በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች
በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች – (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የአረንጓዴ ተክሎች ለጤና ጠቃሚ መሆን የማያጠራጥር ሲሆን ለዛሬ በጥቂቱ ስለተክሎቹ አይነትና ጥቅሞቻቸዉ ልነግራችሁ ወደድኩኝ፡፡
✔ ብሮኮሊ
ይህ አትክልት በቫይታሚን ሲ እና በፋይበር የበለጸገ ሲሆን በዉስጡ የያዛቸዉ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የሳንባ እና የካንሰር ህመሞችን የመከላከል አቅም አለዉ፡፡
✔ ጥቅል ጎመን
የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
✔ የጀርመን ሰላጣ
የጀርመን ሰላጣ ሠዉነታችንን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሠጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለብጉር፤የፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል፡፡
✔ ቆስጣ
ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡
✔ የሾርባ ቅጠል
ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት የሾርባ ቅጠል በዉስጡ ፎሊክ አሲድ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኬ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን የአጥንት መሳሳትንና የልብ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ ሠላጣ
ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡ ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡
✔ ጥቁር ጎመን
ጥቁር ጎመን በዉስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ቢ2፣ቢ3፣ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም ፣ካልሲየም ፣ፎስፈረስ እና አዮዲንንም ይይዛል፡፡የሠዉነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት ነዉ፡፡
ለወዳጅዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ

እናመሰግናለን ዶ/ር
ውድ ወገኖች ሁሉ እንደሰው ለሚያስቡ ጤናይስጥልኝ ሰላም ናችሁ
እኛ መቼም ቢሆን ያለንበትን ሁኔታ ከባድ ነው
ጥያቄ አለኝ
1- በ22/03/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን በሆስፒታልና ከተጎጅ ቤተሰቦች እየተነገር ነው ስለዚህ እባከችሁ ወገኖች ሬድዩ ሆስፒታሎችንና ትምህርት ሚኒስትር ጠይቃችሁ ለወደፊቱ ለሚደረገው ጥንቃቄ እንድንወስድ ብትረዱን?
2- በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ድርቅና ርሃብ ምክንያት የሚመጣው የበሽታ አይንት ምን እንደሚሆን ወርርሽ፣ተስቦ፣ኮሌራ ወዘተ ሕዝብ ቢያውቀውና ብናውቀው መልካም አይመስላችሁም ?
3- ሌላው ጥያቄዩ በአዲስ አበባ ውስጥ ለህክምና ለካርድ ብቻ 1000 (አንድ ሽህ ብር) የሚጠየቀው በምን ምክንያት ይሆን? እሱም ሎሪት የማነብርሃን ክሊኒክ ሲሆን እውነት ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያዊነትን ያውም ብዙ ድሃ ሕዝብ ባለት ሃገር ውስጥ ለካርድ 1000 ብር ለካርድ 1000 ብር ተው ዶ/ር በዛ እጅግ በዛ ከዚህ ሕዝብ ነው የተፈጠራችሁት ያስተማራችሁ ተው እባከችሁ እንደ ሰው አስቡ?
ሳተናው አሊ