የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ከደሃው ጉሮሮ መንጠቁን ተያይዘውታል ኢትየጵያ ውስጥ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡

ኢትየጵያ ውስጥ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDFCorruption‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Ethiopianoppositionparties‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ከደሃው ጉሮሮ መንጠቁን ተያይዘውታል ግን እስከመቼ የለውጥ ሃይሉ በመታገል ፈንታ እርስ በርስት እየተባላ የወያኔን እድሜ አሳልጦታል:: አገሪቷ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ወደላይ እንዲያሻቅብ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የሙስና ጣርያ መንካት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አሳሳቢ መሆኑን መግለጽ ቀርቶ የእገሌን አገር ደረጃ አያክልም የሚለውን አባባል የኢትዮጵያ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡በአሁኑ ወቅት ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቷል፡፡ ባለጉዳይም ጉቦ ካልሰጠ ጉዳዩን እንደማያስጨርስ፤ ጉዳይ ፈጻሚም ገንዘብ ካላገኘ ጉዳይን ማስጨረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በገሃድ በሚታይበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በጉምሩክ፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሆስፒታሎች፣ በኢሚግሬሽን፣ ወዘተ ጉዳይን ለማስጨረስ ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡

ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡ ጉቦ የማይቀበል የማይረባና የማይጠቅም ተብሎ የሚሰየምበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን እያንዳንዱ ሰው በሚገባ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህ በመሰለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም ሲባል ምን ማለት ነው? መረጃው የተገኘውስ ከየት ነው? ከተበዳይ ወይስ ከበዳይ?ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢዎች አነስተኛም ይሁኑ ትላልቅ የፕሮጀክት ጨረታዎች ያለኮሚሽን ክፍያ የተፈጸሙ ናቸው የሚል ጥናት ፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ምንልክሳልሳዊበአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግዢዎችና ጨረታዎች ሕጋዊነትን ለማስያዝ ብቻ የሚካሄዱ ካልሆነ በስተቀር፣ አስቀድሞ ከታቀደውና ከታለመው ሰው ወይም ድርጅት ውጭ ማንም እንዲገባ በማይፈቀድበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የዋህ ሰው ሳይቀር በሚገባ የሚረዳበት ደረጃ ላይ እኮ ነን ያለነው፡፡

ከሀብታም ነጋዴዎች ጋር የሚያያዝ ከሆነ ቀድመው ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ከሚጥሩ ይልቅ ለግልግል በሚሯሯጡበት አገር ላይ እያለን፣ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ነው እንዴት ይባላል? በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሮች ድረስ በሀብታም ተፅዕኖ ሥር በወደቁበት፣ ጉቦ በመቀበል የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡበት፣ ሀቅን በገንዘብ በሚለውጡበት፣ በጠራራ ፀሐይ ብሉ ሌብልና ቪኤስኦፒ በካርቶን በሚጫንበት፣ የሰው ሕይወት በገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት፣ ዓይን ያወጡ ሙሰኞች በሰፊው ሕዝብ ፊት ደረታቸውን ነፍተው ጉራቸውን በሚነፉበትና ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ወቅት መሆናችን እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም እንዴት ይባላል?

የመንግስት ባለስልጣናት የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል ሙስና ኮሚሽን አማሯል።ትናንትና ለሀቅ፣ ለዲሞክራሲና ለአገራቸው ብልጽግና ሲሉ የወጣትነት ዕድሜያቸውን በረሃ የወጡ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ቀብረው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ጀግኖች በሙስና ተነክረው ሀብታም ሥር በተንበረከኩበት ወቅት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ቅጥረኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሠራርና መመርያዎችን ጥሰው በኔትወርክ በተሳሰሩበት ወቅት፣ እርስ በራሳቸው እሳትና ጭድ ሁነው በማይተማመኑበት ወቅት፣ ለሕዝብ ህልውና ዋስትና በታጣበት ወቅት፣ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሳስብ አይገባም ተብሎ እንዴት ይነገራል?

ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ፣ ከአሳሳቢነቱ በላይም ጊዜ የማይሰጠውና ወረርሽኝ በሆነበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይም ሙሰኞች የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ወሬዎች በሚናፈሱበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንዱ ቅንጣት ጥፋት የሌለው ይመስል ከራባቱን አስሮ ‹‹ሙስናን እንዋጋ›› የሚለው ከበስተጀርባው ትልቅ ጥፋት ተሸክሞ ነው፡፡

እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ እኛስ ምን እየሰራን ነው ራሳችንን እንጠይቅ ነጻ ለመውጣት ከመታገል ይልቅ እየተኮራኮምን የራሳችን ባሪያዎች በመሆን በባዶ ሜዳ እየዛረጥን ስለምንገኝ ከዚህ ስህተታችን ተምረን ልዩነት በማቻቻል ታግለን በሕዝብ ትከሻ ላይ የተንሰራፋውን የወያኔ አገዛዝ እናስወግድ!!! ‪#‎ምንልክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

12 Comments on “የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ከደሃው ጉሮሮ መንጠቁን ተያይዘውታል ኢትየጵያ ውስጥ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡”

  1. Minilik
    ante yemitfelgew eko,, weyane hedo

    shabya indefenechibin new kkkkkk
    le shabya qetregna kemegezat

    weyanen be Hizb amets mabarer new yemebejen !!

