ያሁኑ የኢትዮጵያ ሁነታ፤ ይመስላል የተምታታ – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

በአሁኑ ሰዓት የወያኔ አገዛዝ በአንድ በኩል በሕዝባዊ እምቢታ፥ በሌላ በኩል በትጥቅ ትግል ተቃውሞ በሰፊው እንደተነሣበት ይሰማል። ስሜትንና አስተያየትን ለሕዝብ ማቅረቢያውን መንገድ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለሁሉም ክፍት ስላደረው፥ ሕዝባዊ እምቢታውንም ሆነ የትጥቅ ትግሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ እንዳሉ እያነበብንና እየሰማን ነው። ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞና እምቢታ ቢቃወሙ አይገርምም። ሊታሰብበት የሚገባው ዋናው ጥያቄ የወያኔን አገዛዝ የሚጠሉ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያን የትጥቅ ትግሉንና የሕዝቡን ዓመፅ የሚፈሩት በሚገባ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው። ዋስትና ያለው ታማኝ መልስ የለም። ግን ሁኔታው ግልጽ እንዲሆን ጥያቄው መተቸት አለበት። በእኔ በኩል የሚታየኝን ከመተቸቴ በፊት ሁለት ነገሮችን በሚገባ እንድንረዳ እፈልጋለሁ።

አንደኛ፥ ትግሉን ከሚፈሩት ውስጥ አገር-ወዳድና አገር-ወዳድ መስለው የሚጮሁ ተቃዋሚዎች አሉ። አገር-ወዳድ መሰሎቹን ወያኔዎች በአገር-ወዳዱ ውስጥ የሰገሰጓቸው መሆኑን ሰምቻለሁ። አማራ መስለው ለአማራው እንደሚቆረቆሩትና በክልል እንዲወሰን እንደሚፈልጉት ዓይነት ማለት ነው። ውይይቴ ከአገር-ወዳዶቹ ጋር ነው።

ሁለተኛ፥ አገር-ወዳዱ የወያኔን አገዛዝ በሚገባው ልክ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ስለወያኔ አገዛዝ ብዙ ጊዜ የምሰማው (እኔም ሳልለው አልቀርም)፥ “ወያኔ ጨቋኝ ነው”፥” “ወያኔ ፋሺስት ነው”፥” “ወያኔ ሰብአዊ መብት የሚጥስ መንግሥት ነው” የሚሉ አገላለጾች ናቸው። እነዚህ አገላለጾች የሚገልጹት የወያኔን ዘዴ እንጂ የወያኔን ማንነት አይደለም። ወያኔዎች ይጨቁናሉ፤ እንደፋሺስቶች ዘር እየለዩ ሰው ይፈጃሉ። ይኼ ዘዴያቸው ነው። በዓላማ ግን አይመሳሰሉም። የወያኔዎች ዓላማ ዝርፊያ ነው–ድርጅታቸው የዘራፊ ድርጅት ነው።

ስጋቶች፤

ከወያኔ ቀጥሎ የሚመጣውን የሚፈሩ ለሀገርና ለሕዝብ አሳቢዎች “ከዘራፊ (ከማፊያ) የሚብስ ይመጣል ወይ?” ብለው ማሰብ አለባቸው። ወያኔዎች ኢትዮጵያ ለኛ ካልሆነች እናወድማታለን ብለው ምለው ተነሥተዋል። ዓላማቸውን እንዲቀይሩና ዲሞክራሲን አብረን እናስፍን ቢባሉ፥ ብዙ ዓመታት ቢወተወቱ፥ አሻፈረን ብለዋል። እንዲህ ከሆነ፥ የሀገር-ወዳዱ አማራጭ ምንድን ነው? “ከሚያወድሟት ይውሰዷት” ይበል ወይስ የሚመጣውን ደግፎ ውጤቱን ለሁሉ የሚጠቅም ለማድረግ ዘዴ ይፈልግለት?

አገር-ወዳዱን የሚያሰጋው አንዱ የኦሮሞዎች ጥያቄ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት የሆነው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማፊያ ቀምበር ተጠምዶ ሳለ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ኦሮሞች ብቻ የተጠቁ አስመስለው ሲናገሩ መሰማታቸው ነው። አገር-ወዳዱ የሚለው “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲጠቃ ሁላችንም በአንድ ድምፅ እንቃወም፤ የሚጠቃው ኢትዮጵያዊ እንጂ፥ ኦሮሞ፥ ቅማንት፥ አማራ፥ ጉሙዝ፥ . . .፥ እስላም፥ ክርስቲያን አይደለም” ነው።  አማራውንና ኦርቶዶክሱን የበለጠ የሚያጠቁት ለሀገሪቱ አንድነት ማገር ሆነው ስለገኟቸው ነው።

