ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል የተሰጠ የአቋም መግለጫ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ጥቅምት ፳፮ ፳፻፰

ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል                                                                                       
ለሚመለከተው ሁሉ
ድምጽ አልባ ለሆነው ህዝባችን፣ ነጻነቱን ለተገፈፈ ወገናችን በምርኮ ለተቀየረ በቅኝ ለተቀፈደደች አገራችን ልንቆምላት ታሪክ ግድ ስላለን ነው ለጋራ ዓላማ በጋራ የተዋቀርነው። የድልም አብነቱ ህብረቱ ነውና፤ ለዚህ ነው ከተለያየ የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበራት ልዩነትን ወደ ጎን ብለን ግብረ ሃይል የሆንነው። ለነጻነት ትግል መስፈርት የሆነን ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው። የተለያየ ሀይማኖት ስላለን አብሮነታችንን ህብር አደረገው እንጂ አልለያየንም። አፅመ ርስታችን ኢትዮጵያን ስለምንወዳት አጥፊዋን ወያኔን ክፉኛ የተፀየፍነው፤ ተፀይፈን ብቻ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ሳይሆን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ የተቃወምነው የምንቃወመውም!!!
ለግል ህሊና ወይም ትውውቅ መደለያነት ስንል እውነት ብለን ያመነውን ከማስተጋባት ወደ ኋላም አንልም፤ የአቋማችን ጭብጥ በጥቅሉ ለመንደርደሪያነት ከገለፅን በኋላ በግብረ ሃይሉ ውስጥ ከተሰባሰብነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታይ አባላቶች ኢትዮጵያን ለማቆየት ታሪኳ ሳይደለዝ ጥንታዊ ሀይማኖቶቿ ተከብረው አንድነቷ ጠንክሮ ትቆይ ዘንድ የትግላችን አካል ናቸውና፤ ያለፉትን ሁለት ወራት ህሊናችንን ያስጨነቀው በከተማችን ባለችው የደብረ ሰላም ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የፈነዳው ድብቅ ሆነ እምቅ ስሜት ከየት ተነስቶ ወዴት ይደርስ ይሆን የሚለው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ሁኔታውንም ለመከታተል፣ እውነትንም ለማወቅ አውቀንም ለመፍትሄው አካል ለመሆንም ሆነ አቋም ለመያዝ ሙሉ መብት ያለን ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ስለሆን በደብረ ሰላም ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የተካሄደው እና እየተካሄደ ያለው ሁናቴ የጋራ ግንዛቤ አስጨብጦናል፤ ስለሆነም ከወያኔም ሸፍጥ ሌላ በልዩ ሁኔታ የምንጠላው አካል በቤተ ክርስትያኗ ውስጥ የለንም፤ ይህንንም ስንል በበኩላችን እውነታውን ለመፈለግ ባለ አደራ ቦርዱንም ሆነ የተቆሮቋሪ ኮሚቴ አባላትን በአካል አግኝተን በማነጋገር እንዲሁም ለአምስት ተከታታይ ሳምንታት በቴሌኮንፍረንስ ተወካዮቹን በመጋበዝ ከምእመናኑ ጋር ለረጅም ሰአታት በመወያየት በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኗም በአካል በመገኘት በአይናችን ያየነውን በማስረጃነት ያነበብነው ዋቢ አድርገን ነው ከዚህ በታች ያለውን የምንለው።
በቤተ ክርስትያኗ ውስጥ ያየነው መረን የለቀቀ አሠራር የወለደው ኢዴሞክራሲያዊ አካሄድ ቤተ ክርስትያኗን ወደ መዘጋት እየተጓዘች እንደሆነ የተረዳነው። የኛ አቋም ይህ ለአምልኮተ እግዚአብሄር ሲባል በህዝባችን የተገነባች እድሜ ጠገብ ቤተ ክርስቲያን ዳግም መዘጋት የለባትም የሚል ጽኑ ፍላጎት ያለን።
ወደ መፍትሄ ሀሳብ ከመሄዳችን በፊት ከዚህ በታች የምንገልጸው ችግር ብለን የተመለከትነውን ነው፦
ሀ)ከፈጣሪ በታች የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት ህጋዊ አባላት መሆናቸውንና ሿሚ ሻሪዎቹም እነዚሁ አባላቶች ብቻ መሆናቸውን አለመገንዘብ።
ለ)ባለፈው ወር የታወጀው ሹም ሽር ፍፁም የህዝብን የማሰብ ችሎታ የናቀ የቤተ ክርስቲያኗን ህግ የነቀነቀ ለቀጣዩ ትውልድም መጥፎ አርአያ የሆነ፣ በአውደ ምህረቱም ላይ የታየው እና የሚታየው ስሜትን ያልገራ አካሄድ መሆኑን።
ሐ)በግራ በቀኙ ጎራ የተሰለፉ ሃላፊነት ያለባቸው ክፍሎች ችግርን በሰለጠነ ውይይት የመፍታት ክህሎታቸውን የተፈታተነ ሁኔታ በመከሰቱ፦
መ)በተከፈተው ቀዳዳ ፀረ ህዝብና ፀረ አንድነት የሆነው ወያኔ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን መስሎ ሰተት ብሎ እንዲገባ ያመቻቸ ሁኔታ መፈጠሩ።
