ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡
ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ ( ሰማያዊ ፓርቲ ) #Ethiopia #Blueparty @semayewiparty

ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡
ፓርቲው ‹‹ሕዝባዊ መንግስት መመስረትና የሐገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው›› በሚል ዛሬ ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ አካሉ ናቸው፡፡
ሰማያዊ በመግለጫው፣ ‹‹በሀገራችን የደረሰው ግፍና በደል የማስቆምና ህዝባዊ መንግስት የማቋቋም፣ የሀገርን ብሄራዊ ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው›› ብሏል፡፡ በመሆኑም ‹‹…ሁሉም ዜጎች አርዓያቸው የሆኑትን የቁርጥ ቀን ልጆች የመስዋዕትነት ጥሪ በመቀበል ቆርጠው እንዲነሱና የድርሻቸውን እንዲወጡ…›› ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ፋና ወጊና የነቁ ዜጎች የእሳት ራት እየሆኑ ነው ያለው ሰማያዊ፣ ‹‹አርዓያዎቻችንን እያስበላን ዝም ማለታችን አገዛዙ እድሜውን ለማራዘም›› ተጠቅሞበታል ሲል ገልጾዋል፡፡ መንግስት ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲ አባላትንና አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችንና ንቁ ዜጎችን በጅምላ እያሰረ መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል፡፡
በሌላ በኩል የሐገር ድንበርንና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ዜጎችን መንግስት ‹‹ሽፍቶች›› ሲል መጥራቱ ታሪካዊ የክህደት ምስክርነት በገዛ ዜጋ ላይ መስጠት ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አውግዟል፡፡ — በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር==
(ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዞ ቀርቧል)

play
ህዝባዊ ጥሪ ማድረጋችሁ መልካም ነዉ ሆኖም አሁን ህዝባዊ ትግል መጥራቱ ጉዳይ እና የተቃዉሞ ሰልፍ ፈቃድ መጠየቅ ማለት አንድ ናቸዉ ሁለቱም በመንግስት ተቀባይነት አይሰጣቸዉም ስለዚህ እንደ ፓርቲ ሌላ የመታገያ ስልት ለህዝቡ ማሳወቅ ይኖርበታል ለምሳሌ ስራ ማቆም በተለይ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዳይሄዱ በማድረግ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቶች ሰላም ባስን ስልክ የማይደወልበትን ቀን ጥቁር ኮፍያ በማድረግ ሰላማዊ ተቃዉሞ ለማድረግ ፓርቲዉ ቅስቀሳ ቢያደርግ በተጨማሪ ጎንደር ላይ ለምንድን ነዉ ሰማያዊ ፅ/ቤት የማይከፍተዉ
ዬኢትዮጵያ ህዝብ ጤላቶች ኢትዮጵያን ለመበታተን ቀንና ሌሊት በተለያየ መንገድ እየሰሩ ነው::ዋናው ሃገር ማፍረሽኣቸው ዘዴ ህዝብን ከህዝብ ማፈጀት እንደሆነ ግልጽ ነው::ስለዚህ ሃገራችን የሁላችን እነደሆነች ሁሉ በከፋፋዮች ወሬ ሳንደለል ሃገራችንን መጤብቅ የሁላችን ሃላፈነት ነው::
ጥቃቅን ልዩነታችንን ወደጎን ትተን የሃገራችን ነጽኣነት እንጤብቅ:ነቅተን እንታገል::
ሃገር ሲጤፍኣ ዝምታ አያዋጥኣም::
እትዮጵያ ከህዝቦቻ ጋር ለዘላለም ትኑር::
ማንኛውንም ሀገር አድን ተረካቢ ትውልድን አፍኖ እየገደለ እየዘረፈ ያለውን አሸባሪውን ወያኔ በጋራ ከአማራውና ከኦሮሞው ህዝብ ጋር አብረን መቆም ነገ በኔ ነውና ተሣትፎና እርዳታው ተጠናክሮ ይቀጥል።
ወያኔ ይወገዳል
የአባቶቻችንን አደራ በጥንቱ ባንዲራ!!!
@wind of change what about the athers ethiopian.you are thinking for ethiopia or ??????????.
There is always a “story behind the story”. I don’t know if I am becoming unresonably suspicious. If that is the case, I will take full responsibility for my action.
The press release above, reminded me of the Amharic saying, ” lam alegn besemay wotetuanim alayi”. To my understanding it is like puting the cart before the horse.
This is not the time for power struggle. Dr. Engineer Yilikal, please tell us the level of participation of your constituencies in the ferocious struggle with TPLF before talking about post Wuyane. I assumed you are from BAHIRDAR. If wrong i can be corrected. You shall explain more about the objctive and purpose of this press release. Thanks