አባቶች በበሉት የልጆች ጥርስ አይለቅ / ቢንያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ

አባቶች በበሉት የልጆች ጥርስ አይለቅ  ቢንያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ

<<ለሚተኩቱ ሀገረ ይቅርላቸው>>

አምባገነኑ ቡድን ለራሱ ስልጣን ሸልሞ በኢትዮጵያ ላይ ቁብ ያለ ቡድን ነው። ትውልድ እንዲያቀረቅር እና አንገቱን ሰብሮ በለሆሳስ እንዲራመድ የኢትዮጵያዊውን መብት ገፍፎ በጫንቃው ላይ የጎጠኝነትን ቀንበር ጭኖበታል። የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ሀገር ወዳድ ልጆች የመስዋትነት ውሎ እና አዳራቸውን የሚያንቋሽሽ፣ፍፁም የአንድነት ስሜት የተለየውና ታሪካችንን የሚያናንቅ የክህደት ተግባር እየፈፀመም ይገኛል። ይህ ግፍ አድራጊ የወያኔ ቡድን ካልተገረሰሰ፤በእያንዳንዱ መስመር እና አቅጣጫ ሀገራችን ፈፅማ እስክትቆስል እና እስክትደማ ድረስ በበቀል ዱላው ትመታለች። ስለሆነም ምድራችንን ከዚህ ወረርሽኝ ማዳንና ማትረፍ የሚቻለው በጋራ ትግል ነው። መክሮ መታገል፣ በተሞክሮ ከአባቶች በመማር በአንደነት ዘብ መቆም።

የትግሉ ኦሜጋ እና ወሳኙም ምዕራፍ መተማመን፣መያያዝ እና መቀራረብ ብቻ ነው። ጠላታችን ስልጣን ከያዘበት ቀን አንስቶ በክልል፣በጎሳ፣በባንዲራ ለያይቶን በጥምረት እንዳልፋለመው መከፋፈልን በሁሉ ላይ አብቅሎ ለምዝበራው እንዲያመቸው አራርቆናል። እንዲህ አይነት ሥነ-ልቦና እና አምለካከት ይዘን ሀገር ልንገነባም፣ልናለማም፣ነፃ ልናወጣም ከቶ አንችልም፡፡ በፅሞና መግባባት፣ መተማመን እና መወያየት ካልፈጠርን፤ብሎም አንድ ሀገር እንዳለው ወገን በዳይ ተበዳዩን ይቅርታ ጠይቆ ወያኔ የረጨውን መርዝ ለማርከስ እና ለማምከን እርስ በእርስ ይቅርታን በመቀባበል ጎሳችንን ለመገንባት ሳይሆን ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሆነው ጥንታዊት ባንዲራችን በሁላችንም አደባባይ ላይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ክንዳችንን የምናስተባብርበት ጊዜው አሁን ነው። ይህ ካልሆነ ግን በደለኞች ነን። ይህም እያንዳንዱ ዜጋ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመው ትልቅ በደል ነው።ያለመቀራረብ እና ያለመመካከር በሽታ።