    ::

  2. How we can stop it is by first and formost getting out of the ethnis box woyane locked us in and think out side the box.ኦሮሞዎች ወልቃይት መሬት ላይ የወያነን አፍንጫ ማድማት መቻል አለባቸው ወልቃይቶችም ኦሮሚያ ውስጥ ሀደው የወያነን ቭፍንጫ ማድማት መቻል አለባቸው።we need to get out of ክልል።Thats one step.እንጅ ወያኔ በቀደደልን ቦይ ሆነን ወያነን ማሸነፍ አንችልም ! ! !

  3. የባንዳ ልጆች ድሮውንስ ለሀገር አያስቡም አያቶቻቸ ውም ድሮ ጣሊያንና እንግሊዝን ከወደብ መርተው አምጥተው ሀገር ለወራሪ አሳልፈው ሰጥተዋል

  4. @ dedeb from dedebit where do you live i hope you are the man of the century. But to much bla bla.there is no any change from USA or from the WEST.if you are the man why not go to eritrea.like the brave brhanu nega.call me woyane.but i am from wollo.i am OROMO FIRST.belive or not.

  5. Here tesfa gebreb is dirku is oromo first, the same person.
    This homosexual individual is pschiatrically mad of amarophobia by which he has been committing continuous serious crimes of inciting ethnic violence against amaras.
    This homosexual person is working restlessly in anti-amara propoganda with oromos’ pseudo support, aiming to create a mess in ethiopia and to dismantle it for eritrea good futurity.
    This mad evil individual is present by changing names and repeatedly posting extremely hateful anti – amara propogandas, against every good article or posting for the good of ethiopia.
    Donot think these postings are from olf or onegs. They arenot.

  6. ቀን ጥር 24 2008 ዓ.ም ባህርዳር ከተማ የተደረገ ስብሰባ የቀረበ
    የአማራ ልጅ የሆቴል ልቅምቃሜ የመገብ፣ይገደል!ይሥደድ፣ይዋረድ
    ለመሆኑ አማራ ሃገሩ የት ነው? ኢትዮጵያዊነት መስዕዋት ያስከፍላል! ስማኝ አማራ ሆይ!
    የአማራ ልጅ ፈሪ ነው እንደ? መሬቱን ለሱዳን ለትግሬ ለጡበት ብአዲን ጡት ነካሽ ጋር በመተባበር ከሃገሩ አባረሩት ለምን?
    አሁን የአማራ ጥያቄ መሆን ያለበት ሃገሩ የት ነው? የዜግነት ጥያቄ ነው? የምንነሳው አማራ ለኢትዮጵያ አንድነት መስዕዋት አልከፈለምን?
    አድግራት 15 ፋብሪካ ሲከፍቱ ባህርደር ላይ 1 ፋብረካ ብቻ ነው የተከፈተው?
    የአማረን ርስት በመንጠቅ ትውልድን ለአረብ መሽጥ፣ማሳደድ፣ማሳፈን መፍን በጅምላ መቅበር በሁመራ በአረማጭሆ የተገደሉት አማራዎች ደማቸው ፈሶ ይቀር ይሆን? አሁን ባህርዳር በትግሬ ተወላጆች በታጣቆዎች ተወራለች፣የሃሽሽ ማከፋፈያ ማዕከል አደረጎት የአማራ ልጅ አንግዳልጅ ነው ያደረጉት አማራ ነኝ እንዳይል ዘርህን ፣ጎሳህን ፈልግ እያሉት ነው?
    በግንቦት መጥተው የአማራን ልጅ ከትውልድ ቦታው አባበሩት/አባረሩን! ለምን? አማራ ፈሪ ነው እንዴ ጎዝ?
    አንድ ቡድን (ጎሳ)ተሰባስቦ መጥቶ ዘንዘልማን መሬት በትግሬ ባህርዛፍን ለመቀሌና ለአስመራ ሲወስዲ ነገ ግን ነባሮቹን አማራዎች አባረው ከአማራ ድርጅት ጋር በመሰባጠር ዛሬ አለንበት ደረጃ ደረስን ምን እንሁን ?
    ሰ.አ ከባህርዳር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*