ሠ)በኋላም ለሁለት ሳምንት በተገኘ የግለሰቦች ያሸናፊነት ሰላም በፈጠረው አጉራ ስሜት እንደ አሁኑ ሰላም አልተገኘም በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ መጓዝ ዋጋቢስነቱ በመታየቱ።
ረ)በዋናነት ፈሪሃ እግዚአብሄር የሆነው ምእመናን ለሀይማኖቱ ቀናኢ ስለሆነ እምነቱን እንደ መያዣ በመያዝ በተፈጠረው ሁናቴ በገዛ ቤተ ክርስቲያኑ ሃዘንተኛ መደረጉ ሳያንስ በሀሰት ቅስቀሳ እልል በል፣ አጨብጭብ እየተባለ ነገ እውነቱ ሲወጣ የሚደርስበትን ህሊናዊ ቁስል ሊገናዘብ አለመቻሉ ክፉኛ አሳዝኖናል።
ሰ)በተለይ አወቁ በቁ የተባሉ የተማሩትን ትምህርት ያካበቱትን እድሜ ያካበቱትን እውቀት ሁከት ማራገቢያ ማድረጋቸው በኦርቶዶክስ እምነት ላይ ጥቁር ነጥብ ማስጣሉ፤
ሸ)  በመጨረሻም የዚህ ሁሉ ችግር አባላት ተስማምተው ያወጡት ለ ፳፯ አመታት የተመራበትን መሰረታዊ ህግ ተግባራዊ አለማደረግ፤ ህጉንም አለማክበር የፈጠረው ክስተት ዛሬ ምእመኑን ከመከፋፈል አልፎ ነገ ከሚከሰተው ከንብረት አልፎ በሰው ላይ እስከ ደም መፋሰስ ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ቤተክርስቲያኗን የመዘጋት የመሳሰሉ አደጋ እንዲዣበብባት አድርጓል።
ለዚህም ዋቢ የሚሆነው መብታችን ይከበር ብለው በሚጮሁት አባላት እና ወያኔ ከነመርዟ የበለጠ እንዳትገባ ችግሩ ወደ ጠረጴዛ ውይይት ይሂድ ከማለት ውጭ ሌላ አቋም የሌለውን የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይልን ለማጥቃት “በዚህ በምንኖርበት ሀገር ጉልበት መፍትሄ እንደማይሆን እየታወቀ አግአዚን መሰል” የሰላም እና የጸጥታ የወጣቶች ሃይል የሚል እስከማቋቋም መደረሱን እየሰማን እንገኛለን፤ እነዚህና የመሳሰሉ ግንዛቤዎች ሲኖረን በሌላ በኩል ደግሞ ከላይ የተዘረዘሩት ችግርች እንዲፈጠሩ የባለ አደራ ቦርዱ የአሰራር ድክመት አስተዋጽኦ አለው የሚል እምነት አለን።
ታዲያ ምን መፍትሄ አለው ለሚለው የብዙሀን ጥያቄ፦ ችግሩ በአሜሪካ ህግ ፊት ቀርቧልና የሀገሪቷ ህግ መፍትሄ እስኪሰጥ ወይም ዘላቂ የሽምግልና መፍትሄ እስኪያገኝ የሚፈጀው ግዜ በውል ስለማይታወቅ፤ እኛም ከላይ የጠቀስናቸው የሚታዩ ችግሮች ቤተ ክርስቲያኗን በአጭር ግዜ ውስጥ ሊያዘጋት ስለሚችል ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ በግዚያዊነት ቤተ ክርስትያኗ ለምእመናን ክፍት እንድትሆን እና አገልግሎቷ እንዳይቃረጥ ከሁለቱም በኩል እኩል ቁጥር ያለው እንዲሁም ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙባቸው ገለልተኛ ግለሰቦችን በእኩል ቁጥር ጨምረው ቤተ ክርስትያኗ ዘላቂ መፍትሄ እስክታገኝ ድረስ ቤተክርስቲያኗን በገለልተኝነት ያስተዳድሯት ዘንድ እንደ መፍትሄ ስናቀርብ እኛም እንደማንኛውም ምእመን ቤተ ክርስትያኗ ለአንድም ሰንበት እንኳን ቢሆን እንዳትዘጋ ካለን ቁርጥ ፍላጎት በመነሳት ሲሆን ለዚህም ተፈጻሚነት ሁሉንም ወገኖች በእመቤታችን ስም እንጠይቃለን። ይህም የመፍትሄ ሀሳብ እውን እንዲሆን በኛ በኩል ከምኞት አልፎ ትብብር ባስፈለገበት ሁሉ እንገኛለን።
ነገር ግን ይሄንን የመፍትሄ አማራጭ በእንቢተኝነት ባለመቀበል ቤተ ክርስትያኗ የመዘጋት አደጋ ቢያገጥማት እንቢተኛው ወገን ሙሉ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ እና በታሪክም ዘንድ ተጠያቂ እንደሚሆን እናስገነዝባለን።
በማጠቃለያም በዲሲ ያለን የጋራ ግብረ ሃይል አባላት ከሌሎች አገር ወዳዶች ጋር በመሆን ያለንበትን ሀገር ህግ በማክበር ህሊናችን ያመነበትን እውነት ባደባባይ ለመመስከር የምናስፈቅደው አካል ወይም የምንፈራው ሃይል እንደሌለ ከዚህ በፊት ያሳየነው ተግባር ይገልጻል፤ የአቋማችንንም ገለጣ ስንደመድም ስለ ሰላም፣ ስለ እርቅ በመዘመር ነው፤ ታዲያ ግብዝ ጉልበትን መከታ አድርጎ በትእቢት ታጅሎ ስለ ሰላም ቢያወሩ እኔ የመረጥኩልህን እሬት ተጋት ቢሉት በሮ በሮ ሜዳቆ ዘላ ምድር እንዳይሆን ፣ ሆድንም በጎመን ቢደልሉ ጉልበት በዳገት ይለግማልና ስለሚሆን ከአጉል ስሜት ተገርተን የዛሬውን ሳይሆን የነገውን አሻቅበን በመመልከት ለግል ስሜት ሳይሆን የሺ ዘመናት እድሜ ያላትን ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በማየት ገፋ ሲልም ለወያኔን እኩይ አካሄድ በር ሳይከፍት ቤተ ክርስቲያናችንን እንድናፀና ከፈለግን ነገ ሳይሆን ዛሬ ዛሬ ሳይሆን አሁኑኑ ወደ መፍትሄው እንሂድ እንላለን።
ከግል ክብርና ጥቅም በፊት የሀይማኖታችን ክብር እና የቤተ ክርስትያኗ ደህንነት ይጠበቅ!!!

ከዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል የእምነቱ ተከታዮች    [email protected]

54 Comments on “ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል የተሰጠ የአቋም መግለጫ የተሰጠ የአቋም መግለጫ”

  1. የተስፋዬ መቆያ ቡድን በያንዳንዱ የዲሲ ማርያም ደጋፊዎች ላይ ያደረገው ወያኔው ዘመቻ አይደልም። የዘመቻ ዓይነት:-ስድብ፣ ማስፈራራት፣ በባልና በሚስት ላይ መዝመት፣ ስም ማጥፋት፣ ዉሸት ማውራት፣ አስመሳይ አማኝ መምሰል፣አጋዢ መሰል ከቤተክርስቲያን ውጭ ሰው መቅጠር ወ.ዘ.ተ.

  2. አሁን የተስፋዬ መቆያ ወታደሮች ዘመቻቸውን ይቀጥላሉ። የዉሸት መርዛቸውን መርጨታቸውን እንደሚቀጥሉ እንጠብቃለን።

  3. የእነ አባባ ማሙሽ ግብረሃይል እውነቱን የሚያውቅ ሕዝብ እንጂ ማንም በግድ የተያዘ ህዝብ የለም በወር ውስጥ በገንዘብ ተገዝታችሁ መጥታችሁ ልደባደብ ያላችሁት እናንተ በቁርባን ሰአት ስትጮሁ የነበራችሁት እናንተ ቤተክርስትያን እስከነጭምው ያስቆማችሁ እናንተ ከወያኔ የበለጠ ግፍ የሰራችሁ እናንተ ምመናኑ ተበደልኩ ሲል አልተበደልክም እኛ እናውቅልሃል ያላችሁት እናንተ እስከነ መግለጫችሁ ገደል ግቡ

  4. የተበላሸውን ለማስተካከል
    በዶክተር አክሊሉ የሚመራው የጥፋት ቡድን በፍርድ ቤቱ ሂደት ላይ ማጣፊያው አጥሮታል። እነ ዶክተር አክሊሉ በሰሩት break-in (ሰብሮ የመግባት) ወንጀል ተከሰው ተመጣጣኙን ቅጣት የሚቀበሉበት ቀን እሩቅ አይደለም። እኔ የምመክራቸው ግን የሚበየንባቸው ቅጣት ተፈጻሚ እንዳይሆንባቸው ከአሁኑ ተሸናፊነታቸውንና አጥፊነታቸውን ተገንዝበው፣ የሚከተሉት 13 ነጥቦችን ያዘለ ስምምነት ፈርመው የቤተክርስቲያኗ ህጋዊ የባለአደራዎች ቦርድ ይቅርታ በመጠየቅ በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ ማመልከቻ ማቅረብ ነው።
    1) አባላት ላይ በማን አለብኝነት የጫኑትን ህገወጥ “ጊዜያዊ አስተዳድር” ማፍረስ
    2) በአስተዳደራዊ ጥፋት የተወገዱ ካህናትን ለመመለስ ያደረጉትን ህገወጥ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ማቆም
    3) በዝሙት ምክንያት ተወገዘው ክህነታቸውን ከተገፈፉና እንዲሁም በዝሙት ምክንያት ከክህነት አገልግሎት የተባረሩ የቀድሞ ካህናትና መምህራን ላይ የተላለፈባቸውን ውሳኔ ተገዥነታቸውን መግለጽ። እነዚህም ወንድወሰን ኩሩ፣ታደሰ ሲሳይና ህዝቅያስ ማሞ ናቸው።
    4) በር ሰብረው ደብሩን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ የሰበሰቡትን የገንዘብ መጠን በሪፖርት ማሳወቅና ሂሳቡን ከወጭ ቀሪውን ማስረከብና ማወራረድ
    5) ሊቀ ሊቃውንት አወደምህረት ላይ የሰሩትን ህገ ቤተክርስቲያን የጣሰ ወፈ-ግዝት አንስተው
    ምእመናንና ቀሲስ አማረን ይቅርታ እንዲጠይቁ
    6) ቄስ ዘላለም አንተነህ አወደ ምህረት ላይ ቆመው ምእመናንን “ቦርዱ ሶስት መቶ ሽህ ዶላር ከባንክ አውጥቶ ተሰውሯል” ብለው የተናገሩት ውሸት ከአንድ ካህን የማይጠበቅ ስለሆነ ግለሰቡ ንስሐ ገብተው እስኪመለሱ ድረስ ከክህነት አገልግሎት እንዲታገዱ
    7) ቤተከስቲያኒቷ በእምነትና በቀኖና አንድ አይነት ከመሆን ሌላ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ስልጣን እስኪይዝ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ሲኖዶስ ጋር ምንም አይነት የስራ ይፋዊ ግንኙነት እንደሌላት ማስገንዘብ
    8) በደብሯ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አባላት ብቻ በምርጫ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደሚገባቸውና በአባላት መዝገብ ውስጥ ስማቸው የሌለና ክፍያቸውን ያላጠናቀቁ ከውጭ የመጡ በጥባጮች (the mob) በምርጫ ሂደት ላይ ተሳታፊ አለመሆናቸው ማረጋገጥ
    9) የደብሯ አስተዳዳሪና የባለአደራዎች ቦርድ በአስቸኳይ ስራቸውን በተረጋጋና በሰላማዊ መንገድ መጀመር
    10) ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውስጥና በደጀ ሰላም ውስጥ እንዲሁም በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ላይና በአጠቃላይ በደብሯ ዙሪያ ረብሻ፣ አድማና ወረቀት መበተን የተከለከለ መሆኑ
    11) የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ቦርዱ ስራውን ከቀጠለበት በአንድ ወር ውስጥ ማካሄድና እንዲሁም የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁን የቦርድ አባላትን የሚተኩ አዲስ አባላትን ምርጫ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ማድረግ
    12) ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ያለው አባል ምእመን በደብሯ መተዳደሪያ መሰረት አስፈላጊው ምላሽ እንደሚሰጠው
    13) በደብሯ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ዋና ቀስቃሽና አጋፋሪ የነበሩት አቶ አዲሱ አበበ፣ አቶ ታደለ ገብረወልድና ዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ
    ምእመናንን ይቅርታ እንዲጠይቁና በሰሩት ጥፋት ምክንያት ከአባልነታቸው ለሶስት አመታት እንዲታገዱ።

