በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የረሃቡን መረጃ ለማርገብ የገጽታ ግንባታ ስብሰባዎች ሊደረጉ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– ከመከላከያ ሚኒስቴር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ላለፉት ሁለት ቀናት የተሰበሰቡት የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን የሃገሪት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለ ረሃቡ ያላቸውን መረጃ ለማርገብ እና ስለ ህዳሴው ልማት እና ዲሞክራሲ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት በሚል ሰበብ የገጽታ ግንባታ በየክፍሉ ስብሰባዎች በቡድን በቡድን እንዲደረጉ መወሰናቸው ተሰምቷል::

በአስቸኳይ በዚህ ሳምንት እንዲጀምር የሚደረገው ይህ ስብሰባ ሰርጎ ገቦች እንዳያሰናክሉ እና የሰራዊቱ አባላትን በአጉል ስርኣት አልበኝነት እንዳይወሰውሱ ስብሰባዎች ላይ ከባድ ቁጥጥር እንዲደረግ እና በየቡድኑ ሁኔታዎችን ቤንቃት የሚከታተሉ ወታደራዊ ደህንነቶች እንዲመደቡ እንዲሁም ለቡድን አወያይ የሚሆኑ አባላት በልስላሴ እና በሰላማዊ ባህርይ ጸረ ሕዝቦችን ለመለየት በሚያስችል ዘዴ ተመሳስለው ስብሰባውን እንዲመሩ ሲባል ቡድኑ 30 የሰራዊት አባላት ማቀፍ እንዳለበት መመሪያ ተላልፏል::

ይህ በበየእዙ ካሉ በየካምፑ ለሚኖሩ የሰራዊት አባላት የሚደረገው የገጽታ ግንባታ ስብሰባ በከተማ ለሚገኡ የሰራዊቱ አባላት እና ለአየር ሃይል አባላት እደማይሰጥ ከወዲሁ ሲታወቅ በረሃቡ ዙሪያ ያለውን መረጃ ለማለዘብ ግን ለነዚሁ ክፍሎች ግልጽ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የመከላከያ ሚኒስቴር ምንጮች ለምንሊክሳልሳዊ ተናግረዋል::በመከላከታ ስራዊቱ ውስጥ አለመተማመን እና ከፍተኛ የዘረኝነት ጫና ከመኖሩም በላይ የአንድ ብሄር ሰዎች በበላይነት እና በጥቅም ተሳስረው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እያጭበረበሩ እንደሚገኝ ይታወቃል:: ጥቅማ ጥቅም እና ማእረግ ለማግኘት አዳጋች የሆነበት የሰራዊቱ አባላት ጥያቄዎችን ቢያነሳም በአደርባዮች እና በሆድ አደሮች እየታፈነ ለሐሓት ሰው በላዎች ተላልፎ ይሰጣል::

በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን አሁን በሃገሪቱ ከተከሰተው ረሃብ እና ድርቅ ጋር ተደምሮ ከፍተኛ አደጋ ይፈጥርብኛል ብሎ ያሰበው ወያኔ ያለውን ሃይል እና ገንዘብ ሁሉ በመጠቀም መረጃዎችን ለማዳፈን እና ምንም እንቅስቃሴ እንዳሌለ ለማስመሰል ደፋ ቀና እያል በመስራት ላይ ሲሆን በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ላይ የሃስት ዶክመንተሪዎችን በመስራት በችግር የቀጨጨችውን አገር የለማች ለማስመሰ ከመጣሩም በላይ ወገን እየተራበ በየቦታው የሚደገሱ የፓርቲ ድግሶች ለድርቁ እና ረሃቡ አቅም ግንባታ እንደሆኑ ለማኝበርበር በመሰበክ ላይ ይገኛሉ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

8 Comments on “በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የረሃቡን መረጃ ለማርገብ የገጽታ ግንባታ ስብሰባዎች ሊደረጉ ነው::”

  1. የሚገርመው ለቄንጥ 4ወር የፈጅውን ገና መግባቱ ያልታወቀውን የ6ቢሊዬን ብር ሥንዴ በባቡር እናከፋፍላለን ማለቱ እዩኝ እዩልኝ ልማቴን እድገቴን ተርበን የሠራነው ለማለት እየሯሯጡ ነው