የኢትዮጵያ ግፋዊ አገዛዝ ኢትዮጵያውያንን በቋንቋና በክልል ከፋፍሏል። በዚህ የከፋፍለህ ግዛ ግፋዊ ሥትራቴጂውም ህዝቡን በተጨባጭ ተቆጣጥሮታል። በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንም መካከል ሰርጎ የመግባት ሥልቱን ቀጥሎበታል።በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ አንድ ግለሰብ በተለያየ የብዕር ስም እና በበርካታ የማስመሰያ የፌስ ቡክ አካውንቶች ኦሮሞውን ከትግራይ ተወላጅ አማራውንም እንዲሁ ከሌላው ብሔር እርስ በእርስ በማጠላላት ደረጃ በተለይም በሀይማኖት ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ መናቆር እንዲፈጠርና የኢትዮጵያን አንድነት በመሸርሽር፤ተቃዋሚ ፓርቲዋችንም እርስ በእርስ ተቃቅረው ጠንካራ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ ቁጥራቸውን ለማመናመን እና ለማዳከም የወያኔ ጆሮ-ጠቢዎችና ደጋፊዎች ኢትዮጵያውያንን ሥልታዊ በሆነ መንገድ ከፋፍለዋቸዋል። እንዲህ ተቋስሎ የተከፋፈለው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የአገር ቤቱ አገዛዝ ውጤት እና ሥራ ነው። ክፍፍሉ ማኅበረሰቡን ለሌሎች በርካታ ችግሮች ተጋላጭም አድርጎታል። እየተከሰቱ ባሉ ማኅበራዊ ችግሮች ለምሳሌ ትምህርት ማቋረጥ፣ ሥራ አጥነት፣ እንደ እፅና ወንጀል፣ እንዲሁም አስከፊ የሆነ ተስፋ መቁረጥ እና የሀገር ፍቅር መቀዝቀዝ እንዲንሰራፋ ወያኔ በውስጥም ሆነ በዲያስፖራው መሀከል በረጫቸው መርዝ ተሸካሚ አስመሳይ ገፀባህሪያቶቹን ለብሰው በተሰለፉ ደጋፊዎቹ በጥልቀት ተሰማርቷል።

የዳያስፖራው ፖለቲካዊ ሚና በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ወያኔ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ፣እንዲሁም በአረብ ሀገራት ወ ዘ ተ . . . የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦችን ቆራቆስ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። የስራ በር እያመቻቸ፣የሀሰት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በማሰልጠን፣ተማሪዎች፣ ጎብኚዎች በሚል ስምና እንዲሁም ግለሰባዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችንና የማኅበረሰቡን መሪዎች በተመለከተ መረጃ ለማቀበል የሚያገለግሉትን ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች መካከል በመመልመል ጭምር ደጋፊዎቹን በሁሉ አቅጣጫ ሰግስጎ ኢትዮጵያዊውን እያባላው ይገኛል። ይህ አካሔድ ግን እውነተኛ የህዝባችን ባህሪ አይደለምና እያደር ሁሉም ነቅቶበታል እየነቃበትም ነው።

በአለምም ዙርያ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ የሚታወቀው ትልቁ አስደማሚው ሀቅ አንድነታችን ብቻ ነው። ኦሮሞው ከትግራይ መዋለዱ፣ አማራው ከአፋር ዘር ማፍራቱ፣ ሰሜኑ ሲጠቃ ደቡቡ ዘብ መቆሙ፣ ሀረሪው ከጉራጌው ተጋብቶ ዘር ማብዛቱ፤ይህ ነው ኢትዩጵያዊነቱ።

የነበረው ጥምረት እና አንድነት በወያኔ ሴራ ተንዶ ምድራችን እና ትውልዳችን ባለ ብዙ ጥላቻ ባለቤት እየተደረገ ነው። የባንዲራ ብዛት በአንዲት ሀገር ላይ ያለቅጥ ተውለበለበልን፣በየእለቱ በረሀብ እና በእርዛት የሚያልቀው ወገን በየጊዜው ቁጥሩ ሲያሻቅብ ፣ ገበሬው መሬቱ እየተነጠቀ ለባዕድ ሲቸር፣ አዛውንቶች ሲጣሉ፣ ሴቶች ሲደፈሩ፣ህፃናት በጨቅላነታቸው ሲቀጩ፣ አንዱ ብሔር ብቻ በተለያዩ የግልና መንግስታዊ በሆኑ ተቋማት ላይ ሲፈናጠጥ፣መገለሉና አድሎው ነግሶ የተማረው እንዳልተማረ መንገድ ዳር ወድቆ ያልተማረው ፊደል ሳያውቅ የፕሮፌሰርነት ሹመቱን ሲጭን ወ ዘ ተ. . . የሆኑ ክፋቶች ሲከወኑ ፤ ከዚህ በላይ አገር መቀማት ከወዴት አለ? ይህ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ የዘረጋው የበቀል ዱላ ነው።