  5. Mr. Sam,

    Nobody pays either anybody to do the right thing. The only one who pays people is those who are not with truth. You are blaming for Gbrehail about Tesfaye Mekoya who is preaching while the holy communion is occurring? In deed, Woyane is paying those acting illegally for now. Some seems to be radicalized by he propaganda machine.

  6. Kedem silem indetenagernaw yehie gudaye
    Ye shabia ena ye ginbot 7 ijje indalebet
    tenagerenal Christian yimenet teketay
    ke Muslimochun degefo selef indiweta
    benesu telalakiwoch Amare ina Asteraye
    be ESAT ina be Netsanet le Ethiopia Radio
    keskesa ina sedeb be Orthodox imenet teketayoch
    lay sifetsem indenebere yimitawek neaw inezih
    ye ginbot 7 bozene homeless sewoch sihonu
    lemiyakahidut serawoch yekis genzeb yemikefelachw
    nachw abzagnawochu kis awlaki lebboch selemehonachew yekerb
    gizew ye Mesfin Bezun TV show mayet yibekal .

  7. የዘመን መቀያየር ሽማግሌ ጠፍቶ ልጅ ወጣቱ ሽማግሌ የሆነበት ወገን በካራ አንገቱ ሲሰላ በአሳት ሲጋይ በአደባባይ ወጥተን ለዚህ ያበቃቸውን እናውግዝ እንፀልይ ሲባል እኛ ጠገር ቤት ያለው ቢዝነስ ይበላሽብናል ካህን መስቀል ማሳለም ሲገባው ለቦክሰ ሲዘጋጅ ካህን ባሕልን ሥነምግባርን ማሰተማር ሲገባው አዛውንትንና ሽማግሌን የሚደበድብ ቡድን ማቋቋም ይሄ እብደት ነወ ወይሰ ጤንነት እግዝአብሔር ልቦና ይስጣችሁ ቤተክርስቲያኖ ከመፍረስና ከመዘጋት አናድናት፡፡

  8. በአካልም በነፍሥም
    በፖለቲካም በቅድሥናም አንድ እንዳንሆን ወያኔ የተባለ ሠይጣን ኢትዬጵያን ካደቆነ የ 24 አመታትን እያተራመሠን ይገኛል ይህ ጠፍቶን አይደለም ወደ አንድ አቅጣጫ እንምጣ አንድ ሆነን ወያኔን እናሥወግድ ወያኔ ድያሥፖራዎችን ለዩ።

  9. A to Getachew yalew lek neaw maregagechaw ke Getachew betach post
    yaderegutin hulrt sewoch asteyayet
    bedemb temelketut yehulgize ye ginbot 7
    mekeskesha neaw lezihe neaw ine Amare
    teleiko yetesetachw alle yeminelew ke jerba Shabiyas allu .

  10. ውሻ በብላበት ቤት ይጮሀል። ይህ የአባቶች መልካም አባባል ነው። ግብረ ኃይል ተብየው በህዝብ ገንዘብ ተገዝቶ በጫቱና በምርቃናው እያገሳ ና በዞረ ድምር ህዝበ ክርስቲያኑን ሰላም ሲነሳ ከርሞ በድጋሚ ይህ
    ያወጣው መግለጫ በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ የእመቤታችን ልጆች በአሮጌው ቦርድ በተለያዩ ጊዜያት በሚሰየመው የቤተስብ አስመራጭ ኮሚቴ ቤተ ሰባዊ ምርጫ በፖስታ እየተካሄደ የእግዚአብሔርን ቤት የጥቂቶች መፈንጫ ሲሆን ጥያቄ የሚያቀርቡ አባላት ና ካህናት ሲባረሩ ግብረ ኃይል ተብየው የት ነበረ? ሽምግልና ከአንዴም ሁለትዬ አሻፈረኝ ብሎ ያለ አባላት ድጋፍ ቤተ እግዚአብሔር የዘጋው ቦርዱ አሁንም ያለ አባላት ጥያቄ በጥቂት ጥቅመኞች ድጋፍ ወደ ፍርድ ቤት ይሄደው ቦርዱ ታዲያ ምን ይሁን ተብሎ ነው ይህ ሁሉ ድንፋታና ማስፈራራት?
    ቢገባችሁ ሀገሩ የሕግ እንጂ የጉልበት አይደለም። እመቤታችንም ቤቷን እያጸደች ነው ዝም አትልም። ፀረ ማርያም ሁሉ አእምሮ ብትግዛ መልካም መሰለኝ። ሰውን ማታለል ይቻል ይሆናል በእግዚአብሔር ዘንድ ግን አይቻልም። በማታውቁት ድርጊት። ውስጥ በጥቅማ ጥቅም ተደልላችሁ ገብታችሁ ከኑግ የተገኘህ ድሊጥ ….. እንዳትሆኑ!!!

