ዲሞክራሲ በጠና ታሟል!!
ዲሞክራሲ በጠና ታሟል!! Written by ኤልያስ
የዲሞክራሲ ስላቅ በካርቱን!

ሰሞኑን በዲሞክራሲ፣ በነጻነት፣ በሰብዓዊ መብቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችና ገራገር ቁምነገሮችን ከጉግል ላይ ሳስስ ለፖለቲካ በፈገግታ ግብአት አገኘሁ፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለለውጥ ያህል በጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በካርቱንም ነው የምናወጋው፡፡
አብዛኞቹ ካርቱኖች ከእነመግለጫቸው በራሳቸው ጽሁፍ ማለት ናቸው፡፡ የተሟላ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ያውም ዘና እያደረጉ ነዋ። የተመቸኝም ለዚህ ይመስለኛል፡፡ እንደ ስላቅም እንደ ምጸትም ያደርጋቸዋል፤ካርቱኖቹ፡፡

ሰሞኑን በዲሞክራሲ፣ በነጻነት፣ በሰብዓዊ መብቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችና ገራገር ቁምነገሮችን ከጉግል ላይ ሳስስ ለፖለቲካ በፈገግታ ግብአት አገኘሁ፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለለውጥ ያህል በጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በካርቱንም ነው የምናወጋው፡፡
አብዛኞቹ ካርቱኖች ከእነመግለጫቸው በራሳቸው ጽሁፍ ማለት ናቸው፡፡ የተሟላ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ያውም ዘና እያደረጉ ነዋ። የተመቸኝም ለዚህ ይመስለኛል፡፡ እንደ ስላቅም እንደ ምጸትም ያደርጋቸዋል፤ካርቱኖቹ፡፡
ለምሳሌ አንደኛው ካርቱን በት/ቤት ክፍል ውስጥ አንዲት መምህር ህጻናትን ታስተምራለች። “ህጻናት ዛሬ የምናወራው ስለ ዲሞክራሲ ነው” ትላቸዋለች፡፡ ህጻናቱም “ለምን?” ሲሉ ይጠይቃሉ። መምህርቷ ምን ብን ብትል ጥሩ ነው? “ብያለሁ ብያለሁ!” አሁን እቺ እንዴት ነው ህጻናትን ስለ ዲሞክራሲ ማስተማር የምትችለው? (አምባገነን ናት!) በእውኑ ዓለምም ያው ነው፡፡ (በጦቢያም ማለቴ ነው!) ዲሞክራሲን በተግባር ያልተለማመደ እንዴት ከሥርዓቱ ጋር ሊጣጣም ይችላል? (ሚስት ከመደብደብ ኋላ ቀር አስተሳሰብ መች ወጣንና?) አስተማሪም እኮ ከተማሪዎቹ ጋር ያለው ግንኙነት የተመሰረተው በምክክርና በንግግር ሳይሆን በዱላና በቅጣት ነው፡፡ ምን ለማለት እንደፈለግሁ ሳይገባችሁ አይቀርም፡፡ ከዲሞክራሲ ጋር አንተዋወቅም፡፡ ደማችን ውስጥ አልገባም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በገዢውም ሆነ በተቃዋሚው ጎራ እንደ ልብ የተትረፈረፈ ቃል ቢኖር ዲሞክራሲ ነው፡፡ ክፋቱ ግን እንደ አንዳንድ ወሳኝ ጉዳዮቻችን በዲሞክራሲም ላይ አገራዊ መግባባት ላይ (consensus) የደረስን አይመስለኝም፡፡ ከምሬ እኮ ነው፣ልክ እንደ ኢኮኖሚው፣ ዲሞክራሲው በምን ያህል እንዳደገ ወይም እንዳሽቆለቆለ ጥናት ሰርቶ ይፋ የሚያደርግ የግልም በሉት የመንግስት ተቋም የለም፡፡ እናም ስለ ዲሞክራሲያችን የምናወራው በእውር ድንብራችን ነው፡፡ እናም የዲሞክራሲ ግሽበቱ ስንት ደረሰ? ፍላጎቱና አቅርቦቱ ተመጣጥኗል ወይ? ህዝቡ፣ መንግስትና ተቃዋሚዎች በየጊዜው ከዲሞክራሲ ባህል ጋር እየተቀራረቡና እየተዋደዱ ነው ወይስ እየተራራቁና ባዕድ እየሆኑ ነው? እኒህን ሁሉ የምናወራው በግምት ላይ ተመስርተን ነው፡፡
እውነት በጦቢያ ዲሞክራሲ አለ? የምር ነው ወይስ የይምሰል? መንግስት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን ያለው ቁርጠኝነት የቱን ያህል ነው? ተቃዋሚዎች ጨርሶ ቁርጠኝነት የለውም ይላሉ፡፡
እኛ ተራ ተርታ ነዋሪዎች ደግሞ ከሰሞኑ ቀውስ ተነስተን (ጥናት አይፈልግም ብዬ ነው!) ዲሞክራሲው አደጋ ላይ መሆኑን፣ ክፉኛ መታመሙን መገመት እንችላለን፡፡ (ለወትሮም በሽታ ይወደው ነበር!) መቼም ግጭት ባየለበት፣የሰው ህይወት ባለፈበት፣ የአካል ጉዳት በደረሰበት፣ንብረቶች በወደሙበት፣ አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባልተቻለበትና ቢያንስ ለሳምንታት የሰላምና የደህንነት ስጋት አረብቦ በቆየበት ሁኔታ— ዲሞክራሲው ጤነኛ ነው ማለት ዘበት ነው፡፡
እውነት በጦቢያ ዲሞክራሲ አለ? የምር ነው ወይስ የይምሰል? መንግስት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን ያለው ቁርጠኝነት የቱን ያህል ነው? ተቃዋሚዎች ጨርሶ ቁርጠኝነት የለውም ይላሉ፡፡
እኛ ተራ ተርታ ነዋሪዎች ደግሞ ከሰሞኑ ቀውስ ተነስተን (ጥናት አይፈልግም ብዬ ነው!) ዲሞክራሲው አደጋ ላይ መሆኑን፣ ክፉኛ መታመሙን መገመት እንችላለን፡፡ (ለወትሮም በሽታ ይወደው ነበር!) መቼም ግጭት ባየለበት፣የሰው ህይወት ባለፈበት፣ የአካል ጉዳት በደረሰበት፣ንብረቶች በወደሙበት፣ አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባልተቻለበትና ቢያንስ ለሳምንታት የሰላምና የደህንነት ስጋት አረብቦ በቆየበት ሁኔታ— ዲሞክራሲው ጤነኛ ነው ማለት ዘበት ነው፡፡
