ‹ተው ባክህ፤ የት አግኝቶ ይሰማኛል› አለቺው፡፡ ‹እንዴ ይኼኮ የጅብ አገር ነው፡፡ የተራበ ጅብ የጠገበ አህያ መስማት እንዴት ያቅተዋል› አላት፡፡ ‹ባክህ ቢሰማስ ምን ያመጣል› አለቺና አናፋች፡፡ ‹ምን ያመጣል ብሎ ገብቶ፣ ማን ያወጣል ብሎ ጮኸ› እንዲል ነገረ ሕዝብ፡፡
ጅብ ልጁን እየላጨ ነበር አሉ፡፡ ሰማ፡፡ ግን የድምጹን አቅጣጫ ለማወቅ አልቻለም፡፡ አህያም ብትጠብቅ ብትጠብቅ የመጣ ጅብ የለም፡፡ ውሻውንም ‹ባክህ ዝም ብለህ ሽብር ስትነዛ ነው እንጂ፤ ጅቡ ወይ ሞቷል፣ ወይ የለም፣ ወይ ተኝቷል› አለቺው፡፡ ‹አይደለም› አለ ውሻ፡፡ ‹አይደለም፤ ጅቡ ሰምቷል፡፡ አንቺ ግን መስማቱን ማወቅ አልቻልሽም፡፡ አሁንም በዚህ ቢበቃሽ  ጥሩ ነው› አላት፡፡ ‹ጥጋበኛ ሰው ሦስት ነገሩ ይወፍራል – ጆሮው፣ ዓይኑና ልቡ› ይላል መዝገበ ጠቢባን፡፡ ጆሮው ከራሱ በቀር እንዳይሰማ ሆኖ፣ ዓይኑም ከራሱ በቀር እንዳያይ ሆኖ፣ ልቡም ቢያይም ቢሰማም እንዳያስተውል ሆኖ ጥጋብ ይደፍነዋል፡፡ እነዚህ በጥጋብ ሲደፈኑ ደግሞ ‹ኩራትና ትዕቢት› ዓይንና ጆሮ ይሆናሉ፡፡ ከዚያም
ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
ከመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ፡፡ የሚለው ትንቢታዊ ግጥም እስኪደርስባቸው ድረስ እንደ ኤድስ ማስታወቂያ ‹አላይም፣ አልሰማም እያሉ መኖር ነው፡፡
አህያ አሁንም መስኩን ብቻዋን ይዛ ትገሸልጠው ጀመር፡፡ መስክ ብቻን መያዝ ጥጋብ ያመጣልና ልቧ ተነፋ፡፡ ልቡ የተነፋ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መጮኽ ይወዳልና ‹ልጩህ› አለች፡፡ ውሻ ‹ተይ ይቅርብሽ ቅድም የታገሰሺን ጅብ ትእግሥቱን አታስጨርሺው› አላት፡፡ ‹ባክህ ምንም አያመጣም› አለቺና አናፋች፡፡ ‹አናፋች› ማለትስ ምንድን ነው ቢሉ፤ ‹እንዳመጣላት ጮኸች፣ ደነፋች፣ ያዙኝ ልቀቁኝ አለቺ› ማለት ነው፡፡ ልጁን ሲላጭ የነበረው ጅብ፤ አሁን አቅጣጫውን ለየና ወደ አህያዋ ዘንድ መምጣት ጀመረ፡፡ ነገር ግን አቅጣጫውን እንጂ ቦታውን አላገኘውም፡፡ ‹አቅጣጫውን እንጂ ቦታውን አላገኘውም› ሲል ምንድን ነው? ቢሉ፤ ‹ሆዱ ግም ግም ብሏል፣ ልቡ ቱግ ቱግ ብሏል፣ መፍትሔው ጠፍቶበት እንጂ ችግሩን ለይቷል› ማለት ነው፡፡
አህያም እንደለመደቺው ብቻዋን በመስኩ ላይ ተለቀቀቺበት፡፡ ውሻ ግን ምንም አብሮ ቢዘምት እንደ አህያ የሚበላ አላገኘም፡፡ የተረፈው የዘመቻው እንጉርጉሮ ነው፡፡ ያንን እያንጎራጎረ ተኛ፡፡ ምንም ባዶ ሆድ ባያስተኛ፡፡ አህያ ግን ድጋሚ ፎረሻት፡፡ ‹ልጮህ ነው› አለቺው፡፡ ‹ይቅርብሽ፣ አሁን ሲሆን ልብ፣ ካልሆነም አደብ ግዢ፤ የመጀመሪያው መጥሪያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ነው› አላት፡፡ ሲጠግቡ እንጀራ ወደ ሆድ እንጂ ነገር ወደ ልቡና አይገባምና አልሰማቺውም፡፡ ‹ሰሚ ስታገኝ ተናገር፣ ዳኛ ስታገኝ መስክር› ነውና ዝም አላት፡፡ አህያም ጥጋብ አህያ መሆንዋን አስረስቷት ነበርና ለሦስተኛ ጊዜ አናፋች፡፡ ያን ጊዜ ቦታው ጠፍቶት ሲያደፍጥ የነበረው የተራበ ጅብ፤ ከኋላዋ ቦትርፎ፣ አህያ መሆንዋን እንድታውቀው አደረጋት፡፡ ችግሩ አህያነቷን ያወቀቺው ከተበላች በኋላ ሆነ፡፡