ኢትዮጵያን በአስተዳደር ጊዜ በጎሳ፥ በሃይማኖት መከፋፈል የወያኔ ተንኮል ነው። በአስተዳደርና በፖለቲካ ጊዜ፥ ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው። ለጎሳና ለሃይማኖት ማሰብ  ክፋት የለበትም።ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ፥ መከልከል የለባቸውም፤ መብታቸው ነው። መብቱም ባህል ማዳበር ነው፤ ግን መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ሊገባ እንደማይገባው ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡም የሃይማኖቻቸውንና የጎሳቸውን ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ሊያደርጉት አይገባም። አገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው።

የከተማዎች መስፋፋት፤

ከተማዎች ሲስፋፉ ከከተማ ውጪ የነበሩ መሬቶችን ወደከተማ ክልል ማስገባት የማይቀር ነው። በዚህ አጋጣሚ መሬቱ ወደከተማ የተከለለለት ሰው ሎተሪ እንደወጣለት ነው የሚቈጠረው። ግማሹን ሸጦ የሚሊዮን ብር ጌታ ይሆናል። በግማሹ ላይ የሚኖርበትንና የሚያከራየውን ቤት ይሠራበታል። ከተራ ገበሬነት ወጥቶ ዘበኛና አሽከር ቀጣሪ ጌታ ይሆናል። ግን ማፊያዎቹ ወዲያው ከተፍ ይላሉ። ገበሬው የወጣለትን ሎተሪ (መሬቱን) ቀምተው ባለቤቱን አልባሌ ቦታ አሽቀንጥረው ይጥሉታል። ተቃውሞው ዛሬ ተጀመረ እንጂ ዘረፋው የተጀመረው ቀደም ብሎ ነው። ማፊያዎቹ ከተማ ውስጥ የሚያበለጽግ ቦታ ሲያዩ ባለቤቱን ወደሩቅ ቦታ ጥለው እነሱ ፎቅ ሠርተውበታል።

በደሉ የደረሰው በኢትዮጵያውያን ላይ ነው፤ የአሁኑን በደል የተቃወሙት ግን ኦሮሞዎች ናቸው። የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን እንጂ ኦሮሞዎች ስለሆኑ አይደለም። ገብሬዎቹ ኦሮሞዎች መሆናቸው አጋጣሚ ነው። ጉራጌዎች፥ ዶርዜዎች፥ አማሮች ቢሆኑም ይዘረፉ ነበር። መቃወም ያለብን ማንም ቢዘረፍ ዝርፊያውን  እንጂ ማን ተዘረፈ ብለን መሆን የለበትም። የምናደርገው ግን በወያኔ አስተሳሰብ ለጎሳችን እያሰብን ሆኗል። አማሮች ሲፈናቀሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ተቃውሞ ያላሰሙት ስለዚህ ነው። እንዲያውም የአፈናቃሊውና የአራጁ  አካል ሆነው ነበር። ተቃውሞ በተነሣ ቍጥር አገር-ወዳዱን የሚያሳስበው ይኸ ሁኔታ ነው። ማፊያዎች ማንንም ኢትዮጵያዊ ሲዘርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሌላው ኢትዮጵያዊ ዝም ካለ የአንድ ሀገር ሕዝብ መሆናችን ይቀራል። ለጎሳ ማድላት ካማረን ጎሳችን ኢትዮጵያ ናት።

የትጥቅ ትግል፤  

በሰሜን በኩል የተነሣው የትጥቅ ትግል የሚያሰጋቸው አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን አሉ። “እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በራየ” (እባብ የነከሰው ልጥ ቢያይ ደነበረ) የሚለውን አባባል “እባብ ያየ እባብ ቢያይ በራየ” እንደ ማለት አይተውታል። አይፈረድባቸውም፤ በኛ ሀገር እንኳን፥ መጀመሪያ ደርግን፥ አሁን ደግሞ ወያኔንና ሻዕቢያን አይተዋል። እነዚህ በትጥቅ ትግል አሸንፈው ሥልጣን የያዙ ድርጅቶች የዲሞክራሲ ስም ሲጠራ ዛር እንደያዛቸው አፋቸው ዐረፋ ይደፍቃል፤ እንደ ተከበበ አውሬ ይወራጫሉ፤ ሰው ይፈጃሉ። “በትጥቅ ትግል የሚመጣ ሁሉ ከነዚህ እንደማይለይ ለምን ከታሪክ አንማርም?” ይላሉ።