  11. Please stay away from our church. If you gays say you were in a church, why you can not tell the truth? The people (Full of church)are praising GOD peacefully. So, are all of us, except you (about twenty) are forced to worship? Why do you think we give all our money to manage our church? Are we still (as you said) forced to do so? Don’t be ignorant. You better come to the majority and praise GOD. We don’t want your decision or involvement in our church. You proved your self the last three weeks, bothering the service. Do you think it is maturity. If you said you are Christian, you should know about the church service and respect. You guys said a lot about the last Sunday before the church closed that after service the Senbet Temari shout loud, how about you in the middle of the service? Any way, the old board choose to go to the court, and now it is in the hand of them, let the court decide. We are with GOD. Mary is cleaning the church, don’t try to give us your trash opinion (like weyane, tehadesso…), we know everything. We are not kids. There are a lot of intelligent people in the church, don’t disrespect us. Finally, I am advising you to worship the right way. If you say that you are listening the voice, where were you when the old board called for the member meeting and paid for security and ignore members voice and do what ever they want? Anyway let GOD give you knowledge to understand the truth.

  12. አንዲህም ያለ ለህዝብ መብት መቆም የለም፡_
    ሲጀመር አናንተ አምነታችሁ በፖለቲካ አንጂ መቼ በአግዚኣብሄር ሆነና የአናንተው አባሎች አይደሉ ከአንባገነኑ ቦርድ ጋር ተባብረው ቤተመቅደሱን ሲያውኩ የነበሩት፡በሌላ የአምነት ቦታ አናደርገውም ያላችሁትን ትልቅ ድፍረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ለዚያውም የአምነቱ ተከታይ ነን ከሚል መደረግ ነበረበት?ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ስብሀትም ሆነ በረከት ስምኦን ወይም አባይ ወልዱ የሉም፡፡ሰለዚህ የምትቃወሙት ሰውን ሳይሆን አግዚአብሄርንና አመቤታችንን ስለሆነ አቅማችሁን አወቁ፡፡

  13. ያባትዬ ልጆች ሴራው ከሽፎባቸው
    ተመልሰው ሄዱ ወደ ምሽጋቸው
    ሙከራ ያረገችው እመቅደስ ለመግባት
    ባንበሶች ተይዛ ውጪ ወስደው ጣሏት
    ስዳደግ ባለጌ ያልተቆነጠጠች
    በፖሊስ ተይዛ ዘብጥያ ወረደች ፡፡
    ብሶት ያደራጀው የማርያም ሠራዊት
    አስከብሮ ዋለ የወላዲትን ቤት
    ዲያብሎስ ቢልክም ጦሩን አስተባብሮ
    አልተሳካለትም ተመልሷል አፍሮ
    እነመናፍቃን ፀረ ማርያም ሁላ
    በአንበሶች ተገተው ሄዱ ወደኋላ
    ወደ ትፋታቸው ሁሉም ተመልሰው
    ማላዘን ሞከሩ ከደጃፍ ላይ ቆመው
    እቤቱ ቁጭብሎ ያ አስመሳይ ካህን
    ጃስ ብሎ ፈቶ ለቆብን ውሾቹን
    ሊያረክስ ሞክሮ ቤተክርስቲያንን
    እቅዱ ከሸፈ ወደመልን ሰይጣን ፡፡
    ሕፃን አስመስሎ በጋሪ ላይ ጭኖ
    ስፒከሩን በጨርቅ በደንብ ሸፍኖ
    ማስገባት ሲሞክር ተነቃበትና
    ከደጃፍ መለሱት አስገደዱትና ፡፡
    ዛሬም ሆነ ነገም
    ለመናፍቃኖች ምንም ቦታ የለም
    ትላልቅ ሲታዩ ለምድር የከበዱ
    ቀላል ሆነው አየን ተዋርደው ሲሄዱ
    ለሰላም ሳይሰጡ ግምትና ቦታ
    ታውቆ እንደሚመጡ ለሽብር ሁካታ
    የመቤቴ ልጆች ሰልፍ ይዘው በተርታ
    ሴራውን ሲያከሽፉ የላንዳች ኮሽታ
    አድማው ተበተነ በፖሊስ ተፈታ ፡፡
    አወይ ይህች ቀን የተቀደሰች
    የደብረ በጥብጥ አፍ ተዘግታ ዋለች ፡፡
    ተመስገን ተመስገን
    አስጀምሮ ላስጨረሰን

  14. እኔ ለማንም ወገን አልወግንም ምናችውንም በመልክ አላውቅም ግን እናንተ ግብረሀይል ብላችው እራሳችውን የሰየማችው ሰዎች እኔ በበኩሌ ስለማርያም ቤተክርስትያን አይስስ ናችው ብዬ ነው የምለው ምክንያቱም የስጋው ደሙ ክብርን የካዳችው የናቃችው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አይቻልም ማውራት እንካን የምይቻልበትን በማን አለብኝነት በስድብና በግፋ እናንተ ለመሆኑ ምን ይሰማችው ይሆን ደግሞ በህግ ከተያዘ ህግ ይዳኛል ምነው በርጋታ ሆናችው ብትጠባበቁ ለምን እንደዝህ ትሆናላችው የቦርድ አባላት የምባሉትም ብትሆኑ እኮ በደመወዝ የምሰሩት ስራ አይደለም ደመወዛችው ቀረ እንዳንል ምን ብቀርባችው ነው እንደዝህ መሆናችው እባካችው ትዝብት ውስጥ አትግቡ ሌላው ቤተክርስትያን ለማዘጋት የምታደርጉት ጥረት ጥሩ አይደለም አሜሪካ ነው ያለነው የህግ ሀገር እስክ ተረጋጉና ህጉን ጠብቁ በናንተ ያልተሰበሰበውን የማርያም የምጽዋት ገንዘብ እያሰባ ችው አጉል አይወድቁ አወዳደቅ እንዳትወድቁ በጣም ተጨንቃችዋል ተረጋጉ አሁንስ በጣም ያስታውቅባችዋል እውነትም በቤተክርስትያን የምሰበሰብ የምጽዋት ገንዘብ ምን ያህል እንደምታገኙ ከሁነታችው በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