በተለያየን እና መራራቃችን በየወቅቱ በጨማረ ቁጥር በሰምበራችን ላይ ወያኔ የአርጩሜ ማህተም ጀርባችን ላይ እየመታ እንዲገዘግዘን እየተስማማንም ነው። ከሁሉም በላይ እና አሳዛኙ ድርጊት በእቅፋችን ውስጥ ያሉ ህፃናት እና ቀጣዩ ትውልድ እኛ እያለፍንበት ባለው ጭቆና እንዲያልፉ፤በመለያየታችን ጠንቅ ምክንያት ሁኔታዎችን እያመቻቸን እንደሆነ በጽሞና መገንዘብ ያስፈልገናል። ኃላፊነቱም የአሁን ጊዜ ነዋሪዎቹ የእኛ ነው፡፡

አባቶች በበሉት ፍሬ የልጆች ጥርስ ማለቅ የለበትም። ልጆች ባልበሉት በማያውቁት ዳፋ ያልኖሩበትን ዘመን እዳ ቀፍቃፊ በመሆን በአለም ሀገራት የታሪክ ማህደር ከተመዘገበችውና ከምትታወቀው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሌላ ፀጉረ ልውጥ ትውልድ በምድራችን ሳይበቅል ስለ ተከታዩ እና ሀገር ተረካቢው ትውልድ እንቀባበል፣እንዋሀድ፣እንስማማ እንማከር።

ነብር በቆዳው ቢዥጎርረጎር በውጫዊነቱ እንጂ ፤በውስጡ ግን አንድ ነው። ይህንን ነው ከኢትዮጵያ ጋር መፅሐፉ አነፃፅሮ ያስቀመጠው። ኢትዮጵያም የብዙ ጎሳ የብዙ ቋንቋ የደጋግ ቤተሰብ ክምችት ብትሆንም ሁሉን አጋብታ አዋልዳለችና ለመገንጠልም፣ለመለየትም ፣ለመክፈልም እጅግ አዳጋች ነው። ዥንጉርጉርነታችንም በውስጣችን ተዳፍኖ የተቀመጠውን አንድነት ሊደብቀው ከቶውንም አይችልም። ብዙዎች ስንሆን አንድ ነን።እንደዚያ ተሰርተናልና ሊገነጥሉን ሲያስቡ የሚያመን ህዝቦች ሆነናል። ስለ አፍሪቃ አንድነት የምታወራ አንዲት ኢትዮጵያ ትላንት በመጣ ጠላት ልትቆረስ እና ልትመዘበር ታሪኳ ተረት ተረት ሊሆን ከቶውንም የተገባ አይደለም።

ከባእዳን ወራሪዎች ጋር ለዳር ድንበሯ የተዋደቀ ህዝብ የነበራት ኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች ያሉ ነዋሪዎች በመተማመን፣ በመቀራረብ ታግለው የጭቆና ሥርዓቶችን መገርሰስ ከቻሉ ፤ ዛሬም እንደ ጥንቱ በአንድነት ታግለን ከወያኔ ምድራችንን ነፃ ለማውጣት የማንችልበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም፡፡ የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ ራሱን የሰየመው ጎጠኛ ቡድን በትግራይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እና በተቀረው ዜጋ መሀከል ቁርሾን ያዘለ የበቀል ጊዜን ብቻ በሚጠብቅ መልኩ የትግራይ ወንድሞቻች እና እህቶቻች ውስጥ የነበረውን የኢትዩጵያዊነት ስሜት አላሽቆት የክልል ፍቅር የጎሳ እና የመደብ አፍቅሮት ውስጥ ነክሮአቸዋል። ይህ በትውልድ ላይ የተሴረ የባቢሎን ድብልቅልቅ ዘመን እና በሌላውም በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ የፈፀማቸው በደሎች ሰምበር ሁልጊዜም የሚያመን ቁስል ነው፡፡ታግለነው ግን እንፈወሳለን ። የዳነ እና ከእዳ ነፃ የሆነ ምድር ለልጆቻችን እናስረክባለን።

