የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምስክርነት እንደማያቀርበው ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4/2008 ዓ.ም ለልደታ ፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹የ18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለመስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን›› ብሏል፡፡
እስክንድር ነጋ ለእነ ዘላለም ወርቃገኘው በመከላከያ ምስክርነት ከተቆጠረ በኋላ ከህዳር 13 /2008 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀጠሮዎች በምስክርነት ሳይቀር የቀረ ሲሆን ዛሬ ታህሳስ 6/2008 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ በላከው ደብዳቤ መሰረት ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ ከአንድ አመት በፊት ከ6 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩል ለ30 ደቂቃ ሲጠየቅ የነበረው እስክንድር ነጋ በአሁኑ ወቅት እንዳይጠየቅ ተከልክሏል፡፡ በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ እስክንድር ነጋ የታሰረበትን ክፍል በመፈተሽ መፅሃፍ ቅዱስን ሳይቀር መነጠቁም ይታወሳል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

እረ የጀግና ያለህ እረ ያርበኛ ያለህ እስክንድር ነጋን ምንም ነገር እንዳያነብ መከከል ማለትእኮ በቁሙ መግደል ማለት እኮ ነው። imagin that you are not allowed to read any thing all day all night. you know if our organs are not used for the appropriate function they eventually become dysfunctional and እስክንድር needs our help,but how? ? ? ጎቨዝ ! ! ! ጀግና ! ! ! “ደም የተቀባ ዝምብ አይፈራም”ይባላል ወያኔ እኮ already ደም በደም አድርጎናል። ቃሊቲ, fucken ማዕከላዊ፥ቅሊንጦ እና ዝዋይ አንድ ነገር መደረግ አለበት ! ! !
እውነት በሀሠት ካባ አትዳፈንም!!!