ሰማያዊና መድረክ ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ
ሰማያዊና መድረክ ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ

የሰማያዊ እና የመድረክ ፓርቲዎች አመራሮች ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች የሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ከስዊድን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ዛሬ የካቲት 9/2008 ዓ.ም መወያየታቸው ታውቋል፡፡
የፓርቲ አመራሮቹ ከስዊድን ስድስት ፓርቲዎች ከተውጣጡ 11 የልዑካኑ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ እና በጋምቤላ ክልል ስለነበረው ግጭት ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

አመራሮቹ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ በተመለከተም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ የፓርቲ አባላትን እና በነጻነት ስራቸውን በሚያከናውኑ ጋዜጠኞች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እየጨመረ መሆኑንና በሀገሪቱ ፓርላማም አንድም ተቃዋሚ ድምጽ የማይሰማበት መሆኑን እንደገለጹላቸው ታውቋል፡፡
የስዊድን ፓርላማ አባላትም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉት ስላለው የፖለቲካ እንቅስቃሴና በጋራ ስለሚሰሩበት ጉዳይ ጥያቄ አንስተው በፓርቲዎች አመራሮች ገለጻ እንደተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የስዊድን የፓርላማ አባላት ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር እንደተወያዩም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቡዳው ፖለቲካችን
በተጨማሪም ለልዩ ሚስጥራዊ ግንኙነቶችን ለማዳመጥ ወያኔ ላለፋት 3 አመታት የውጭ ጥሪን በሀገር ውስጥ ቁጥር ጠልፎ በማስቀረት ጥሪዎ ከሀገር ውስጥ እንደሆነ በማወናበድ ምስጢራዊ የድምፅ አቀዳድ መሣሪያን ተግባራዊ አርገው ይገኛሉና ምንም አይነት መረጃን በሞባይልና በመስመር እንዳትጠቀሙ ልብ ያለው ልብ ይበል ሁለተኛውን አማራጭ ተጠቀሙ።
ሞት ለወያኔ የብሄር ፖለቲካን ለመቅበር ዝግጁ እንሁን
********************************
This is it WOYANE IS DONE……..SWEDEN WOW
ምሁር ማለት ምን ማለት ነው በኢትዮጵያ ሁኔታ?
ለሕዝቦች አንድነት ወይስ የዐንድነት ስጋት ዘርኝት፣ጎጠኝነት የዘመናችን በሽታዎች ለኢትዮጵያ ነቀርሳ እየሆነ ነው!
የምሁራን ግብ ምንድን ነው? እስቲ እንወያይ እንነጋገር ነገሮች አሁን አሁን በሃገራችን ጥሩ አይደለም !
ነገር ግን ሕዝብ ያውቀል፣ ያስተምራል፣ትግስት አለው፣ምሁራንንም ይመራል ያስታርቃል ሆዴ ሰፊውም ሕዝብ ነው!
ሃገር አሳድጋ፣አስተምራ፣ለወግ ማዕረግ አብቅታ ዛሬ ለምንድን ነው ብሔራዊ አንድነቷ መስቀለኛ መንገድ ላይ ያለው?
ምሁራን ተብየዎች ጠባብ አዕምሮ ያላቸው ለምንስ ደጋፊ አገኙ?
ለሃገር የሚበጀው ልዩነት ሳይሆን አንድነት ነው? በኢትዮጵያ የምሁራን ሴራ?
ሳተናው አሊ