በአዋሳ እና በሻሸመኔ በእኩለ ቀን በአማራ ዴሞክራሲዊ ሃይል( አዴሃን) የትግል ጥሪ በያዙ በራሪ ወረቀቶች እና ፖስተሮች ተጥለቀለቀች::
የአዴሃን ዋነኛ አላማ የሚያስረዳና ለትግል የሚቀሰቅስ ፁሁፎች በአዋሳ በሰፈረ ሰላም: ገብሬል: ዋርካ :ፒያሳ: አላሙራ: አቶቴ ሞቢል አረብ ሰፈረ እና በማስታወቂያ ቦርዶች በሻሸመኔ ሰማኒያ አንድ ሰፈር አሮጌ መነሃሪያ አዲሱ መነሃሪያ ሞቢል ሰፈር በበቂ ሁኔታ ተሰራጭተዋል::
የህወሃት መንግስት አጥብቂኝ ዉስጥ በመዉደቁ ህዝባዊ አንድነት አጠናክረን በአጭር ጊዜ ልናስወግደዉ ይገባል:: በተጨማሪም ንቅናቅዉን በመቀላቀል እና በመደገፍ ፀረ ወያኔ ትግሉን በማፋጠን ነፃነታችን እንጎናፀፍ ሲል ጥሪ አቅርቧል:: ንቅናቄዉ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ
መሆኑን አዉስቷል::