ስናብር የምናስረው ጠላት አለ። ከዚያም ለታሪክ ፀሀፍት አሳልፈን እንሰጠዋለን።ወያኔ አስፀያፊ ታሪክ ሆኖ ይቀራል። በቅድሚያ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ድርሻ ሊሆን የሚገባው የተገረፍንበት የወያኔ ጅራፍ ባሰመረልን ሰንበሮቻችን እና ቁስላችን ላይ መወያየት፣ ከችግሮቹም እንዴት መፍትሔ እንደምናገኝ ነፃነታችንን እንዴት እንደምንጎናፀፍ ከተሞክሯችን ዘዴ መዘየድ።ይህ ‹‹ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ›› ሊሆን ይገባል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከሁሉም አስቀድሞ በራሱ ወርቃማ ፈር ቀዳጅ የለውጥ ሃዋርያነት ብሎም የታሪክ ፈርጥነት ሊያምን ይገባዋል፡፡ በትግሉ መደምደሚያ ላይ ከዚህ ቀድሞ እንደሆነው ሁሉ የለውጥ አልፋና ኦሜጋ ሕዝብ እንጂ ጥቂት የፊት ተቀማጭ ፖለቲከኞች ሊሆኑ አይችሉም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቃት ያለው ጀግና ህዝብ ነው።በተደጋጋሚ ወራሪዎችን ተፋልሞ አስደማሚ ታሪክ አስመዝግቧል። ሊገዙት ካሰፈሰፉት ጋር ሁሉ ግብግብ ገጥሞ አሳፍሯቸው ያውቃል፡፡ ከዚህ ሁሉ ከተፈፀመበት የጭቆና፣የመገነጣጠል፣ የአፈና ዶፍ እና ዝርፊያ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማቁን ጥሎ ትቢያውን አራግፎ እንደሚነሳ ለአፍታም እንኳን ማንም አይጠርጥር።

ከተስፋ መቁረጥ ጋር የምንፋታበት ጊዜ ላይ ነን። ጥቂቶች ለመታገል ሲነሱ ወኔያችው ሞልቶ እንዲትረፈረፍ የምንደግፍ እንጂ ተስፋ ቆርጠው እንዲቀመጡ የምንመካከርበት ጊዜ አባጅቷል።የኦሮሞ ወንድሞቻችን ጠላት አማራው አይደለም ከትግራይ ተወላጅ ጋር ደቡቡም ሆነ ጉራጌው አልያም ሌላው ብሔር ጠላትነት የለውም። ለሁላችንም ከወያኔ በቀር ጠላት የለንም። ሁላችንም ተያይዘን ምድራችንን የሚሸረሽረውን አሳች በመፋለም ለልጆቻችን ብሔራችንን ሳይሆን አንዲት ኢትዮጵያን እናስረክብ። እኛ ችግሮቻችን ፈትተን ለነፃነት ትግል ስንነሳ የሚቦለቦለው የችጋርና የጭቆና የመለያየት እሳተ ገሞራ ይቀዘቅዛል።በብርቱ አንድነታችን የነፃነት ትግል ማድረግ ስንችል ደግሞ ንዳዱ ከእሳትነት ወደ ክስለት ከዚያም አልፎ የጠላታችን እሳት የአመድ ቁልል ይሆናል። የዛን ጊዜ የትውልድ ደማቅ የፀደይ ቀናት የሀገር ተረካቢ ውብ ዘመናት ተግተልትለው በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይመጣሉ፣ይዘከራሉ፣ይከበራሉ። የጭቆና ሰንበሮቻችን ሁሉ ፈፅመው ይሽራሉ፣ ይፈወሳሉ፣ይከስማሉ፡፡እንግዲህ ልጆች ባልበሉት ፍሬ ጥርሳቸው እንዳያልቅ ለተተኪው ትውልድ በእኛው ዘምን ታግለን አንዲት ኢትዮጵያን እናስተላልፍላቸው። የዚያን ጊዜ እስካሁን ያልቀረፅነው እና ከቅርሶቻችንን ሁሉ የላቀውን ታላቅ ሀውልት በአንድነት በምድራችን ላይ እናቆማለን። ይህ ነው የውስጣችን ማህተም። የነፃነት፣ የእኩልነትና የወንድማማችነታችን ሀውልት በሁላችን ዘንድ ለመታሰቢያነት በልባችን የሚቆመው።

