ወያኔ ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት ቀረጻ አካሄደ::

ወያኔ ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት ቀረጻ አካሄደ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎Anwarmosqueexplosion‬ ‪#‎AnwarConspiracy‬

የወያኔ መንግስት በዛሬው እለት አንዋር መስጅድ ና በህገ-ወጡ መጅሊስ ለተጨማሪ ፕሮፖጋንዳ ቀረጻ አካሄደ
የመንግስት ሚዲያዎች ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት የአንዋር መስጅድ ኢማም ጡሃ ሃሩን እና የአንዋር መስጅድ አስተዳደርን አቶ ሸምሱን እንዲሁም የአንዋር ምእምናን በማለት የተዘጋጁ ካድሬዎችን አነጋገሩ::

”መውሊድ ማክበራችንን እንቀጥላለን በአሸባሪ ጥቃት መውሊድ ማክበር አንተውም ” የአንዋር መስጅዱ ኢማም – ”ጁምአን ጠብቀው ሆን ብለው ነው አሸባሪዎች ጥቃት የፈጸሙት ‘የአንዋር አስተዳደር አቶ ሸምሱ
ጥቃቱ አክራሪነትን ከመታገል አይገታንም የህገወጡ አዲስአበባ መጅሊስ መጅሊስ አመራር ዶክተር አህመድ
ትላንት ቢቢኤን ጨምሮ ለተለያዩ ሚዲያዎች ኢንተርቪው አልሰጥም ያሉት ሚዲያዎች በዛሬው እለት ለመንግስት ሚዲያ አስገራሚ ንግግሮችን አድረገዋል
ቢቢኤን ታህሳስ 1/2008
በትላንትናው እለት በታላቁ አንዋር መስጅድ ከጁምአ ሶላት በሁላ የቦንብ ፍንዳታ መከሰቱን ቢቢኤን በቀዳሚነት ከዚያም በመንግስት ሚዲያዎች፤ እንዲሁም በውጭ ሚዲያ አልጀዚራ እና ቢቢሲን ጨምሮ ክስተቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
በርካታቶችም ድርጊቱ በመንግስት የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ የተነሳበትን ከባድ ተቃውሞ ለማስቀየስ እና ሙስሊሙን በመውሊድ ሰበብ ለመከፋፈል የታቀደ መሆኑ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
የዚህ ማሳያ የሚሆኑ ቀረጻዎች በዛሬው እለት ኢዜአ በታላቁ አንዋር መስጅድ ጠዋት 3፡30 በመገኘት የአንዋር መስጅድ አስተዳደር አቶ ሸምሱን እና ኢማሙን ጡሃ ሃሩን አነጋግረዋል
በትላንትናው እለት ስለሁኔታው እንዲያስረዱ በተደጋጋሚ ከቢቢኤን ሲደውላላቸው ሶላት ላይ ነኝ እናንተ ጋር ሶላት የለም ወይ ሲሉ የነበሩት አቶ ሸምሱ ዛሬ ለኢዜአ ሲናገሩ እንደነበር በቦታው የነበሩ እማኞች ገልጸዋል
አቶ ሸምሱም ለኢዜአ ሲናገሩ አደጋው ሆን ተብሎ ጁምአን ጠብቆ የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ ጁምአ በመሆኑ አንዋር ግቢ ውስጥ መኪኖች ፓርኪንግ ስለማይቆሙንጅ መኪኖች ቢኖሩ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ መንግስት እነዚህን አሸባሪዎች ፈልጎ ይቅጣልን ሲሉ በተማጽኖ እና በማስተዛዘን ተናግረዋል
የአንዋር መስጅዱ ኢማም ደግሞ ለኢቲቪ ዛሬ ሲቀረጹ ሲናገሩ ” የፈለጉትን ቢያደርጉ መውሊድ ማክበራችንን እንቀጥላለን በአሸባሪ ጥቃት መውሊድ ማክበር አንተውም ” በማለት የተጠበቀ ከፋፋይ ንግግራቸውን እና የመንግስትን እኩይ የመከፋፈል ግልጽ አላማ የተገመተውን ተናግረዋል፡፡
የአንዋር መስጅዱነ ኢማም ጡሃ ሃሩን ከዚህ በፊት በአንዋር መስጅድ ስለገቡት የፕሮቴስታን ሰባኪያን አያገባኝም ምን አገባችሁ ሲኩ ቆይተው አሁን ደግሞ ሆን ተብሎ በመውሊድ ለሚያከብሩ ተብሎ የተደረገ የሽብር ጥቃት በማስመሰል የመንግስት ጉዳይ አስጻሚ መሆናቸውን በሚያስብቅ መልኩ ተናግረዋል፡፡
ከሁለቱ በተጨማሪም አንዳንድ የአንዋር መስጅድ ምእምናን በማለት ሶስት የተዘጋጁ ምልምል ካድሬዎችን ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታው ለማዋል ቃለመጠይቅ አድረገዋል ይህንንም በቦታው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ይህንንም በምሽት ዜና ወይም በቀጣይ በሚሰራ የሃሰት ዶክመንታሪ ሊታይ ይችላል ተብሏል፡፡
በትላንትናው እለት የተፈጠረው አደጋ ሆን ብሎ መንግስት ከዚህ ቀደም በአሜሪካ መንግስት እና በዊክሊክስ እንደተጋለጠው ራሱ አደጋ በማድረስ አሸባሪዎች አደረሱት በማለት ይሰራው የነበረው ድራማ አካል መሆኑን በርካቶች እየተናገሩ ነው፡፡
በሌላ በኩል የህገወጡ የመጅሊስ አመራሮችም ጥቃቱ ከጀመርነው የአክራሪነት ትግል አይገታም ሲሉ ለህዋሀት ልሳን ለሆነው ፋና ተናግረዋል መንግስት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በአክራሪነት እና አሸባሪነት በመፈረጅ በቀጣይ ጊዜ ለሚያደርገው ጥቃት ድራማ ነው ተብሏል

