‘አማራ ነን‘ የወልቃይት ሕዝብ ያልተመለሰ ጥያቄ – የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ እንደሚከተለው ቀርቧል።
የወልቃይት ማህበረሰብ ከአዲስአበባ በ977 ኪሎሜትር ላይ በትግራይ ክልል ስር በሁመራ ዞን አድረመጭ ወረዳ የሚገኝ ነው። 
በ11ሺ 149 ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ ሰፈረውና 413ሺ564 ሕዝብ እንዳለው የሚነገርለት የወልቃይት ማህበረሰብ ባለፉት 24 ዓመታት የአማራ ብሄር ነን በሚል በአማራ ክልል ለመካለል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲቀርብ ቢቆይም ጥያቄው በትግራይ ክልል በአዎንታ መልኩ ባለመታየቱ ለእስር፣ ለሞትና ለስደት መዳረጉን ከሕዝቡ የተወከሉ የኮምቴ አባላት ያስረዳሉ። ባለፉት 24 ኣመታት አማራ ነን የሚል የብሄርተኝነት ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ 116 ያህል ሰዎች ታስረው የገቡበት እንዳልታወቀ የኮምቴ አባላቱ በስም ዝርዝር አሳውቀዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ንብረታቸው በጠራራ ጸሀይ የተነጠቁ ሰዎችንም ዝርዝር እንዲሁ በማስፈር አቤቱታቸውን ለፌዴሬሽን ም/ቤት እና ለሰብዓዊ መብት ኮምሽን ሰሞኑን በጹሑፍ አሳውቀዋል።
የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ እንደሚከተለው ቀርቧል።
……………
የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ መነሻ፣
በመሰረቱ የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አሁን የተነሳ ጥያቄ ሳይሆን ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የተነሳና በሕገ-መንግስቱ የሰፈሩትን ሃሳቦች ታይተው ምላሽ ያልተሰጠው በየጊዜው እየተንከባለለ የመጣ ነው። ጥያቄው እንደ ጥያቄ ማንሳት በሕግ እንደሚያስቀጣ ሕገመንግስታዊ መብት ነው ብሎ እንደመብት ተደርጎ ባለመወሰዱ የተነሳ ሲንከባለል የቆየ ጥያቄ እንጂ አዲስ ጥያቄ አይደለም።
የወልቃይት የአማራ ብሔተኝነት ጥያቄ እንደ ጥያቄ ሲነሳ ዋናው መነሻው ሕገ-መንግስቱን መሠረት ያደረገ ነው። በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39 ተራ ቁጥር 2 ተራ ቁጥር 5 እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል።
ተራ ቁጥር 2 “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ በቋንቋው የመናገር የመፃፍ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባህሉን የመግለፅ የማዳበር የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም በተራ ቁጥር 5 በዚህ ሕገ-,መንግስት ውስጥ “ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለፀውን ባህሪይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚንፀባርቅ ባህል ወይንም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው ሊግባቡ የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው የጋራ ወይም የተዛመድ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ የሥነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ በመልክዓምድር የሚኖሩ ናቸው።
