ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የደህንነት ቢሮው አለመተማመን ሰፍቷል::

ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የደህንነት ቢሮው አለመተማመን ሰፍቷል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianSecurity‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎ChangeinEthiopia‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ለሹሞቻቸው እና አባሎቻቸው የዛቱበትና የወልደስላሴ እጣ ካማራቹ በያዛቹን መስመር ቀጥሉ ብለው ያስፈራሩበት ግምገማ እና አባላቱን ከሞባይላቸው ጀምሮ እስከ ቤት ጓዳቸው የተፈተሸበት ግምገማ ካለቀ በኋላ በደህንነት ቢሮ ውስጥ አለመተማመኑ ከመስፋቱም በላይ የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች በሁለት መንገድ ከቢሮው ይወገዳሉ ተብሎ ይጠበቃል::በከፍተኛ ደረጃ መሰሪ እና አድብቶ አጥቂ እንዲሁም በቅርቡ የሲአይኤ ተባባሪ አባል ሆነው የታጩት በመለስ ዜናዊ አስተዳደር ወደ ጎን ተገፍተው መለስ ከሞተ በኋላ የአንበሳውን ድርሻ የያዙት አቶ ጌታቸው አሰፋ ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ ከምክትላቸው ከአቶ ወልድስላሴ ጀምሮ የሚፈታተኗቸውን ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች እርምጃ ወስደውባቸዋል ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::

በደህንነት ቢሮ ውስጥ እንደ መርዝ ጦር የሚፈሩት አቶ ጌታቸው ገነው ለመውጣት የማይፈልጉ ሲሆኑ በደህንነት ባለስልጣናት እና በአባላቱ መካከል አለመተማመ እንዲኖር እርስ በእርስ እንዲፈራሩ እና በግምገማ አንዱ ሌላውን እንዲያንኳሥ እንዲሁም የሌሎች ብሄር አባላት አንገታቸውን እንዲደፉና በሽብር በጥርጣሬ እና በፍርሃት እንዲኖሩ የሚሰራ ቡድን እንዳላቸው ይታወቃል::ባለፍው የተካሄደው ግምገማ የፈጠረው አልመተማመን 132 የደህንነት አባላት ስራቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ማመልከቻ ያቀረቡ ሲሆን ውጭ አገር ለትምህርት ተልከው የነበሩ የኦሮሞ ብሄር የደህንነት አባላትም በድንገት ወደ አገር ቤት በማስመጣት ትምህርታቸውን እንዳይቀጥሉ መደረጉ ምንጮች ተናግረዋል::

ከሁለት ወር በፊት የተካሄደው ግምገማ በተለይ የሕወሓት ሰዎች የሆኑትን የትግራይ ተወላጆች ያላጠቃ እና የሌሎች አባላት መብት የገፈፈ ያዋረደ መሆኑ በቢሮው እስጥ ያለውን የአለመተማመን መንፈስ ያሰፋ ሲሆን አባላቱ አንገታቸውን እንዲደፉ ከማድረጉም በላይ እርስ በእርስ እንዲናቆሩ በፊትም የራስ መተማመን የሌላቸው ከመሆኑም በላይ ከቀድሞ በበለጠ ራሳቸውንም እንዳያምኑ አድርጎ የሰበራቸው መሆኑ ሲገለጽ ምንጮቹ እንዳሉት በደህንነት ቢሮ ውስጥ የበላይነት ለመያዝ ተቃርቦ የነበረው የብአዴን አባላት ሃይል አከርካሪው የተመታበት ግምገማ የነበር መሆኑን ገልጸዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

12 Comments on “ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የደህንነት ቢሮው አለመተማመን ሰፍቷል::”

  1. አንባ ገነን ዘራፊ ወንበዴ አገርን ቆርሶ የሚሸጥ ሽፍታ መንግስት ነኝ ሲል አያፍርም? ከአዶልፍ ሂትለር፣ ከመሰሎኒ፣ከኢዴያ ሚንዳአዳና ከ… ወዘተረፈ የበለጠ አንባ ገነን ነዉ ወያኔ

  2. Minilik,
    You do not know what you are talking about. For sure we know very well you do not have any source in the Ethiopian intelligence. You Scribble your hearsay and imagination and what you wish to happen. Wish is one thing no body could be denied. You have been allteging all sorts of things. Go and refer to what you have writtenso far. Nothing happened as wished for so far. Give some respect to yourself if you do not respect your readership.

  3. Comrade workers:
    Thank you for coming and
    listening my discourse on
    socialism – communism of karl
    marx, markeshaw.
    Socialism is nationalization =
    consfication of all the means of
    production = of all income
    generating properties, services,
    resources by the government of
    the workers for the common and
    equal use of society.
    Socialism wealth distribution
    principles are:
    1st stage socialism for each
    according to each ability
    2nd stage communism for each
    according to each need.
    Upto now no pure, real socialism
    exists due to u.sa, uk, and other
    capitalist-imperialists fight against
    it, because it is anti- exploitation
    and oppression, e.i., against
    capitalism-imperialism.
    Socialism is equality, justice,
    peace. Humanity, cooperation,
    internationalism, Friendship,
    comradeship, heaven in earth.
    Soon socialism will replace
    capitalism as an unenvitable
    human historical development
    necessity.
    Currently Cuba and north korea
    are relatively near good socialists.

  4. nothing is true in this news.

    hard to believe, or take it serious.

    source of the news/ FETERA/ WUSHET……….

  5. ተውኝ ወንድሞች ብአዴን የሚባል ድርጅት የለም!
    ቢኖርማ ራሳደጄን ተራራ ወደትግራይ ክልል ሲከለል ለምን የሚል ጥያቄ ያስነሳና መፍትሄ ይፈልግ ነበር
    አማራ አከርካሪው ተመትቶል ኦርቶደክስም፣እስልምናንም ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ በወያኔ ሃይል ተመትቶል
    የብአድን አባላት የሚባሉት ሃይሎች ሆዳሞችና ከርስ አደሮች እና ከዚያ ውጭ ያለ ካለ አርካሪውን በተደጋጋሚ የተመታበት መሆኑን ይታወቃል፡፡
    ሰ.አ

  6. በተጨማሪም ለልዩ ሚስጥራዊ ግንኙነቶችን ለማዳመጥ ወያኔ ላለፋት 3 አመታት የውጭ ጥሪን በሀገር ውስጥ ቁጥር ጠልፎ በማስቀረት ጥሪዎ ከሀገር ውስጥ እንደሆነ በማወናበድ ምስጢራዊ የድምፅ አቀዳድ መሣሪያን ተግባራዊ አርገው ይገኛሉና ምንም አይነት መረጃን በሞባይልና በመስመር እንዳትጠቀሙ ልብ ያለው ልብ ይበል ሁለተኛውን አማራጭ ተጠቀሙ።

    ሞት ለወያኔ
    የብሄር ፖለቲካን ለመቅበር ዝግጁ እንሁን

    ********************************

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*