ግን አማራጭ ሲጠፋ ከብዙ አንድ አይጠፋም ብሎ ዕድልን መሞከር የግድ ነው። የዛሬው ተቃውሞ ለዕድል ብቻ የሚጣል አይደለም። የታጣቂዎቹ ዓላማ እንደ ወያኔ ራሳቸውን ወይም አንድን ጎሳ ለማበልጸግ አይደለም (የቱን ጎሳ?)። ወያኔዎች ትግል ሲጀምሩ እነማን እንደሆኑ ልጆቹን አናውቃቸውም ነገር። ዓላማቸው ትግራይን ለይቶ ለመጥቀም መሆኑን ግን ሳይደብቁ ነግረውናል። ዛሬ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱትን ግን እናውቃቸዋለን። የወያኔ ብጤዎች አይደሉም።

ሁለተኛም አገር-ወዳዶች የትጥቅ ትግሉ አካሄድ ካሰጋቸው መድኃኒቱ ተደባልቀው በጦሩና በአመራሩ መሳተፍ ነው። ለመሳተፍ ፈልገው  እምቢ እንደተባሉ አልሰማንም። የምንሰማው ቁጭ ብለው ተቺዎችን ነው። “የምትሰጉትን ውጤት ለማስወገድ ለምን አብራችኋቸው አትታገሉም?” ሲሏቸው፥ “በዚያ በኩል የሚካሄ ትግል ወያኔን ሊጥል አይችልም” ይላሉ። የትጥቅ ትግሉ ውጤት ከሌለው ሊያሰጋቸው አይገባም ማለት ነዋ!! ወያኔዎችም ችላ ይሏቸው ነበር። የምንሰማው ግን ወያኔዎች በየቀኑ የሚያወርዱባቸውን የጥላቻና የፍርሃት ፕሮፓጋንዳ ነው።

ሌላው ስጋት እርዳታው ከኢሳይያስ አፈ ወርቂና ከሻዕቢያ መምጠቱ ነው። “ኢሳይያስና ድርጅቱ ለኢትዮጵያ በጎ አያስቡም፤ ቢያስቡ ኖሮ የኤርትራን መገንጠል ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሔ አያደርጉም ነበር” የሚል ነው። ይኸንን ልንክድ አንችልም፤ እውነት ነው። እርዳታቸውን ለማግኘት ስንልም ታሪክ አንከልስም። ኤርትራ ወስጥ አንድነቱን መቃወም የተጀመረው ከፌዴሬሽኑ መፈጠርም መፍረስም በፊት ነው። ሻዕቢያ ጦር ያነሣው ፌዴሬሽኑ በመፍረሱ ምክንያት አይደለም፤ እሱ ሰበብ (casus belli) ነበረ።

ፌዴሬሽኑ ማንንም ኤርትራዊ ያላስደሰተ፥ ትርጕሙ ለሁሉም እንቆቅልሽ የሆነ  ዱብ እዳ ነበር። አንድነቶች የተቀበሉት ውሕደቱን ሲያደናቅፍ ባለማየታቸው ነው። የኤርትራ ፓርላማ ፌዴሬሽኑ እንዲነሣ ሐሳብ ሲቀርብለት፥ የአንድነት አባላት ያሉት፥ “ለመሆኑ ምንድነው እሱ፥ አንድ ሆነን የለም እንዴ? ፌዴሬሽን የሚባለው ለአንድንታችን ገደብ ለመፍጠር የታቀደ ኖሯል ወይ? ኧረ ወዲያ ጣሉት” ነው።

ኢሳይያስ የሚሠራው ሥራና የሚያካሂደው ፖለቲካ ያቺን የነጠቃትን ግዛት ለመጥቀም ብሎ ነው። ከወያኔ በቀር ለያዘው አገር ጥቅም የማይሠራ ገዢ የለም። “ወያኔዎችን የሚቃወሙ ድርጅቶችን የሚደግፈው ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው” የሚል ያለ አይመስለኝም። የአንድ ሀገር ገዢዎች ለሌላ ሀገር ጥቅም አይሠሩም። ግን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባናውቅም (ልንጠረጥር እንችላለን) ኢሳይያስ  የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ተቃዋሚዎችን ይደግፋል። የሚፈልገውን ቢያገኝ/ሲያገኝ ድንገት ድጋፉን ሊነፍጋቸው ይችላል። በዚህ ጊዜ የወያኔ ማፊያ ተቃዋሚዎች ግዴታ ድጋፉን  እስካገኙ ድረስ  የሚያደናቅፉ ጥያቄዎችን ሳይሰሙ ቶሎ ቶሎ በድጋፉ መጠቀም ነው። “ጀምበር ሳለ ሩጥ . . .” ዋናው ነገር በሰላማዊ ትግል የዘመቱት የትጥቅ ትግሉን ብቻ ተስፋ በማድረግ የራሳቸውን ትግል እንዳያረግቡ ነው።