በሕገመንግስቱ አንቀፅ 39 ተራ ቁጥር 2 እና 5 በተቀመጠው መሰረት እኛ የወልቃይት ሕዝቦች የራሳችን አማራዊ ባህል ያለን ሲሆን ይህ ባህል ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የተረከብነው እና ከዘመን ዘመን እያደገ የመጣ የነበረ ነው። ሆኖም ግን በዚህ 24 ዓመታት ውስጥ ይቅር የራሳችን ባህል ማሳደግ፣ ማስፋፋት፣ መከባከብ ይቅርና እነሆ የማንነታችን መገለጫ የሆነው ባህላችን እየጠፋ በሌላ ባህል እየተተካ የእኛ ባህል እየከሰመ በምትኩ የሌላ ባህል የሚያድግበት የሚስፋፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ህገመንግስቱ ያስቀመጠው መብቶቻችን ተረግጦ በምትኩ አዲሱ ትውልድ የሌላ ብሔር ባህል እንዲቀበል በመደረጉ የአንድ ብሔር ባህል ጠፍቶ በሌላ ባህል መተካት ሕገመንግስታው ጥሰት መሆኑ እየታወቀ በእኛ ላይ ይህ መሰል ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥሰት የተካሄደብን ስለሆነ ይህን ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ቆሞ ታሪካችን ወጋችን ባህላችን በአጠቃላይ ማንነታችን ወደሚከበርበት አማራ እንድንከለል የተነሳ ጥያቄ ነው።
በሌላ በኩል ከደርግ ውድቀት በፊት ሃገራችን በተማከለ አስተዳደራዊ ስርዓት ስትመራ በነበረበት ወቅት እኛ የወልቃይት ህዝቦች በጎንደር ክ/ሃገር በወገራ አውራጃ ውስጥ ስንተዳደር የነበርን ከአማራ ህዝብ ጋር ተፋቅረን ተመሳሳይ ሳይሆን አንድ አይነት ባህል ወግ ታሪክ ያለን የስነ ልቦና ትስስር ያለን በተያያዘ መልክአምድር ጋር የምንኖር ህዝቦች ሁነን እያለን ህገ መንግስቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ እነዚህ እላይ የተገለፁትን የብሔር ብሔረሰብ መገለጫ ተጠቃሚ ሳንሆን ቀርተናል። ያለ ህዝቡ ፍላጎትና ምርጫ ተከለልን እንጂ በራሳችን ፍቃድና ሕገ-መንግስቱ ባረጋገጠልን መስፈርት ተመስርቶ ባለመካለላችን ማንነታችን እንዲጠፋ አድርጓል።
ስለሆነም ዛሬ በዓለማችን ሆነ በሃገራችን ዴሞክራሲ በማደግ ላይ ነው። ምንጊዜም ቢሆን ዴሞክራሲ የሚያድገው በሂደት ስለሆነ ትላንትና እንደነውር ወይንም እንደወንጀል የሚታዩ የነበሩ፣ ነገር ግን የዴሞክራሲ መብቶች የሆኑ ጊዜአቸው ሲደርስ መብት ሁነው ሲገኙ በዴሞክራሲ ስርዓት መልስ ያገኛሉ። ስለዚህ በሀገራችን ሁሉን ያካተተ ህገመንግስት አለን። ስለዚህ ሕገመንግስት ሲባል ክብረ መስዋትነት ተከፍሎበታል። በመሆኑም በሕገ መንግስቱ አማካኝነት የሚመለስ ጥያቄ እስከአለን ድረስና ይህን ጥያቄ የሚመልስ ሥርዓት እስካለን ድረስ የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት ጥያቄ ማነሳታችን ወንጀል ሳይሆን ሕገመንግስታዊ መብታችን መሆኑ አሁንም ሊታወቅልን ይገባል።
በወልቃይት ሕዝብ የደረሱ የፖለቲካ ተፅዕኖዎች
- ልጆቻችን በቋንቋቸው እንዳይማሩ በግድ ትግርኛ እንዲማሩ ተደርገዋል፣
- በየትኛው መ/ቤት የስራ ቋንቋ በግድ በትግርኛ እንድንናገር ተገደናል፤
- የአማርኛ ባህል ቀይራችሁ የትግርኛ ባህል በግድ ተቀበሉ እየተባልን ነው
- የአካባቢያችን ጥንታዊ ያሀገር፣ የወል እና የጋራ ስሞች ማትም የወረዳ፣ ከተማ መንደር፣ ወንዝ ጋራ ሸንተረር ምንጭ በትግራይ ስም ተሰይመዋል።
- በትግራይ ባሉ መስሪያ ቤቶች የወልቃይት ተወላጆች 5 በመቶ የትግራይ ተወላጅ 95 በመቶ ሲሆን፤ ያሉትም እኩል መብትና ስልጣን የላቸውም፤