ኢትዮጵያዊነት ያብባል!!!

እናቸንፋለን!!!

http://ethfreedomfighter.blogspot.no

mailto:[email protected]

12 Comments on “አባቶች በበሉት የልጆች ጥርስ አይለቅ / ቢንያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ”

  1. ቢኒያም

    ጥሩ ሃሳብ ነው። በአማሪኛ ቋንቋ ተጽፈው ካነበብኳቸው ጽሁፎች ሁሉ የተለየ ነው። በምእራባዊያን ሃገሮች እየኖሩ አንድነት እና እኩልነት ምን ማለት እንደሆነ ያልገባቸው ‘ፕሮፈሰሮች’ ያንተን ጽሁፍ አንብበው ቢረዱት እንዴት ጥሩ ነበር? አንተም በኢትዮጵያ ውስጥ ባንድራ መብዛቱ ያሰጋህ ትመስላለህ። አትስጋ! አሜርካ እኮ 50 የስቴት ባንድራዎች እና አንድ የፌድራል ባንድራ አላት።

  2. Gizie yeseTachew (elites) yagerachn chgr feTrewal, mewcha mefthiewn demo ahunm belegiziewech endifeTru weqtu eyeTeyeqe new. Ye etiyopiya bhieroch ers bers Tornet geTmew yetelalqubet gizie yelem. Yh sidereg yenore new yemilun zegemt-angolu sbhat nega ena deqemesmurochu ene adisu legase, onegoch nachew. Awe bewoyanie, oneg, ohdd amaran bemechefchef ena bemafenaqel balefut 30 ametoch yezer fjt tefeTmual. Ke 30 amet befit endih aynet neger tayto, tesemto, tedergo ayawqm.Yetgrai woyanie bemelawa etiyopiya lay lalefut arba ametoch quami Tornet keftual. Gna lemeqeTlem gizie tornetun lemasqeTel tezegajtual. Amarawn, oromown, anuakun, somaliewn, sidamawn, afarun chefchfual. Kerasu ager ketgrai besteqer hulunm bhier, bhiere seboch gfna chfchefa woyanie feTmobachewal. Bemehonum ende eskezariew andnetachn aTenakeren keyebhieru, keye mahbere sebu, keye budnu ena keye glesebu bandnet adisuan etiyopiya megenbat yemnsha teTerarten gizie sanabakn tolo befTnet yegara yewedefit mengstachn amesrart, aweqaqer, astedader yegara sened azegajten, tesmamten, teferarmen, woyanien maTqiya yetgl slt nedfen, awten, wede tegbarawi woyanie yemedemses tegadlo engba. Ageru yeña new, srawm yeña new, belu beyalnbet and blen enjemr ahun, eyegezefe yyayazal. Dl le neTnet hailoch, mot letgrai woyanie.

