የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሳፍራ ስትጓዝ በነበረች ተሽከርካሪ ላይ የከፋ የትራፊክ አደጋ ደረሰ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሳፍራ ወደ አዲስ አበባ ስትጓዝ በነበረች ተሽከርካሪ ላይ የከፋ የትራፊክ አደጋ ደርሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ።ተሽከርካሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ የጭነት መኪና ጋር በመጋጨቷ ነው አደጋው የደረሰው።

ዛሬ ሰባት ሰዓት ላይ አደጋው የደረሰው በመቂ እና ሞጆ ከተሞች መካከል ላይ በሚገኘው የአዋሽ ወንዝ ድልድይ ላይ ነው።በሀዋሳ ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ስጋት ውስጥ የገቡት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ መኖሪያ በመመለስ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

የሱፍ ጌታቸው's photo.