- ትግራይ ክልል መሆን አንፈልግም ብለው የተቃወሙትን ከ300 በላይ የሚሆኑ የወልቃይት ተወላጆች ከየቤታቸው በጨለማ ታፍነው ተወስደው ያለፍርድ ጠፍተዋል። ለዚህ አባሪውን መመልከት ይቻላል። የእነዚህ ወገኖች በአመለካታቸው መጥፋት ዋናው ምክንያት የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው በመሆኑ የወገኖቻችን መጥፋት ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት ስለሆነ ይህን የፈፀመው የትግራይ መንግስት መሆኑ፤
- ወልቃይት በመወለዳችን በማንነታችን እንድናፍር ሁነናል፤
የወልቃይት ህዝብ በኢኮኖሚ የደረሰበት በደል፣
- ትግራይ አይደለንም ያሉትን በቀጥታ ንብረታቸውን ሀብታችን ተወርሰዋል። ሃብትና ንብረታቸው የተወሰደባቸው ዝርዝር ከአባሪው ጋር ተያይዟል፤
- መሬታቸው ተነጥቆ ለትግራይ ተወላጅ በመስጠት የወልቃይት ተወላጆች ወደ ድህነት እንዲወርድ ተደርገዋል።
- በግልባጩም የትግራይ ተወላጅ አለአግባብ ሃብታም እንዲሆኑ ተደርጓል።
ለዘመናት የወልቃይት ህዝብ ገበሬ ሲያርሰው የነበረ መሬት ተነጥቆ ለትግራይ የእርሻ ድርጅት ተሰጥቷል። እኛ የት እንውደቅ ተብሎ አቤቱታ እንኳን ቢያቀርብ ህዝቡን የትግራይ ክልል በየአመቱ ለምዕራባዊ ዞባ እያለ አዳዲስ የመሬት አዋጅ በማውጣት ለትግራይ ተወላጅ በወልቃይት መሬት ባላባት ሆነው እንዲያስተዳድሩት ሲደግፍ የወልቃይት ህዝብ ግን ከመሬቱ እንዲነሳና እንዲሰደድ የተለያዩ እርምጃዎች ወስዷል። የዚህ ሰለባ የሆኑት ሰዎች የወልቃይት ተወላጆች ለአብነት በአማራ ክል በሶረቃ፣ በአብራሃጅራ፣ በአብደራሬ፣ በመተማ፣ በቋራ በሽህዲ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና በጋምቤላ ክልል ተሰደው ይገኛሉ። የትግራይ ተወላጆች ግን በሰፈራ የመጡ አሁን ከሁለት ሄክታር አሳልፈው የአምሳ እና የመቶ ሄክታር ከዛም በላይ ባለቤቶች ሆነው ይታያሉ። በአጠቃላይ በአካባቢያችን አልምተን እንዳንጠቀም እድሉ ተፈፅሞብናል።
በወልቃይት ሕዝብ በማህበራዊ ኑሮ ላይ የደረሰው ጉዳት፣
- ከመንገድ አንጻር የትግራይ አካባቢ ከወረዳው ቀበሌ የሚያገናኝ ጥርጊያ አብዛኛው ተሰርቷል። የወልቃይት አካባቢ ግን ከወረዳ ቀበሌ ይቅርና ከወረዳ ወደ ወረዳ የሚያገናኝ አንኳን በቅጡ ተሰርቶ አይታይም። ዛሬም የወልቃይት እናት መኪና አጥታ በወሊድ የምትሞት ናት።
- ውሃ ዛሬ በብዙ የትግራይ አካባቢ ንፁህ ውሃ ሲጠጣ የወልቃይት ህዝቦች ግን እንስሳ እና ሰው በአንድ የሚጠቀሙበት በብዙ ቦታ ይታያል።
- ትላንትና የመጣ የትግራይ ሰፋሪ ህዝብ ቧንቧ ውሃ ሲዘረጋለት ጥንታዊ የወልቃይት ህዝብ ግን ምንም ውሃ እና የጉድጓድ ውሃ ሲጠቀም ይታያል የህክምና ተቋማትም ተመሳሳይ ለትግራይ ተወላጆ በሚጠቅም መልኩ የተሰራ ነው።
- የትምህርት ተቋማትም አንድም ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ የለም።
የወልቃይት ህዝብ ልጆቹን አስተምሮ በተወለዱበት አገር ስራ ቅድሚያ መስጠት እና ማግኘት ሲገባቸው ቅድሚያ ለትግራይ ተወላጆ የስራ ቦታ እና እድል ይሰጣል ሊሰጥ ከሆነ ደግሞ በናቱ ወይም በአባቱ የትግራይ ዘር መወለድ ቅድሚያ በሚሰጥ ይጠናል። አጠቃላይ የወልቀቃይት ህዝብ ማህበራዊ ኑሮውን ከትግራ ተወላጆች ተጠግቶ እንዲጠቀም የተፈረደበት ይመስላል። ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደተሞከረው አሁን ሀገራችን በዴሞክራሲና በልማት ጎዳና ባለችበት ወቅት ምንም እንኳ አንዴት እነዚህ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ብሎ የሚጠይቅ አካል ስለማይጠፋ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለመፈፀማቸውና እየተፈፀሙ እንዳሉ ዋናው ምስክር ህዝባችን ስለሆነ ህዝባችን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲያነጋገርልን።