  15. በእለተ ሰንበት በየሥምንቱ እየመጣችው በር ላይ ስትጮሁ ስትድሳደቡ ሁሉም አልተሳካም እኔ ስለናንተ አፈርኩ ፓልሶች እንካን ታዝበዋችው ንቀዋችው ምንም መልስ ሳይሰጣችው አፍራችው ትሄዳላችው እንደዝህ አይነት ክርስትና አለ እንዴ ምድረ ስራ ፈት ምን ታደርጉ ስራ አትሰሩ የማርያም ገንዘብ ነበር ጉዳችውን ሸፍኖ ያለው አሁን ግን የለም አይገኝም ይልቁን ስራ ፈልጋችው ብትሰሩ ይሻላል እስክ ሌላውን ተውት መንዳት የማይችሉ እናቶች አድስ የመጡ ወንድም እና እህቶች በየቀኑ የምማጸኑትን ቤተክርስትያን ለማዘጋት የምታደርጉት ጥረት እግዚአብሔር ብቻ ለናንተ መልሱን ይስጣችው በጎዳና ላይ ቆማችው መዘጋት አለበት የምትሉ ምነው በሀገሩ ላይ የተወሰነ ቤተሰብ ያልዘረፈው ቤተክርስትያን መዘጋት አለበት ያለው ማነው እባካችው አደብ ግዙ።

  16. ግብርሀይል የአማጽው ቡድን ማፈሪያ ወያኔ ነው እንዴ የማርያምን ብር ሰብስቦ በልቶ በዝናብ ያበሰበሰው የእያንዳንዳችው ቤት ምን ይመስላል እስክ በማርያም ምጽዋት ገንዘብ የማርያም ቤተክርስትያን ግን እኔ ያየሁት ዝናብ ያንጠባጥባል ለዝህ መከራከር ነው ክርስትና እንጅ በየበላችውበት እንደውሻ የምትጮሁ ሁሉ ክርስትያን ነኝ ብትሉ አይገባኝም።
    ስንት አመት ሙሉ የተሰበሰበ ገንዘብ በልታችው አንድ ነገር ሳታደርጉ የናንተ ወያኔን መናገር ምን የምሉት ነው ወያኔ ብበላም እየሰራ ነው እናንተ ምን አደረጋችው በሀይማኖት ስም የምትነግዱ ሌባ ዋና የአለም አጭበርባር እናንተ ናችው የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ ማለት እናንተ ናችው አሁን ምን ለመሆን ነው እሔ ሁሉ ጬኸት ለምን ጉዳያችው እስከ ምጣራ አርፋችው አትቀመጡም ለካስ እዝህ ሀገር ካልተሰረቀ ለውጥ የለም የምባለው እውነት ነው ሰዎች ከስርቆታቸው ስታገዱ ልያብዱ ነው።

  17. YE DC majirat mechiwoch
    Sint Dollar tebeteselachuh Seaw American ager iyonere
    Serto menor sichal sirkot min ametaw. Shimeles irasu
    Lebba neaw. AYE Maferiyawoch?

  18. Amare ena Asterye lemindenew
    beyesamentu ke Dimtsachin Yisema
    gar abrew Allahu Akbar yimillut
    hizebe Christianun nikewal
    Awardewal silezih iziaw yamleku .
    Ayedresubin.

  19. Inezih gibere belew yemichohut
    bemullu bozenyewoch wustachew
    Grade 8th yicherese seaw yelebetim Shimeles andu neaw .

  20. ግብረ በላዎች ብትባሉ የሚሻል መሰለኝ፤

    ማፈሪያዎች፣ አሁን የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረባችሁ ነው በናንተ ቤት። እግዚአብሔር ታጋሽ ሆኖ ጊዜ በመስጠቱ የሌለ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሗል።
    ከሁለቱ ተውጣጥተው ያስተዳድሩት የሚለው ሃሳብ ተቀባይነት የማይኖረው፣ አብረው መስሎኝ ሲሰሩ የነበሩትና አብረው ለመስራት የማያስችል ችግር ስላለ እኮ ነው፣ ከብዙ ዓመታት ሽምግልና በሗላ ፈንድቶ ወጥቶ እዚህ ደረጃ የተደረሰው።
    ይህም ሆኖ እያለ ተዉ በምክክር እና ሽምግልና ይፈታ ቢባል፣ በትዕቢት ተሞልታችሁ ወደ ፍርድ ቤት የሄዳችሁት።
    አሁን የፍርድ ቤቱም ጉዳይ እንደማያዋጣ ስትገነዘቡ፣ የግብረ በላ አሸማጋይ ቡድንን ይዛችሁ ብቅ።
    ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ ሲባል አልሰማች ሁም፣ አበቃ እንግዲህ ደግሞ እነዚህን ተራው ይሰጣቸውና ዓመላቸውን እንዪ፣ ጥጋብ ልክ እንደናንተ የተሰማቸው ጊዜ ደግሞ ዋጋቸውን ያገኛሉ።
    አዲስ እስኪ እንሞክር የተሻለ ብናገኝ።
    በግብረ ሃይል ስም የመጣችሁት ሰዎች እነማን እንደሆናችሁ፣ ለየትኛው የፖለቲካ ድርጅት እንደምትሰሩ እናውቃለን፣ በያዛችሁት መስክ እንኳን ውጤት ሳታመጡ ወደዚህ መምጣታችሁ ዕርባና እንደሌላችሁ አንዱ ማረጋገጫ ነው። ለዚያውም ነው አባላት ማፍራት ያቃታችሁ።
    ወያኔ እያላችሁ ሰዎቹን ትወነጅላላችሁ፣ በዚህ ስሌት ከሆነ ታዲያ እናንተስ በፖለቲካው ተወክላችሁ ጣልቃ መግባታችሁ አይደለም ወይ።
    ስለዚህ የመፍትሔ ሃሳቡ ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ማለት ነው። ስለዚህ ዉድቅ ሆኗል በኔ መመዘኛ ።
    ወያኔም ካላችሁ፣ ብዙ አገር ቤት የሚሰራ ስራ ሞልቷልና ይህንን ለኛ ተዉልን፤ ሌሎች ፖለቲከኞችም እዚህ እየመጣችሁ ከምትቸገሩ፣ ይህንን እግዚአብሔር ጋ አቤት ለማለት ለሚመጣው ምዕመን ተዉልን እባካችሁ።