  3. አመሰግናለሁTe’ara… ስለ ስቴቶቹ ባንዲራዎች ያልከው ትክክል ነው ግን ዋናቸውን ከፍ አድርገውና አስቀድመው ነው። ወደ እኛ ተመልሰን ያየን እንደሆን ግን ለየት ብሏል ። ከአሜሪካ ጋር ማነፃፀር ቀላል አልሆነልኝም። ከሀገር ይልቅ ብሔር ከፍ ከፍ ብሎ የሀገራችንን ባንዲራ አንዳንዶች ካቃጠሉት እና መያዝ ካሳፈራቸው ኢትዮጵያችን ከትውልዷ ልብ ተነቅራ ተተፍታለች ማለት ነው። ይህ ከስጋት በላይ ሆኖብኛል ። አንተ ግን ፅና!!!

  4. ato biniam sititay endetemare sewu mesilehi newu tsihufuni lemaqirebi yemokerikihawu negeri gin alememarihin sireda asteyayeti lemesiteti tegedijiyalehu.ante ke mani wegen endehonikina mina ayineti tebabi astesasebi endaleki lemeredati qelali newu.mikiniyatum be ante ayneti astesasebi hageritun lememirat atse Tewodros,Miniliki ,H/selasie ena dergi mokirewu neberu gin alitesakalachewum .le berikata ametatim hagerachin ethiopia be ersi bersi torineti simuwaa yitawoqali berehabim aliqewal silezihi endeti newu yaanin besositi mengisitati temokiro yaqatewuni le ethiopia hizibi yemitimegnewu ? negeri gini weyane bametawu siriati 1.ersi bersi torineti yelem,2.sciencena technology eyadege newu,yesira edilim eyetfetere newu siratinet be america europa yale newu,yedemokirasina melikami astedaderi chigiroch be hideti yemifetu bemehonachewu newu ye ethiopia hizibi ye anten yemayisemawu ke chigirochi yetemare hizibi bemehonu newu be face book ena beteleyayu midia lay silemayitsifi yaligebawu mesiloki atishewedi antena betesebochi betedeladele nuro lay honachihu egnani lemasicheresim atimokirewu timihiriti batimari enkuwan yesewu hageri nurona chigiru bizu alastemarehim ende? anteni yesewu hageri nuro silecheneqehina meheja yataki bitihonim emiye ethiopia lay wenjel sileserahi hageri atehi tinkeratetalehi ezihi ko 80,000000 hizibi eyechefere yadiral wuchi yalu diasporawochim egi setewu bekibiri gebitewu eyeseru nachewu ya newu le ethiopia hizibi wegeni yemibalewu hizibu sayimoti lemetageli lemesirati wede hageri beti yemetawu ene kadire aydelehum yemastrsi degiree bemeyazi betinishi demewozi yemisera sewu negni negeri gini hageri sitadigi hizibu siteqem enemi eteqemalehu biye newu ende ante lerase hodi bicha basibi noro ebetebiti neberi le ethiopia hizibi ke mechewum gize belayi yeweyane siriati temechitotali antenina meselochini yemisema yelem.betorineti metalehu bile bitasibi hagerachin “Neaukiler bonbi chemiro yetateqe befiqiri le emiye hiwetuni lemesewati yetezegaje ke 300000 belayi yehibi liji aleni beqa abeqahu yaleki tesfa 1.balehibeti tigegna mehoni 2.eji setehi bekibiri esirihini meceresi 3.eza yalu wudi yediaspora lijochin amalaji melaki newu alebeleziya teseqilehi memoti newu yami bihoni andi ethiopiawi teseqilo mote sibali ye egnani imagi yabelashali gini yihuni le ante biye newu.

  5. @Biniam endet yareghal ante ye woyane hod ader cadre woyem eraseh Tigre Woyane.

    Bekedemia wede ante yechinket aseteyayet kemegebate befit ante lehodeh be hodeh becha yemetaseb yehelina deha selehonk tshafiwun lemetechet ayedelem ewuketu moralum yelehem .