  2. ይህ መከላከያ ተብዬ ደግሞ የሀገርን ሀብት ምንዛሬ እጅጉን እየመጠጠ ያለ ተቋም ነው የታንክ መድፍ ሂሊኮፕተር ታንክ ድሮን አውሮፕላን አቶቢሥ ….ሠራሁ እያለ ከ100ቢሊዮን ዶላር ያላነሠ ምንዛሬ እያባከነ ይገኛል ዘመናዊ የጦር ሀይል የተባለው በሦማሊያ ውጊያ እየታየ እንደቆሎ እየረገፈ ይገኛል ራሻ ጥሎት የሄደውን መሣሪያ አዲሥ መግዣውን ባለፈ አሠልቺ ጥገናና በየገደሉ ተደፍተው የሚቀሩት ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ብክነት የሚታይበት ተቋም ጭምር ነው ሠራሁ የሚላቸው ትራንሥፎርመሮች በየቦታው እየፈነዱ የሀይል ችግር ፈጥረው ኢንደሥትሪውን እንደግመል ሽንት ወደሀላ እየጎተቱት ነው ለትውልት እና ዘመን መሻገር የማይችሉት ተሽከርካሪዎቹን ቀደም ሢል በደርግ ግዜ የራሽያው ኦራል ካማዝ ኒቫ አይፋ “ለእናት ሀገሩ ተደፋ” እያልን ሥናፌዝባቸው የነበሩት ከራሽያ በእርዳታ ነበር የምናገኛቸው የውጭ ምንዛሬ ብክነት ፈፅሞ አልነበረም አሁን የተገላቢጦሽ አወኩኝ ናቅኩሽ የቻይናን ሥሪት ሢኖ ተሽከርካሪዎችን አሥገብቶ ለመገጣጠም እርዳታችሁ በእውቀት ይሁንልኝ ብለው ይህን የምናሪ ሀብት እጅጉን እያባከኑ ይገኛሉ እሽ የሚሸጠው የታንክ አሩር ገቢ የታል? እሥኪ ይንገሩና ይህን ብክነት ማካካሻው የት አለ? ታንክ ሸጥን ትላላችሁ ገቢውሥ? ይህን ካልኩ መቼም ሞታም ሥራ የማታቆመው ምላሣችሁ የሥራ አጥ ለመቀነሥ ነው ትሉን ይሆናል አይደለም ወጣቱ ሥራ እድል ለማግኘት ብቸኛው የሞኖፖሊ ሥርአት አራማጅ ተቋም መከላከያ ብቻ መግባት አይጠበቅበይም በርካታ ብዙ አማራጭ ሥራዎችን ከኤፈርት የሚበልጡ ተቋማትን መቀላቀል ይችላል እናም ወጪው ከገቢው በላይ የሆነ ተቋም ሀገርን እየጠቀመ ነው ማለት ዶሮን በመጫኛ እንደመሸወድ ነው ለ24 አመታት ኦዲት ያልተደረገ ያለጥቅም ተዘርጥጠው በሚገኙት ተቋሙ የሀገር ሀብትን እንደልቡ እያሽከረከረ እያምታታ የሚበዘብዝ መሆኑን ሁሉም ያውቃል የሚገርመው ከውጭ አገልግለው የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ዋጋና መከላከያ ምንዛሬና የሠው ሀይል አባክኖ ካመረታቸው በዋጋም በአገልግሎትም ሀገርን የማይመጥኑ መሆናቸው ያሣፍራል ተግባራቸው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ እየሆኑ ነው ይህ ተቋም እሥካሁን ያባከነው ሀብት በምግብ ራሣችንን ለመቻል ከእርዳታ ነፃ ለመሆን የሚያሥችለን የረሀብ አደጋን ልንመክትበት የምንችለውን በአፍሪካ ትልቁን ዘመናዊ የእህል ጎተራ ለ10አመት ያላነሠ እደላ የሚውል ማቋቋም እንችል ነበር ይህ ከአጀማመሩ በረሀብ ቁንጣን ብረት የጨበጡት ሌባ ወያኔዎች ግባቸው የት ላይ ነው በሥልጣን እያሉ እንኳን በትንሹ ከ5 ያላነሡ ረሀብ አደጋዎችን መቋቋም አልቻሉም ወገን ይረግፋል እነሡ ግን ይሠባሉ ።

  3. know that any conference, meeting, or gathering by woyane is only and only to know what the targeted audience is thinking about about them (ye amlekakt fetesha), to identify who is a against them (so that to eliminate him) and who is a coward (so that can be recruited to be a sellout “Hodam” appointee wherever they want him) The best strategy: listen to what they say, don’t criticize, don’t give information that may benefit them, praise them in a smart way , and call it a day! Be smart, not arrogant when fighting woyanee from the inside.

  4. ሰው ከሆኑ በድርቅ ወቅት ሕዝብ በረሃብ የእሞት እነሱ በጭፈራ ደንዝዘዋል/ሰውንም አደንዝዘዋል ከቶ ምን ይሻለን ይሆን?
    አይ የሰው ልጅ ከንቱ ምን ለመሆን ታስቦ ይሆን በኢትዮጵያ ላይ
    ሃገርን ለማጥቃት ብአንዱን (300.000.000) ሶስት መቶ ሚሊዩን ብር ወጪ አውጥቶ ድግስ ደግሶ በየከተሞች፣በችግር በኩፉ ቀን ወገን፣እንሰሳት በርሃብ ፣በጥም እየሞቱ ፣ስደት አይግባኝ እየነጎዲ
    ደግሞ የብአድን ታጋይ ተባየዋ መጽሃፍት አስመረኩኝ ትላለች ጉድ ጉድ ዘመነ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ጡት ነካሾች ብዛታቸው
    ለወደፊትም እናጠፋታለን ነው የሚሉን/ቱ/ ሃገረን፣ወገን ለረሃብ አጋልጦ ስንት ወር ጨፈሩ እውነት እነዚህ አማራን ይወክላሉ?
    ወንድሙን ገድሎ ሃውልት የሚስራ/ት/ የኢትዮጵያ ጠላት ማን ነው?
    ብአንድን በዘመናት የሚፈነዳ ለትውልድ ትውልድ ያስተላለፈው የማይሽር ሃኪም የሌለው ነርሳ የተከሉ እሾኮች ናቸው!

    ሳተናው አሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*