    ቸር ያሰማን እናንተንም ወደልባችሁ ይመልሳችሁ።

  21. 7127757035 cod #702899 ዘወትር ረቡዕ ከ8pm ጀምሮ ያዳምጡ በግሪሳዎች ተከባችሗልና ንቁ በዚህ አጋጣሚ ብትችሉ ቃለ ዓዋዲ የሰበካወንጌል መተዳደሪያ ገዝተው ያንቡና እውነቱን ይረዱ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

  22. መዝሙር 91

    1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

    2 እግዚአብሔርን። አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

    3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

    4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

    5 ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

    6 በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

    7 በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

    8 በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

    9 አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።

    10 ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።

    11 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

    12 እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

    13 በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

    14 በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

    15 ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

    16 ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

  23. በናታቹ የግብርዬ መሪዎች ስንት ነው አማረ የሚከፍላቹ በጣም ነው ለማወቅ የምፈልገው ምናልባት እኔም ከናንተ ጋር ሆ እንድል። እስኪ ንገሩኝ በናትህ ጣሰው ንገረኝ እስኪ አንተ ንገረኝ ቴዲ ወይ ሌሎቻቹ። አስተርአየ ይሆን እንዴ የሚያሽጋቹ። ምናልባት ተሳስቼ ይሆናል አማረ ያልኩት።

  24. ሰይጣን እንደው ስምህን እየቀያየርክ አንዴ በዲስ ግብረ ሀይል አንዴ በአማረ አንዴ በነገደ አንዴ በአስተራየ እበወዘተ ብተ ዙፋን ባደረካቸው በአማረ ልጆች በጳውሎስና በቤተልሔም አማረ በተደጋጋሚ በትቧጥጥ ድንጋይ ብታገለባብጥ የድንግልን ቤት ደብረ ሰላምን እንደሆነ በፍጹም አታገኟትም። በዚህ ሊንክ ላይ ከምትታየው እንስሳ በታች የነዚህን የተጠቀሱትን ሰዎች አስተሳሰብ ከማድረግ ውጪ ምንም የምታመጣው ነገር የለም

    [youtube http://www.youtube.com/watch?v=_MgHBvp1uwk&w=640&h=360%5D

    https://youtu.be/_MgHBvp1uwk

  25. የበቃው በትክክል ነው የሰጠሄው ምሳሌ you are so amazing አድንልቅህ ነኝ ምክንያቱም እራሳቸው ከሰው እነሱ ተረቱ፣ እነሱው ይናደዳሉ በቀን በቀን በየቦታው አቤቱታ አይሉት ድጋፍ ህዝቡን እኛን አዳምጡን እያሉ የሰው ሰላም ይነሳሉ እነሱ ጥቅም ስለቀረባቸው ነው ሌላው ስራውን ጥሎ እነሱን የምከተል ይመስላቸዋል እነዝህ ሰዎች ማበዳቸው ነው በየቦታው ጅንጆሮዋስ በአንድ ቦታ ሆና ነው ማንንም ሳትረብሽ እሳ ትሻላለች ከነሱ ።

  26. YEHIE HULU DEBBA KEHOALA
    Hunew yemisherebt Amare
    Ena Asteraye Ke ESAT
    KETEREGNOCH GAR HUNEW
    BE DIMTSACHIN YISEMA
    POCKET MONEY EYETEKFELACHEW neaw astebabariw kewsu Shimeles
    Neaw.

  27. ዘፍ: ም 6: ቁጥር 5-6
    እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።
    እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።
    ዘፍ: ም 6: ቁጥር 5-6
    እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።
    እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።
    ዘፍ: ም 6: ቁጥር 5-6
    እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።
    እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።

  28. ያልበላችሁን አትከኩ። እናንተ ከወያኔ የባሳችሁ ትዕቢተኞችና አምባገነኖች ናችሁ። የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ የለመዳችሁትን ማጓራት የተቀደሰችው ቤተ ክርስትያናችን ውስጥም ገብታችሁ ሜጋፎን በመጠቀም የቅዳሴውን ሥርዓት አወካችሁ። ፍርድም በቀልም ከእግዚአብሔር ነውና ዋጋችሁን ታገኛላችሁ። እኛ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ቤተ ክርስትያናችንን እንጠብቃለን። እናንተ ማንም ያላወቃችሁ ዘመናዊ አይሲስ ናችሁ። ትንሽ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላችሁ፣ ማስተዋል የተሳናችሁ አድር ባዮች! እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጣችሁ!