መደምደሚያ፤

ትግሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ ድምፃቸው በየቀኑ ስለሚሰማ፥ ሁኔታው የተምታታ ይመስላል፤ ግን አይደለም። ምክንያቱ የተለያየ ይሁን እንጂ ዓላማው አንድ ነው። ከአገር-ወዳድ ነን ከሚሉ ሳይቀር መጠን የሌለው ስድብ ሲወርድባቸው ጆቷቸውን ዘግተው ለነፃነት መታገላቸው የሚያስደንቅ ነው።  አሸንፈው፣ ሥልጣን ሲይዙ ማየት እንፈልጋለን። ይዘው እነሱም እንደሌሎቹ የሚያስቸግሩን ከሆነም፥ ዕድላችን ነውና እንደፈረደብ አዲሱን (ሌላውን ዓይነት) ችግር ለማስወገድ እንታገላለን። ወያኔዎች አንገፍግፈውናል።

33 Comments on “ያሁኑ የኢትዮጵያ ሁነታ፤ ይመስላል የተምታታ – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ”

  1. መተማ ላይ ለአገር ክብር የተሰየፉት ዮሃንስ
    ከትግሬ አብራክ ተወለድኩ የሚለው ወያኔ
    ድጋሚ አገር በመሸጥ ሰየፋቸው#

  2. “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲጠቃ
    ሁላችንም በአንድ ድምፅ እንቃወም፤ የሚጠቃው ኢትዮጵያዊ እንጂ፥ ኦሮሞ፥ ቅማንት፥ አማራ፥ ጉሙዝ፥ . . .፥ እስላም፥ክርስቲያን አይደለም”

    ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው።

    ማፊያዎች ማንንም ኢትዮጵያዊ ሲዘርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሌላው ኢትዮጵያዊ ዝም ካለ የአንድ ሀገር ሕዝብ መሆናችን ይቀራል።

    ለጎሳ ማድላት ካማረን ጎሳችን ኢትዮጵያ ናት።

    እባብን ያላየ ለወሥፋት ይሸሻል እና ከበረታን ወያኔን በቅርቡ እናሥወግደዋለን።

    ጥሩ ምክር ነው

  3. ኮለኔል (ፕሮፌሰር)ባሉት ሁሉ ባልስማማም ከእድሜዎ ጋር የሚስተካከል ምክር ብጤ ስለ ፃፉ የድርሻዎትን በማለትዎ ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ሌላው የዛሬዉ ትውልድ እርሶ ከሚያቁት የተለየ ነው፡፡ አውቅልሃለሁ ባዩን ሁሉ ለይቶ አጣርቶ ነው ወደ ተቃውሞ ምርጫ ያዘነበለው፡፡ አሮጌዉንም ናፋቂ ኣይደለም፣በአሁኖቹ ብልጣብልጦችም አይሸወድም። ችግሩ ሁሉም ፖለቲከኛ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የሁሉንም ህዝባችንን ጥቅም ቢያስቀድም የተሻለ ዉጤት ላይ ባፋጣኝ ይደረስ ነበር፣ ምን ያደርጋል ታድያ፡ የድሮዎቹ እኛ ካልተመለስንና የረሳነዉን ካልቦጨቅን እያሉ ሲያልሙ፣ ሌሎች ደግሞ የለም አሁንስ በቃን ነው ነገሩ፡፡
    ሌላው፡ ለተዘራፊው የሚያዝን አንጀት ነው ዝርፊያን የሚያወግዘው አንጂ፡ ማይሙት፡ አሁን የተዘረፈው ንብረት እና የተፈናቀለው ገበሬ ከርስዎ ወገን ቢሆን መቸም አንዲህ አድርገው አይፈርዱ፡፡ የአዞ እንባ ይሉታል ይህ ነው፡፡

  4. “ሞትማን” ፕሮፌሰሩ ስለሰጥኡት አስተያየት መተቸት ሲገባህ “ማሽሙጤጥን” መረጥክ::ሰው ማንን ይመሰላል? ቢሉ ንግግሩን ይባላል::አንተ እሳቸውን ሰደብኩ ብለህ አነተነትህን አጋለጥክ::በጥላቻ አይምሮው ከደነዘዘ ሰው ምን ትምህርት ይገኝኣል?ለመሆኑ አንተ በሰው አይምሮ ነው የምታሰበው?

  5. የኢትዮጵያ ሁኔታ አልተምታታም የተምታታባቸው ግን አሉ፡፡የአንዳንዶቹ በእድሜ መጃጃት የመጣ ይሆናል ብዬ ስለማስብ አልቀይምባቸውም፡፡

  6. This archaic and out of date guy is paranoid about the Oromo- all the time. He is persistently Oromo-phobic for reasons he would not reveal publicly. The young fighting Woyanne could be his grand children and also great grand children, who are almost free of any racial/ethnic animosity. Their age ranges from as young as 8 up to a maximum of 25 years.

    They are the victims of Tigre savagery and consider the aggressor as their oppressor. Thus, and aslo due to the generation they belong to have no sentiment against the Amara.

