ጋምቤላ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ነች፡፡

  • ከጧት ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ በከተማዋ ፈሷል፡፡

በትላንትናው ዕለት በአኙዋክና በኑዌር ብሔረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ በርካታ ሰው መሞቱ የሚታወስ ነው፡፡ ከሟቾቹ መካከል የቀድሞ የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሐላፊ ከቅርብ ጊዜ ጀምረው ደግሞ የክልሉ የገጠር መንገድ ስራዎች ሐላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሚ/ር ጋዳድ ይገኙበታል፡፡

አሁንም ጋምቤላ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ነች፡፡ ዛሬ ከነጋ ብዙ የተኩስ ድምፅ ባይሰማም የከተማዋ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ የመንግስት መስሪያ-ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተዋል፡፡ መላ የጋምቤላ ኗሪ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው፡፡