የመብራት መቋረጥ የባቡር አገልግሎቱን እያስተጓጐለ ነው ተባለ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት በመብራት መቆራረጥ አገልግሎቱ እየተደናቀፈ ሲሆን ተጠቃሚዎች ላይም እንግልት እየፈጠረ ነው ተባለ፡፡ ባለፈው ሣምንት ቅዳሜና እሁድ ለረዥም ሰአታት አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበር የጠቀሱት ተገልጋዮች፤ ማክሰኞ ዕለትም ተመሳሳይ ችግር ማጋጠሙን ጠቁመዋል፡፡ መብራት ሲጠፋ ባቡሩ ለረዥም ሰዓት ቢቆምም ለምን እንደቆመ ገልፆ ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ ተጠቀሙ የሚል አካል እንደሌለ ተገልጋዮች ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በበኩሉ፤ የመብራት መቆራረጥ በአገልግሎቱ ላይ እንቅፋት እየሆነበት መምጣቱን ጠቁሞ ችግሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እያጠና እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ለብቻው ለባቡሩ የሃይል አቅርቦት መዘጋጀቱን ኮርፖሬሽኑ ጠቁሞ፤ የሃይል መቋረጡ እያጋጠመ ያለው ከምንጩ ነው ብሏል፡፡ ህብረተሰቡ በከፍተኛ መጠን የባቡር ተጠቃሚ እየሆነ በመጣበት ሰዓት በሃይል መቋረጥ አገልግሎት መስተጓጐሉ አግባብ አለመሆኑን የተናገሩት የኮርፖሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ፤ ችግሩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ መፍትሔ እስኪገኝ ህብረተሰቡ አገልግሎቱን በትዕግስት እንዲጠቀም ጠይቀዋል፡፡
ከበሠበሠ ሥርአት ምን ትጠብቃላችሁ?
የመብራት ችግር 10 አመት ሞልቶታል ይቀጥላል…..
እንዲው ምን አይነት ፖለቲካ ነው ያለን ጅቡቲ ለ6 ሠአታት በግዥ ከኛ በወሠደችው መብራት ኑሮዋን እየመራች ነው ለምን ለህዝቧ ክብር ሥላላትም ነው ይህ በኪሎዋት 0.50ዶላር የሚሸጠው ሀይል ምንም ያህል ጥቅም የማይሠጥ ወሀ ቅዳ ውሀ መልሥ ፖለቲካ ሥለመሆኑ በሀገር ውሥጥ ያለው በመብራት ጥገኛ የሆነ ኢንደሥትሪ ክፉኛ ኪሣራውሥጥ ባለበት የውሸት የፕሮፓጋንዳ ዜሮ ፕሮፊት የፖለቲካ ፍጆታ እየዋለ መሆኑን እንረዳለን።
Ke 120 amet befit be aTie mnilk gizie jemro ke jibuti adis abeba eske derg wdqet dres sisera yeneberen babur mamelalesha woyanie slTan siyz endiferars adrgo ke jibuti mekelie yebabur mesmer eyezerga new, menaña ye adis abeba qelal babur mesratun ynegrenal. Engdih tgrai woyanie mrT mrT yehonew hulu le tgrie ena letgrai slehone alemaw, yeneberewn aTfto, afrso wede migeneTlat tgrai mesmer eyezerega new. Yh newna woyanie mibal, andnet feTern endequsew, ydemses.