    Even so, this old guy who needs to be placed in a museum is waving the fun of hatred and division – all the time. It does not serve any positive purpose. People are trying to reconcile and build a united Ethiopia. This is true, especially for the two big nationalities, i.e. Oromo and Amara.

    Someone needs to tell this old individual that his time is up, that it is a new generation in the making of new history, that his vindictive attitude towards a certain group in Ethiopia would not work (except aiding Woyanne’s agenda of divide and rule), that he enjoys his old age in a corner in Minnesota and wait and see events unfolding in a more constructive manner, etc.

  7. yetun ye Titq tigil new yemeyawerut ????

    be Areb ena be shabya telaT Guya yegemawin, 50 yemaymola serawi tor ??

    kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

    gidyelotim , weyane be HIZBAWI AMETS YEGERESESAL 111

    yetagesu !!!!!!!!!!!

  8. ሱዳን መተት ወያኔ መሬት ሊለግሰበው? ዴቼ ትበላለህ መስሎሃል ታሪክ አላነበብህም

  9. this is a confusion and nightmare; how could this guy try to turn down peoples revolution? is really thinking for Ethiopian people sustainability? nothing else his is a fault digger.

  10. GETACHEW Haile,
    You expirations date itself had expired before Yekatit 1965. So as your political gritts. Check into cheapest nursing home, worry about your final days.

  11. You why I’m not visting the Ethiomedia website
    it’s b/s the page will always filled by the
    NEFTEGNA PORFESSORS AND DOCTORS AND ITS SO
    disgusting visting that website . This days around
    I become biased to read any articles by Professors
    and Doctors and most of them are more feudal than
    their fathers and retarded too.

  12. Professor getachew haile, amara
    endehonu ena derg aseqaqi gudat
    yefeTemebachew mehonun
    semchalehu.
    And weqt, ” ye etiyopiya hzb woyanie sichawetbet zm blo miyayew melak le mehon weys
    ensesa”, yalutn hulie astwsalehu.
    Ahun yeseTut scientific analysis of
    current ethiopian politics or
    asteyayet ejg reqiqi ena Teqami weqtawi new. ETer mTn blo hulunm chgrachn qulch adrgo
    yabrara Tuhuf slehone lieloch
    mhuran biketelut mñotie new.
    Yetelemedut Tere-amara woyaniewoch ye professorun zer bemaseb yedro nafaqi, gizie yalefebet, enddrow engzachuh bay yemil mnm kaqerebut hasab gar gnñunet yelielew yemaTlalat asteyayet seTtewal. Baltebal ena
    beliele guday mawenabed new.
    Tola yemil sm, professorun yale bahriyachew oromo phobia
    nachew blual.
    Gn yerasun Tlq yehone paranoidal amaraphobia agalTual. Sr besedede ye amara Telacha feTari yangol, ye aemro beshta yeteTeqa mehonun asaytonal.
    Professoru kemilut yeteleye hasab saynorew ena balasayut Tere-
    oromo bahri yzelfachewal.
    Yh chgrachn woyanie ena olf,
    ohdd nachew.
    Semonun sle andnet ye miyaworut ewnet new weys ahun woyanie skichenef new blen
    beTlqet endnasb ena endnwesn
    ygabzenal. BergT olf bahunu saat bedn mut new, gn kewoyanie yeteleTefew ye ene muktar kedru opdo, mnalbatm yebulchaw -merar drjtm opportunistic (agaTami felagi) new. Etiyopiyawinet sayhon le gl bhierachew new miyasbu.
    Degnetu ye oromo hzb megenTel
    aysham.
    Gn shabiya enj ye eritrea hzbs meche megenTel felge, woyanie endemigezan, shabiya asgeddot enj.
    Mefthiew mefalem new TegenTayn.

  13. ሙላት ፡ አንተ የሳቸዉንም ምክር ዪሁን የኔን አስተያየት በግባቡ አላነበብከም፣ ጥላቻ ላልከው፣ ያደኩበት ማህበረሰብ ጥላቻ ስላላስተማረኝ አላውቀውም፡፡ የተሰማኝን ማለት ደግሞ ተፈጥሮ የሰጠኝ መብት ነው። እኔን ያላስደሰተ ሁሉ ይጠላኛል አትበል። መጻፍም መብት እንደሆነ ሁሉ፣ መተቸትም መብት ነው። አ ን ብ ብ ።

  14. የተለየ ሀሣብ አፍላቂን መሥደብ ማሠር መግደል ለወያኔዎች አዲሥ አይደለም ግን ትውልዱ ወያኔን ያሥወግዳል ህዝባዊና ብሄር ተኮር ያልሆነ መንግሥት ይመሠርታል።

  15. ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው።

    አሁን የታል?