    Yemigermegn eko tsehafiwu ketenagerew neger lay wushet neger linorew kerto andachim gedefet yelebetem. Enam bertalen hagerachin be woyane Tigre eyetefach selehone antena meselochih gulbetachihun ena ewiketachihun hageren ke woyane Tigre tefat lemetadeg hizbachinen ye mankat ena erasun ena hagerun ke Woyane Tigre netsa endyawota besefiwu mekeskes asfelaginetun lasemrebet ewodalehu.

    Yeh kelay tsuhufun bemasereja yetekawome sayehon tsehafiwun lemaseferarat yemokerew sewuyew mehayem selehone lesu woyane malet bedehaw ye Ethiopia hizb sem ke World-bank & IMF betebederew birr condominium bet serto selesetewu ena ye deha lej eyasaredu yegele tekemun masaded selehone ya felegew Un bil ayedenkem. Yhen be hizb ank etef tebelo yetetefa ye zerafi buden man ke mengistenet yekotrewal yawum degemo kene Minilik Haileselasie ena Derg ga liwodader yekerena be Ethiopiawinet sewu menesatu legna wurdet new.

    Aye Gura woyane Tigre be melas wushet menzat ena zerfo be lebnet mekber ende seletanie yekotere agezaz new kumnegeru eyandandu woyanena degafiwu mechereshas Enesu beserut beye berhaw yale eserbet sihon sewum yegedelu degmo yejacheeun yagegnalu besemachew ena be betesebochachew yetazut nebret gin yedehawun Ethiopiawi netkewu ena zerfew selehone be hizb yeworesal.

  6. 300000 wotader leziawum nuclear yetatek selalen yetetke tegel endatmokerut yelenal endeza waotaderoch yegnaw wondemoch mehonachewun gin mesemate yamewal. Ye Egypt mubarek be hizb tekawomo siwoged wotaderu talka algebam yawum mubarek ke Tigre Woyane ga siwodader melaak (angle) new gin atefelegim worede. Tigre Woyane be plastic sandal chama ena kumta suri meto siltan ketekotatere behwala enen mankat constitution woyem hege-mengist mankat selehone wotader hig-mengstun masetebek alebet yelenal. Woy neket ena ebrit.

    Yehe ye woyane mengist mewoged lemen endemigebaw meknyatochun bachiru asekemetalehu.

    1.woyane erasu be misebkew ye afe demokrasi politica enkwan anasa (minority)buden selehone be geza fekadu siltanun melkekun alebet.

    2.ye miketelew policy hager yemyatefana ye zegochin mebet yemigef new. Ex- arso aderun be meret larashu be Derg tagegnewun ye meret balebetnet mebet meret ye mengist habte newu belo gefo arso aderun tewoldo kadegebetena endihum derg besefera ke akwakwamew meret lay eysfenakefle kene betesebu yetem beteno meretun
    Le wuchi hager balehabt berekash ena be wodeke waga yeshetal.

    3.ye mengist nebret yeneberu ye work maiden ena leyu leyu fabricawochen sheto be genzebu Tigraylay adadis factory yekefetal.

    4.meleyo lebashun ye kedem own ye derg serawit neh belo beteno yahunun degemo be selam asekebari sem dollar mesebsebia adergot beye berhaw yedeha lij be maymeleketew yasecheresewal

    5.ye hagerachin denber kedemom betekekel yrtekelel ayedelem bemil Enesu ye zare 20 amet metetew tarikna manenetachinen eyatefut mererachinen Le Sudan yesetalu gena Le somalie yesetalu egna hagerachinen eskaltebeken deres.

    6.hagerachinen be gosa ena be kwànkwa kefaflew ena kilel meseretew sewu be hageru ende kedemow yetem hedo serto endaybela aderrgut.