በአሁኑ ሰአት መንግስት ባለበት ከፍተኛ ተቃውሞ ምክኒያት አለም አቀፍ ሽብረተኝነት ስእል ለማላበስ እና ለማስቀየስ የሰራው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ማህበረሰቡም የመንግስትን እና የደህንነቶቹን እኩይ ሴራ እየተከታተለ በህብረት ማክሸፍ እንዳለበት ድምጻችን ይሰማ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

Minilik Salsawi's photo.

14 Comments on “ወያኔ ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት ቀረጻ አካሄደ::”

  1. All the pictures and

    Videos that are posted

    in social media are all

    from the recent BURKINAFASO

    uprising. Shameful act.

  2. ቪዲዮውን በሥሎው ሞሽን ታይቷል ድርጊቱን የፈፀሙትና ሢሸሹ የነበሩት የወያኔ ቅልብ የፈንጂ እውቀት ያላቸው መሆናቸው በሠከንድ ልዩነት ከፈንጂው ቀድመው ሢሮጡ ተመልክተናል ይህን የማወናበድ ሥራ የሠራው ወያኔ ሥለመሆኑ አንጠራጠርም ከላይ ያላችሁ የወያኔ ውሾች ህዝብን አሣንሣችሁ አትመልከቱ ህዝቡ ጥሎዋችሁ ሄዷል አሁንም ጨለምተኛው የሙት መንፈሥ አልተዋችሁም።

    ሞት ለወያኔ

    ፈንጂው የተቀናበረው በወያኔ ነው!

  3. በግራም ነፈሠ በቀኝ ይህ ድርጊት የወያኔ ነው ጥርጥር አይግባችሁ ወገኞቼ ባንዳ የባንዳነቱን ሥራ አይተውም ከሀያ አራት አመት በፊት እኮ ድርግን መፅረጊያ መወልወያ እያሉ እያዞሩ ሢያፈነዱ የነበሩትን ለምሣሌ ሽርሙጣው አቦይ ሥብሀትን ማንሣት እንችላለን።

  4. Yihe gize yalfebt akahed newe echin doro qofra yemtawetaw bltet newe minm trtr yelwum be weyane ena be weyane yetqenabere newe

  5. way back in the day I used to heat the
    Governmet in power but now I have changed
    my mind b/c I came to observe that these
    extremist are world # layers the will not
    hesitate to damage the country .

  6. ይህ የወያኔ ሥራ ነው መንዙማ እየዘመሩ ባሉበት ግዜ ከሀላ በመምጣት እንደወረወሩና እንደሸሹ በግልፅ አይተናል ይህ የፈንጂ ወዳጅ የሆነው ወያኔ ሥለመሆኑ አንጠራጠርም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*