የፌዴሬሽን ም/ቤት ባለው ስልጣንና ኃላፊነት በሰላማዊ መንገድ ያነሳነው የዴሞክራሲ ጥያቄያችን ተመልክቶ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን፣ እኛ የህዝባችን ተወካዮች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ህዝባችን የደረሰበት ሕገመንግስታዊ ጥሰትና እየደረሰበት ያለ በዴሞክራሲ መንገድ እንዲፈታ ከህዝባችን ጋር ለመወያየት እንዲፈቀድልን፣ የህግ ከለላ እንዲሰጠን። በሌላ በኩል ወደእዚህ የመጣን የህዝባችን ወኪሎች ስንመለስ በራሳችን፣ በቤተሰቦቻችንና በሀብታችን ላይ ጉዳት እንዳይደርስብን የሕግ ከለላ እንዲደረግልን በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።
Sendek
ይሄ በ ጭራሽ የ ወልቃይት ህዝብ አይወክልም ከ እውነት የራቀ ሀሰት መሆኑ ለመግፅ እወዳሎ
የህወሃትን የትግል አጀማመርና ቁጭት የሚገልጽ ጽሁፍ አንብቢያለሁ፤ እንደተረዳውትም የአማራ ህዝብ ከአጼ ሚኒልክ መንገስ በኋላ የትግራይን ህዝብ ታሪክ፣ የትግራይን መሬት/ቦታ ወስዷል፣አማራ በትግራይ ህዝብ ታሪክ ይኖራል የሚል የቁጭት ሃሳብ ያነሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ኢህአዲግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ይህ የህወህት መነሻ ሃሳብ የአማራ ህዝብ እየተረዳውም ሆነ ሳይረዳው ከ1983 ጀምሮ በተግባር እየተተረጎመ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በአጼ ሚኒሊክ ዘመን የትግራይ መሬት ተቆርሶ ተወስዷል የሚለውን የትግል ጥያቄወቻቸውን ለመመለስ ከአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎችን/ቀበሌዎችን በመገንጠል ወደ ትግራይ ክልል ወስደዋል፣ እንዲያውም አሁን ዓይን እያወጡ በመሄዳቸው የአማራ እና የትግራይ ክልል መንግስታት ወደ ግልጽ ግጭት ያመሩበት ሁኔታ በ2007 ታይቷል፡፡በአጣቃላይ ህወሃቶች የሚሰሩት ሥራ ራስ ወዳድነት ፣ግብታዊነት የሚታይበት ስለሆነ ከዚህ መጻፍ ደብሮኛል ፡፡ ስለዚህ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ተብሎ የተጻፈው ነገር ትክክል ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከናዚ 80%የከፋ ወያኔ
ወገኑን የበላ ጊዜ ይፍረድ።
በሀገራችን ላይ የወረንበላው ዘራፊ ቡድን ወያኔ ዙሪያውን ክልል ድንበር በመሸጥ ከዛም ባለፈ ለአባይ ግድብ ተብዬው ካሣ እጅ መንሻና መጎናፀፊያ ያደረጎትን እምዬ ኢትዬጵያን እውነት ግዜና ሠአቱ አሁን ነው በጀግንነት ሉአላዊነታችን አሥከብረን የኖርን ህዝቦች በታሪክ አተላው ቡድን ውርደት ውሥጥ ሥንሆን ኦሮሞውንም አማራውንም ጥቅሙን ማንነቱን የሚፃረሩ የውሥጥ ተወላጅ ባንዳዎችን ከሥራቸው ነቅለን እንደምናሦግድ እውን ነው።
ይህን መልክታችንን በመከላከያ ሠራዊት ውሥጥ በፖሊሥ አባላት እሥካሁን በዜጎች ላይ የገዛ አፈሙዝ ላለማሣለፍ ለሣምንታት በትእግሥት ሥትረዱን ቆይታችሀል አሁን ቀጣዩ ታማኝ ተብዬ የናዚው ቅልብ ወታደሮችን እንደምናሥወግድ እና እየተላለፈላቸው ያለውን መልእክት አጠናክረን በማሥቀጠል እንዲሁም የደንብ ልብሣችሁን በማቃጠል የገዥውን ሥርአት ያላችሁን ጥላቻ አሣይታችሁናልና እናመሠግናለን በርቱ።
ሞት ለወያኔ!