  16. Ye Ignih talakina be idime ye beletsegu abat betam garmognal.

    Be amarigna, tiliku dabo lit hone yibalal. Be oromigna degmo, Sangaa guddaan siribsiisee gasha jennaan —balleessaa jedhama.

    We expected an advise of wisdom from an opinion leader like our grandfather, prof. Getachew Haile. What we got is the oposit. He is preaching division instead of unity and suspicion instead of trust. In my opinion, if we waste this oportunity to nurture the unity of Amhara and Oromo we all be regret. I think, the prof. Is unintentionally serving the wuyanes.

    I always use the 3 languages to make my point. This is because I am not good any of them as a result of the educational system my generation have been through. Appology.

  17. Ye professor getachew haile,
    Tuhuf ende berkata mhuran or
    professors Tuhufoch rejim alemehonu bcha sayhon
    yagerachn ye politika chgroch
    bemulu ejg aTrto aqrbuachewal.
    Yenihn mhur hasab yemiqawemu
    ke woyanie liela megenTel
    yemifelgu yebhier genTayoch
    nachw.
    Professor getachew haile
    aTenkrew yasasebut ager
    wedadoch dar kumachuh
    kemecheneq betTq tglu weym
    behzbawi ameTu tesatefuna
    lehulum etiyopiya ekual
    yemtTeqm ager endtmeseret
    adergu new.
    Land bhier bcha sayhon lehulum
    ekual enqum new.
    Yalut yhn new, ende gena anbbut.
    Yhn maletachew ke woyanie
    besteqer mannm ayaskefam.
    Ke zih yeteleye hasab kalachuh
    agarun.
    Eniem ye ersachewn hasab degfie
    lehulachn ekul yemtTeqm andit
    etiyopiyan lememesret andnet feTeren woyanien endemss elalehu.

  18. gobez andad dedeboch yemiseTut asteyayet betam hala qeroch nachew eNih profesor tkkl nachew yedro yedro ybalal hulacnm eko lezari mannetachn yehonut yekedemt abatochachn mannet new ensu baynoru noro ethiopiya ende ager balqomech tewededem tetelam bezer eyandandachn ager noron buhon noro zarilay chgrachn lila lihon ychl neber man yawqal eyetenegagern yalenew sle ethiopiya yemtbal ager new yhci ager hzbocha yeyerasachewn tarik bemesrat behaymanotm yerasachew tarik bemesrat manNawm ager bealem lay endeager endeqomut ethiopiyam berasa tarik ende ager komalech mengst akumew tedadrewal yh sereat bezemenu teketayoch teqeblew agerachewn keTelat eyetebeku kezemen zemen sihidu sreatochu kezemenuga abrew yemayhidu kehonu sreatoch yfersalu ager ena hzb gn mefres alebet teblo ahun seleTenn yemnl yezer lhiqanocm honen weym ethiopiyanoch mechekacheq ena be ethiopiyawst yalefut abatoch atftewal blo zarilay komo lemenager moralum chlpotawm yalen aymesleNm lezawm yekelizer tebedlo slenore megenTel alebet bemalet ager lemekures kemaseb gara yezer mannetn mastebeq endemichal mawrat ena betaktik beseletene zemen ager bezer lemeqemat yemidereg enka slanta bcha new hulum zer tarik alew qanqa alew beteley degmo ityopiyawi yehonebet ager yakomebet meseretu ahun yebanda erzrazoch bezer mannet kefaflew lemezref zer lematfat kemetubet menged gar gnNunet yelewm slezih bemejemeriya beagerachn kezemen zemen yemishashalutn negeroch endelilaw ager eyashashaln mehid metfo bahl kalen kezemenuga mastekakel …enji yalefu mannetachnn atften zari eNa bcha yemnlew neger ysema yalefut ager siyakomu alawequbetm ahun gn eNa ageran afrsen ager akefaflen yeyerasachnn ager …enmesertalen yedekamoch astesaseb new negerum ende weyani tgri yefashisht plan yzo ager bewerera eyasefu mezref ager bezer masdat mekemat new yh degmo ahun seltnenal yemilu hayloch blt hnew kalefut abatochachew lemeshal yemiyadergut tret new gn abatochachew yeseferut yetegeNut ethiopiya yemtbal ager wst new slezih ethiopiyawinetn kemekebel lila chans alneberachewm ayasbutm neberem asbewbet bihon noro yezer lhikanoch zari dem balafasesu beager keld yelem

  19. u gays are really idiots, why you don’t wish a little good for the innocent people….why u don’t try to get rid off the dirty thinking from mind.