ዘወትር ህመም በማያጣው ዲሞክራሲያችን ተስፋ ያድርብን የነበረው የኦሮሚያው ችግር እንደ አጀማመሩ በሰላማዊ ተቃውሞ ብቻ ወደ ውይይትና መፍትሄ ቢገባ ኖሮ ነበር፡፡ የዲሞክራሲ ሥርዓቱ አሳዳጊ እንደ ሌለው ምስኪን ልጅ ችላ እንደተባለ ሌላው ማሳያ በዚሁ በፈረደበት የማስተር ፕላን ጉዳይ አምናም ተቃውሞና ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ህይወት ማለፉ ነው። ግና ከዓምናው ትምህርት በመውሰድ ቀወሱን ለመቀነስ አልቻልንም፡፡ አሁንስ በጠበጠን እኮ! /ጦሳችንን ይዞት ይሂድ!/ ይሄም የዲሞክራሲያችንን መታመም እንጂ ጤንነት አያሳይም፡፡
http://addisadmassnews.com/
http://addisadmassnews.com/
Ye etiyopiya hzb kezih dwy yetgrai woyanie melkam neger eyeTebeqe kehone, kebab enqulal ergb ende meTebeq new ale yeshabi radio band weqt. Mnm neger kewoyanie anTebq, medemsesun bcha new mafaTen yalebn.
ዲሞክራሢን በቀይ ሽብር ጭምብል ተሸፍኖ ይክው 25 አመት ሆነን አይደል ህዝቦች በማእከላዊ ይሠቃያሉ ይረሸናሉ ይህ በብሄርና በዲሞክራሢ ሥም እየነገደ የሚገኘው የበሠበሠ ሥርአትን በጋራ ሆነን ገንድሠን መጣል ግድ ይለናል።
wey dimokrasi mejemeriya ager ynuren ethiopiyanoch abatochachn demachewn afssew nesanetachnn ethiopiyawinetachnn asrekbewn zari bebanda hwehat tgi eko ager eyeteqeman mannetachnn eyatefun new slezih kedimokrasi yalefe ager ena neSanet yasfelgenal Mot lehwehat tgri ena ashkeroch lekefafayoch
ዲሞክራሲ ሞቶ ተቀብሯል አትይም ? ? ? ? What an insult ? ? ?
ትክክል ወንድሜ።መጀመሪያ አገር ይኑረን ክዚያ በኋላ ስለዲሞክራሲያ መጨንቅ።አሁን አገር የታለ እና ነው ? ? ? ዲሞክራሲ አሁን ለኛ የቅንጦት ጥያቄ ነው።”መጀመሪያ የመቀመጫየን”የዝንጀሮዋ ትያቄ ነው።
They have struggled to terrorise Ethiopia and rob our resources! Not for democracy. So NO DEMOCRACY at all in Ethiopia so far!!
@dedebu from dedebit you Said they rob our resources ?what they rob our oil,our gaz,our gold,our diamond.why we ethiopians lies too much.most ly the ORTHODOX.
Smh dedebu yalk, ewnetm deded neh. Awe woyanie zerfual habtachn (our resources), lemsalie werq, bret, meriet, derg bwrs yehzb yaregachew factories, bietoch, derg yegenebachew factories, hnTawech, derg yegezachew meqinawech, ye derg construction ministry mulu machinaries, yemengst ersha machinaries, ere snt teqoTro liyalq bewoyanie yetezerefew, yager habt den, eTan ena mucha sayqer bewoyanie tezerfual. Endihum beqTat, beqmiya, bezereñanet beyeteqañe sme gbr tezerfenal, negdun rasu woyanie tesemartobet yasr br eqa bemeto br eyesheTe yzerfenal, ere sntun yewoyanie mezrefiya slt zerzro liyalq. Endiya bachru tgrie tgrain lemalmat eyetesewan tezerfenal. dl le etiyopiya tagayoch., mot le tgrai woyanie
Democracy wasn’t in Ethiopia.
Democracy is when the will or wish of the majority is governing. Abzañaw hzb yefeqedew mengst astedadari sihon, yabzañaw hzb flagot hg sihon new. Hzbu mayfelgewn guday yemisera siweged new. Yh tnsh bihonm bahaleslasie yebarlama abalatn bememreT taytual, denber akelalen ke sudan gar be parlama adebadbo, mnm denberachn endayneka bemalet abzañaw dmT seTtual. Mnalbatm bekefil bihonm bederg yekebelie liqemenabrt mrcha tenTebarqual, hzbu yemifelgewn ymerT neber. Gn be woyanie gizie qalun degagmo bemeTrat kemadenqor besteqer mnm ye democracy fnch betegbar altayem, miTeqes andm neTebraq yelem . Yelielen democracy tamual malt trgum yelewm.
With out existance Demicracy became sick! Funny