ያን የአየር መንገዱን የጥንቃቄ ማስታወቂያ እዚያ መስክ ላይ በአህያኛ የለጠፈላት ቢኖር፣ እርሷም የመስሚያ ጆሮና የመስማሚያ ልብ ቢኖራት ኖሮ በተረፈች ነበር፡፡ ከእርሷ በፊት እንደ እርሷ የመሰለ ነገር የገጠማት ቀበሮ ከአደጋው በፊት በማስጠንቀቂያው ተርፋለች ተብሎ በእንስሳት ታሪከ ነገሥት ውስጥ እንዲህ ተመዝግቧል፡፡ አንበሳ ታምሜያለሁ ብሎ በተኩላ በኩል እያስነገረ እንስሳቱ ሁሉ ሊጠይቁት ሲሄዱ በክርኑ ደቁሶ ይበላ ጀመር፡፡ በኋላ መተኛት ሰልችቶት ከአልጋው ተነሣና ምስጢሩን እንዳታወጣ ተኩላን አንገቷን ይቀነጥሳታል፡፡ አንበሳ ጫካ ውስጥ ሲመላለስ ቀበሮን ያገኛታል፡፡ ‹እፈልግሻለሁ› እያለ ይቀጥራታል፡፡ ትጠፋበታለች፡፡ ይቀጥራታል፤ ትጠፋበታለች፡፡ አንድ ቀን አሳቻ ቦታ አገኛትና ‹ለመሆኑ ለምን እንደምፈልግሽ በምን ዐውቀሽ ነው የምትጠፊው› ይላታል፡፡ ‹እኔማ በምን ዐውቃለሁ፤ ከተኩላ ጭንቅላት ተምሬ ነው እንጂ› አለቺው አሉ፡፡ ካለፉት ስሕተት የማይማር፣ ያን ስሕተት ለመድገም የተረገመ ይሆናል፡፡ የታሪክ አንዱ ጥቅሙ ከአደጋው በፊት በምልክቱ እንድንነቃ ለማድረግ ነውና፡፡ ያለፉንን ሰዎች ስንወቅስ ከመኖር የተወቀሱበትን መረዳቱ ይበልጥ ይጠቅም ነበር፡፡
ቅሬታዎችን ማዳመጥ፣ ችግሮችን በጊዜ መፍታት፣ ለጥቃቅኑ ጉዳዮች ቀድሞ ትኩረት መስጠት፣ ጢሱን ሲያዩ እሳቱ እንደሚከተል መገመት፣ ከአደጋው በፊት በማስጠንቀቂያው ለመንቃት ያስችላል፡፡ የተናቀ ባቄላ ሆድ ይጎጥራል፡፡ ቻይኖች ጠብታ ውኃ እድሜዋ ከረዘመ ዐለት ትሰብራለች ይላሉ፡፡ ዝሆን አደን ሲሄድ ትንኞች የተሰበሰቡበት ሥፍራ ደረሰ፡፡ ሚስቱ ‹እኔ ይሄ ነገር አላማረኝም እንመለስ› አለቺው፡፡ ዝሆኑም ‹ለትንኝ ብለን› ይላትና ዝም ብሎ ይሄዳል፡፡ አንዷ ትንኝ ጆሮው ውስጥ ትገባና ትጮህበት ጀመር፡፡ ያ እንደ ሰፌድ የሰፋ ጆሮው መልሶ ድምጽዋን ሲያስተጋባለት የትንኟ ጩኸት እንደ ፈንጅ ድምጽ እየተሰማው ያስሮጠው ጀመር፡፡ ሚስቱ ተው ስትለው አልሰማ ብሎ የነበረው ዝሆን፣ ትንኝ እያስጮኸች መንደሩ ደረሰ፡፡ ለደግነት እንጂ ለክፋት የሚያንስ የለም፡፡
የመሪዎች፣ የመንግሥታትና የድርጅቶች ታላቅነት የሚለካው ከአደጋው በፊት ለማስጠንቀቂያው በሚኖራቸው ዝግጅት ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን የመጀመሪያው መስሚያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ይሆናል፡፡