  20. ፕሮፌሰር እባክዎ በሰሜን በኩል የተጀመረውን ውጊያ ቦታ ይንገሩኝ ። ማን ነው የጀመረው ? የት ቦታላይ ነው ውጊያ እየተካሄደ ያለው ። ግንቦት ሰባት ጀምሮታል ብለው እንዳያስቁኝ ። የኢሳት ወሬ ነው ። ኮሽ ያለ ነገር እንኳ የለም ። እርስዎ እንኳ እንዲህ ከተታለሉ ገለባውማ ቃሊቲ ደርሰዋል ቢሉት ያምናል ። በቂ መረጃ በሌለዎት ጉዳይ ላይ መደምደሚያ መስጠት ስህተት እንደሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ።

  21. የቱ ፓራግራፍ ላይ ነው የድሮ ስርአት ስለማስመለስ የሚጠቁመው ? ? ? ፕሮፌሰር ጌታችሄው ኃይሌ is not my favorate scholar either.He ill-intentionally has ridiculed my hero ዐፄ ቴዎድሮስ on several occasion,but I have to forgive him because he has a lot of other positive contributions.የድሮ ስርአት ይመጣል ብሎ የሚጠብቅ ካለ ዘገምተኛ ጭንቅላት ያለው መሆን አለበት።እሱን ለመከራከር ጊዜየን አላጠፋም።ከአሁን በኋላም ከሰማይ እግዚአብሔር መርጦ አንተን እንድገዛ የመጣሁ ነኝ የሚለኝም ካለ እሱም ዘገምተኛ ጭንቅላት ያለው መሆን አለበት። Now having said that I would like my Oromo brothers to accept the fact that citizens paid with their lives to remove that monarch oroms,amaras,tigress alike.Are we dismissing the fact that Mengistu and Germame Niwaye who conducted the first coup detat against that monarch were amharas ? ? But they died to liberate us as citizens and not as a single tribe.I can list numerous heroes from Oromos and Tigres as well.Can we think out of the tribal box please please,please ? ? ? ጥቂት በጣት ከሚቆጠሩ ምርጦች በስተቀር ማነው ከድሮው ስረአት የተጠቀመው ? ? ? የግፉ መጠን በደቡቡ የአገራችን ክፍል በእጅጉ አስከፊ እንደነበረ የሚያከራክር አይደለም። When i think of that ስርአት I say to myself Mengistu Haile Mariam should have excited not only 62 of them ,but may be more 62 times 62.I do not want to think of it.

  22. YE diaspora Doctors ena Professors yejajew
    ideme achew sayhone amelekaketacew chimer neaw
    sewu Doctor weyim Professor yimil yemairg meteria
    simeleket ayenebewum bemulu yezorebachew lehizb
    neket yalachew kale Doctor awaki yelim yemilu
    ena retarded nachew . yensu medeberia Ethiomedia neaw
    lela manim aykebelachewum yhem seweye astesaseb hulu
    inde rasu yetetameme neaw .

  23. I am tempted to accept the theory that a Japanese scientist, a few years ago, said that Ethiopians are having the lowest IQ in Africa. Here is my reason: we are unable to agree on anything be it politics, social and some other even small things. We are selfish, evil and always suspecting.

    We all agree wuyane is our common enemy. So we came to a conclusion that Oromos and Amharas must united. We the majority Oromos accepted it. And I believe the majority Amharas also accepts it. We can’t defeat wuyane by being devided. This was being preached to oromos by Amharas for the last 25 years. Now the right time arrived and the oromos took the lead in fighting and accepted the one ethiopia concept.

    Now all of a sudden some old proffosors started sawing “engrdad” instead of encouraging the unity agenda. There are few extreems from both sides. They have to be ignored. Unity between these two big groups is the only way out. We got to grab this oportunity and defeat wuyane.

    These old controvecial porofosor must leave and shut up now. Had the king transfered the power to the crown prince before he was too old we wouldn’t have faced this havoc as a country. Old age can’t think clearly. The profosor is not exception.

  24. ” *
    * Gotta Oromo says:December 31, 2015 at 4:45 pm

    this is a confusion and nightmare; how could this guy try to turn down peoples revolution? is really thinking for Ethiopian people sustainability? nothing else his is a fault digger.
    [Reply
    ]Reply

    * Tinqishu says:December 31, 2015 at 7:58 pm

    GETACHEW Haile,
    You expirations date itself had expired before Yekatit 1965. So as your political gritts. Check into cheapest nursing home, worry about your final days. ”

    The two guys above are not Ethiopians, at least they do not know the Ethiopian “chewanet” and “respect for the old”. I wouldn’t be surprised if they are Eritreans or shabians.

    Professor Haile is a well respected senior citizen and only sid adeg persons like the two above, be they Ethiopians or eritreans, would have no respect for such a senior citizen.

    That said, we know about oromos who are angry about the professor because of his writings about the immigration of oromos to Ethiopia since the 16th century.

    Well, those Oromos should know that they have to accept historical facts whether they like them or not.