ይድረሥ ለወያኔዎች……
በወልቃይትና ቅማንት የሚገላወደው ወያኔ የዘረፈውን ዘርፎ የማተራመሥ መግለጫዎችን በተለያየ መንገድ ሠምተነዋል አሁን መልሡ አንድ ነው ያለምንም ማጭበርበር ትግራይ የአማራን መሬት ወደ ቀድሞው ሥፍራ ይመልሥ ለቆ ይውጣ ለመገንጠል ካሠቡ እኮ የታሪክ ከለላን መጣሥ ከውንብድና አይተናነሥም።
ሞት ለወያኔ ቶሎ ለቃችሁ ውጡልን
ዘግይቶ በደረሰኝ መረጃ ከአራዳ ፍርድ ቤት እሥረኞች ማምለጣቸውን እጅጉን አሥደሥቶኛል እንዲህ ነው እንጂ ፖሊሥ እኮ የህዝብ ነው አግአዚ አይደለም ነገ ግን አግአዚ ነን ባዬች ሸሚዛችሁን አንጥፋችሁ አራዳ ላይ ሥትለምኑን እንደምናይ የሩቅ ህልም አይሆንም
*የፒያሣ የሥልክ ኔትወርክ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል
ሞት ለወያኔ
Awaj awaj yesemah lalsem asema ye gonder semien- merab gzat yehonut welkait, Tegedie, Telemt, humera ke Telat tgrai woyanie worera neTa wetewal. Ke zariie tahsas 7/4/2008 be etiopia aqoTaTer jemro enezihn ye gonder Tentawi smien mrab weredawech merab tgrai malet wonjel new yasqeTal, ye duryie worada woyanie tebabari net bemehonu yaseqlal. Blu ye gonderiew welkaitie, Tegedch, Telemtie new.
Worada woyanie wede meqabr
የፈለገ ኢንተለጅንሥ ቢኖር የህዝብ ፍላጎትን ማቆም አይቻልም!!!
እስካሁን የዘገየው በህዝቡ ድክመት ይመስለኛል እንጅ ለመገናኛ ብዙሀን ተግታችው ማቅረባችሁን አታቋርጡ
መቼም ቢሆን የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ መመለሱ የግድ ነው።
ሞት ለባንዳ
You are Tigre and you are defending the genocide committed by Woyane. You will pay the price.
But azeb mesfin she is from welkayt.is azeb mesfin amara.i am from welkayt and i am not tigre i am not amara i am from ethiopia.most of the opposition called TPDM are from welkayt.but TPDM is from tigre.so the answer is
ወያኔ የቤት ስረውን አልጨረሰም ገና ብዙ ይቀረዋ
ጎንደር የለም ወሎ የለም
በአሁኑ ሰዓት በወሎ ውስጥ ምን እየሰራ ይመስላችሎል
ወርኢሉን አካባቢ ፈላሻ ሞራ ዘርን ነው በማለት ሕዝብን ሰነልቦና በመስልብ ላይ ናቸው ይህን ስራ የሚሰራው ደግሞ አንዳንድ ሆደማ ምሁራንና እስራኤላዊያን መሆናቸው ታውቆል
ነቃ በል ወሎ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሃገራችሁን የምትወዲ እንቃባቸው!
ሳተናው አሊ
ወያኔ አንድነት ያጠፋዋል/ያመዋል/ያሰጋዋል
ነገር ግን ወያኔ ሻቢን ግብጽ፣ሱዳን ኢትዮጵያን ከማጥፋት ወደላለ አይሉም
ጎንደርን ወሎን አፈራረሱ በታተኑ
አዎ ገብሩ አስራት በስልጣን በነበረበት ወቅት በሁመራ የሠራው ደባ ሲጋለጠ 40 ወጣቶችን በእስር ቤት ውስጥ መግደሉ መቼ ይሆን ይህ ነፍሰገዳይ ዛሬ በእኛ መካከል መኖሩ ሳይ ያመኛል እንድታውቁት ላልሰማ አሰማ
ሳተናው አሊ