23 Comments on “አደጋውና ማስጠንቀቂያው – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት”

  1. This is why i say no body realy knows eprdf this is what they especialysed on conflict resolution no wories they will handl it

  2. you right dakon Daniel 25 years too much the EPRDF has to listen the people question we need Ethiopians equality and free the political prisoners until when EPRDF depend with a gun when the flood comes it’s hard to go any where this is the time to listen the people.

  3. aye Daniel kibret,,

    min tibela yehon ?
    YET TIGEBA YEHON ?
    weyane yehede ILET !!

    ANTE MESERI
    YE AFLIHO METETEGNA

    ANTE YE WEYANE CADRE !!! UFFFFFFFFFFFFFFFFFFFFF

  4. Sewun min nekaw yetegebe sew jorom aynim yelewim lik end ahiyayitu naw mechereshaw simot bicha naw yemilekew Danil egizer yistilign antes negrehachewal EPRDF Ke dergim ke Janhoyim memar alchalem beteley yalenibet 21 kifle zemen mehonunim restewal atifredubachew sewoch arjitewal nefse yimar belilign!

  5. የመሪዎች፣ የመንግሥታትና የድርጅቶች ታላቅነት የሚለካው ከአደጋው በፊት ለማስጠንቀቂያው በሚኖራቸው ዝግጅት ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን የመጀመሪያው መስሚያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ይሆናል፡፡
    I wonder why is not recruited by EPDRF!! Comparing people’s uprising to hyena’s roar is not acceptable.
    Down with Woyane

  6. ቀላማጅ ዳቆን ሆድእቃ ህይዎት ላላቸውፍጡሮች
    መገለጫ እንጂ? ሰው ለሰራው እቃ አይመጥንም

  7. How can they learn from the past? They are blind to history. They don’t even want to learn from their own Mega mistakes. They might be learning after their death. The next generation use them as a teaching aid.

  8. wesagn kin na mistir atweikim? dekama bihonim sew new.tunishuan neger eyanesan metechet tilikun gumineger enatalen.

  9. ለአንድ ህዝብ የለህን ንቀትና ጥላቻ ለመግለፅ ይሄን የህል መድከምህ በጠም የሰዝነል፡፡ አንተ ተጠቀሚ ስለሆንክ ሌለዉ መሞት አለበት?

  10. ካድሪው ዲያቆን የሰሞኑን ህዝባዊ አመፅ ለመቀልበስ ከአህያ ጋር እያነፃፀረ መፃፍ ጀመረ፡፡ ብቻ ይህ ቀን ያልፍና ያስተዛዝበናል፡፡ያለፉትን ሰዎች የሚሳደበው ዲ/ን ዛሬ ደግሞ መውቀስ አያስፈልግም ይላል፡፡አንተ እንደ እስስት በተቀያየር መጠን እኛም የምንቀያየር ከመሰለህ ተሳስተሀል፡፡አንዴ የሰረሀት ስህተት ለታሪክ ትቀመጣለች፡፡ባለፈው አፄ ቴዎድሮስን መሳደቡን ረሳውና ዛሬ ሊመክረን የኛ ዲ/ን ….

  11. ሆድ አደር ከርሳም የቤ/ን ቀንደኛ ጠላት የኦሮሞን አመፅ ለማፈን መሞከርህ ጅልነትህ ነው፡፡አጋዚ ያላቆመውን አመፅ አንተ በተረት ልታኮላሸው አትችልም፡፡

  12. ዲ/ን ተብሎ ፖለቲከኛ። የልጆች ፕሮግራም ተረት ተረት ታስተምር ነብር መሰለኝ። ይሀ የጅቦች ተረት የሚስራው በናንተ እድሜ ለነብሩ ልጆች ነው። የኣሁኑ ልጅ ኣስተሳሰብ መረዳት ኣልቻልክም።ምናልባሽ የኣሁኑ ውጣት ከኣንተ ሶስት እጥፍ ተራቅቆዋል። EBC የልጆች ፕሮግራም ብታቀርብዉ ጥሩ ንው።

  13. I liked your way of expression keep it up pastor or Diacon Respected Daniel Kibret. Its so funny people don’t understand what the message is but still they curse , sad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*