    But within an Ethiopian context Oromos or so-called Oromos, since most so-called oromos are either mixed or former Hadiyas, Kembatas, Gurages, Damos, etc , are citizens like anyone else and will enjoy rights and will have to respect laws.

    Important to those Oromos is to fight against tribalism and for a united Ethiopia. In post-TPLF Ethiopia the illegally dissolved historical provinces will be reintroduced and there will be no place for a fictional killil called oromia or any other killil.

    Based on that the future will be bright for Oromos just like for other tribes. And please dont use the term nationality to mean tribes. There is only one nationality in Ethiopia, and it is called Ethiopian.

    We know shabians hate and fear that, but we Ethiopians dont give a fk what shabians hate or fear, our struggle is not to please shabians.

    http://www.emapsworld.com/images/ethiopia-provinces-map.gif

  25. @king size,

    you sound to be a shabia, why i say that ?

    ” I am tempted to accept the theory that a Japanese scientist, a few years ago, said that Ethiopians are having the lowest IQ in Africa. Here is my reason: we are unable to agree on anything be it politics, social and some other even small things. We are selfish, evil and always suspecting.”

    Because you quoted a trash. Only a ferenji mental slave like shabians buys everything ferenjis say. To be honest only shabians have the lowest IQ on the planet, because they worship ferenjis like no other.

  26. ደደብ FROM ደደቢት could be a CIA agent.

    Dont you think the likes of Mengistu and Germame were CIA agents ?

    Can’t you see that the problem we have now was started by them ?

    You could as well be ihapa or shabia, and dont deny that the Haile Selassie government was the best we had compared to Woyane and Derg.

  27. Neftegna professors ?

    What an idiot you are !

    Neftegnas are the ones who created and defended Ethiopia. You must be a shabia to be against the great Neftegnas.

    ” Mekete says:December 31, 2015 at 10:07 pm

    You why I’m not visting the Ethiomedia website
    it’s b/s the page will always filled by the
    NEFTEGNA PORFESSORS AND DOCTORS AND ITS SO
    disgusting visting that website . This days around
    I become biased to read any articles by Professors
    and Doctors and most of them are more feudal than
    their fathers and retarded too. “

  28. Warning,
    a lot of SHABIANS here.

    Mostly they take oromo identity, and they address Ethiopians with tribal names. That how to identify them.

  29. Quote below is absolutely correct. We all should reject tribalism and religious extremism.
    We all should organize under the banner of Ethiopianism.
    In terms of numbers mixed Ethiopians and Ethiopian nationalists are by far the majority, also proven in the 1997 (2005 g.c.) elections.

    But we have to be extremely careful of foreign powers like Eritrea, Arabs and ferenjis like USA who will certainly work to derail the struggle.

    Among the steps we could take is to tell journalists and writers no longer to use TPLF’s tribalist language such as killil names and tribal names, instead to use the names of the illegally dissolved provinces and “Ethiopians”.

    ” አገር-ወዳዱን የሚያሰጋው አንዱ የኦሮሞዎች ጥያቄ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት የሆነው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማፊያ ቀምበር ተጠምዶ ሳለ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ኦሮሞች ብቻ የተጠቁ አስመስለው ሲናገሩ መሰማታቸው ነው። አገር-ወዳዱ የሚለው “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲጠቃ ሁላችንም በአንድ ድምፅ እንቃወም፤ የሚጠቃው ኢትዮጵያዊ እንጂ፥ ኦሮሞ፥ ቅማንት፥ አማራ፥ ጉሙዝ፥ . . .፥ እስላም፥ ክርስቲያን አይደለም” ነው።  አማራውንና ኦርቶዶክሱን የበለጠ የሚያጠቁት ለሀገሪቱ አንድነት ማገር ሆነው ስለገኟቸው ነው።

    ኢትዮጵያን በአስተዳደር ጊዜ በጎሳ፥ በሃይማኖት መከፋፈል የወያኔ ተንኮል ነው። በአስተዳደርና በፖለቲካ ጊዜ፥ ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው። ለጎሳና ለሃይማኖት ማሰብ  ክፋት የለበትም።ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ፥ መከልከል የለባቸውም፤ መብታቸው ነው። መብቱም ባህል ማዳበር ነው፤ ግን መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ሊገባ እንደማይገባው ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡም የሃይማኖቻቸውንና የጎሳቸውን ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ሊያደርጉት አይገባም። አገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው። ”

    Those who attacked the good professor for giving us advices like above must be the enemies of Ethiopia, and most likely SHABIANS !

  30. After reading the whole article i wonder why some of the people commented it so negatively. They must be the “Sid Adeg” shabians.
    The professor’s article is balanced, and i disagree with a lot of it, like his positive views about armed groups that come from Eritrea. I dont believe that we can expect anything good from Shabia controlled armed groups, still i have respect for the professor.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*