    7.ye e wushet adregen eyalu 15 million erabtegna ena 70 million belay be ken ande gize meblat yetesanew hizb adehytew ena awardew eyegezu Enesu ke 5 million yemaybeltu tigrewoch selalefelachew becha adgenal eyalu yesalekubenal. ……..etc

  7. Bniyam gzawn lemetechet smu biniam yemil yewoyanie tultula tgrie frie yelesh zbrqrq tuhuf bTie chenequaqurual. Tuhufu ende mimesekrew master degree sayhon, kezqtena dereja tmhrt biet ketmhrt jemari temari yanese chlota yeyaze gleseb new. Mnm saymaru master, professor eyale woyanie yameTabnn chgr masweged andu yetglachn akal new. Yarat, 4 mengstat sm zerzro, benezih sost mengstat yalsera sendeq alama ( bendiera) new ylenal., yh minagerewn ende mayaqew yasayal, yhchn monechachro, sra sleserahu shumet ena shlmat yseTeñ lemalet new. Ketiewdros eske derg wede 180 amet yeqoye bandiera endiet alseram ylewal, zent alem yemiqoy neger ende liele algebtotm. Yh ye zegemte-angolu sbhat nega deqemezmur hafretyelesh tgrie siwash , ” yers bers Tornet qerto, ager selam hunual, technology tesfaftual, sra moltual, hzbu besta ychefral”, blo yqebaTral. Awe woyanie beqnat ena mqeñnet Tere-amara hasab yzo, tgrie bcha kalgeza, etiyopiyan tgrie be belaynet kalyaze, engeneTelalen, enasgeneTlalen blo enedetenesa tesaktoletal. Kbur president Mengstu hailemariam endalew, amara tgrien alchequno, andem amara tgrai teshumo ayaqm, andm amara tnsh suq enkua tgrai wsT nurot ayawqm. Kenakatiew amara wede tgrai mehied enkua aysham. Dro woyanie be chaka ligeneTelna liyasgeneTl ager lemeTebeq yetesemaru wetader wegenochn eyefeje, ketema eyeworer, dldy eyaferes selam neston endenore ena zarie demo ketema gebto slTan yzo bemela etiyopiya quami Tornet awjo bagazi Tor amarawn, oromown, sidamawn, somaliewn, anuakun, afarun eyegedele selam neston ygeñal. Gn yh bezu meto shwechn megdel, millonochn mafenaqel, maser, medebdeb lewoyanie ena tultulawochu yetgrie jegnnet masaya slehone bebzu meto milions bir dgs eyedegesu asresh mchew blew bedesta endemichefru eyenegeren new new tultula woyanie. MrT mrTun, hulun letgrie bemil memeriya woyanie yetgriewochn yebelaynet slaregageTe sra bsh new ylenal tultulaw. Eñama kesera eyetebarern new, ke 40 belay mrT amara professors, doctors ke addis ababa university tebarewal. Be derg ye construction ministry yeneberew, ena ye transport tequamn bemafres woyanie mekelie mesfn engineering ena sur construction maquaquamun new tultula technology tesfaftual yemilen. 15 million hzb berhab eyaleq new woyanie hlina bis bedesta eyecheferu endalu yenegeren, yascheferachew hzbu berhab siyalq tgriew bcha ageritun yyzatal kemil esabie meseleñ. Zm blachu bngelachuh mutu, atchuhu, btchegerum alem new zendro eyalachuh ke dar qumachuh ajebun eyalen new tultulaw. Melsachn dl le Tere-woyanie tagayoch, mot le tgrai woyanie. Ebi ashaferen new.

  8. Biniyam:- Eyetah(milketah) dink new… esu lay betedla eyenork hememachen yegebah ; ye Ethiopiyawinet demeh yalkezekeze ; “Lemen” beleh yemeteteyik…. Bizu beleh bewodedku- gen kalatoch embi alugn! Ante ena meselocheh lezich ager tasfeleguatalachuh. Beirehen yibarkew. Ketelebet.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*