  29. ምድረ ግሪሳ ሀራጥቃ ሁሉ ተንጫጫ ስራችሁ ታውቋል ህዝቡን አባላችሁት፣ አወቁ የሚባሉትን ወሰዳችሁ(አሳሳታችሁ) አባቶችን ማዋረድ መሳደብ በባህላችንም የለም ግን በእናንተ ታየ በመግደል፣ በመስደብ ፅድቅ የለም አስርቱን ትእዛዛት አፍርሳችሗልና መቼም እንደማትቀበሉት ባምንም ለመጻፍ እገደዳለሁ ባለፈው እሁድ እህቶችን ወንድሞችን እዚህ ሆነ እንጂ አገር ቤት ቢሆን በገጀራ ነበር የምልሽ ማለት ምን ማለት ነው? ሲጥ ማድረግ ነበር ማለትስ መግደል የማን ስራ ነው? የሰይጣን ቃኤል በአቤል ላይ አድርጏልና እራሳችሁን መርምሩ እመቤታችን ሰውን ገድላችሁ ውደዱኝ አትልም እውነትን ፈልጉ አለበለዚያ ግን ግሪሳ ሁላ ተንጫጫሀሀሀሀሀሀ በሳቅ ።

  30. ስለ እግዚአብሔር ይሁንባችሁ ከቤተ ክርስቲያን ላይ ገለል በሉ። እንቢ ብትሉ ዋጋችሁን ዋጋውን ከሚሰጠው እግዚአብሔር ትቀበላላችሁ። ስለምን ሐሰት ታወራላችሁ!

  31. Yemedaw tigel alhon sil fitachwin wede
    betekristian yazorubet mikeniyat Muslimu
    keigna gar self siweta lemin Christianu
    ayiwetam bemil neaw . lezehem Amare ina
    Asteraye bizu tagellew altesakalachwum
    gebere hailochu ye Shabia ferefari lekamiwoch
    nachew . wend kehonu yimokurna initeyayalen
    arefo beye mall iyozere yisrek LEBBOCH .

  32. የተስፋዬ መቆያ ግሪሳ ሁላ ሀራጢቃ /ተሃድሶ/ ተነቅቶባችሗል ድንግልን ልቀቋት ስድብ የድስተሶ ነው በየስልካችሁ ላይ ፓስት ብታደርጉ እያስመሰላችሁነው የአምደሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ብታድጉ አሁን ግን ተስፋዬ በዘዴ በልችሁ ታላላቆችን እንኳን ያስታሉ ተብሏልና ንቁ በይበልጥም የተሃድሶ ዘዴ እንደሚቀያየር በደንብ ተረድተናል ስም ማጥፋት የሌለ ስምመለጠፍ፣ ለመሆኑ ቦርዱ የበላው ተገኘ እንዴ ? ይዘውትስ የተሰወሩት፣ ቀሲስ አማረ ምንም አላደረጉንም ይመለሱ የተባለውስ? የኑፋቄ ትምህርቱስ ከየት መጣ? አሁን ቀሲስ አማረ ላይ የተላከከው? የቀሲስ አብርሃም ስም ተቀየረ እንዴ እሱ ያስ ረዳችሁ የፍቅር ህብረት ሰንበት ተማሪዎች እነዝናሽ የትሄዱ ቀሲስ አብርሃምን ገትራ ተያዘችው የተዋህዶ ልጅ ያሁኖቹማ እንደከብት ተነዳችሁ በተጮኸበት የምትጮሁ። ክርስትና በልብስ ይመዘን ይመስል ነጭ ብትቀያይሩ ይኒፎርም ብታማርጡ ትርጉም የ ለውም አይተን የታዘብነው ነው። በግቢ ገብርኤል አምደሀይማኖት ያደገ የክህደት ስራን አይከተልም ያርማል ይቃወማል እንጂ እንደ እህቴ የቀድሞዋ አገልጋይ ዝናሽ ያሁኖቹ አመድ ብቻ እነ መምህር ብርሃኑ የአሁኑ ቀሲስ ብርሀኑ ጎበና ያስተማሯቸው እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር ተብለው። ብቻ ልቦና ይስጣችሁ ግድ የለም እኛን እስካባታችን ሴይጣን አይሰስ ሌባ ሌላምሌላም በሉን ይባርካችሁ ። እስከዛሬ 25 አመት ትልቁም ትንሹም በሰይጣን መንፈስ ነብር ይመራ ይተዳደር የነበረው ማለት ነው? ሌላው ስድብ አባቶችን መዝለፍ ከየትኛው ወንጌል ውስጥ ነው የተጻፈው? ሰውንስ ለመግደል መዛት መምታትስ ቀኝህን ቢመታህ ግራህን ስጥ ነው እኮ የሚለው፣ ታላላቆችህን አክብር ፣ አትዋሽ በሀሰት አትመስክር፣ አታመንዝር በጠቅላላው አስርቱ ትእዛዛትን አንብቡ ቃሉ ካላቃጠላችሁ ። ሌላው አታመንዝር ስንቶቻችሁ ናችሁ በቅዱስ ቁርባን አግብታችሁ ፈታችሁ አሁን ከኢትዮጵያ ሚስት ያመጣችሁ ለምሳሌ ዘማሪ ተስፋዬ ረታ ሰላማዊትን ዝሙት ስትሰራ ብትፈታህ አንተ ግን ታገለግላለህ ብለህም አገባህ እረ ቤቱ ይቁጠረው ምን ታደርጉ ታላላቆቻችሁ መንገድ ከፈቱላችሁ ዲ/ን ሕዝቅያስ፣ የቀድሞው ቀሲስ ወንድ ወሰን ፣ አሁን ቆሞስ የሁኑት ታደሰ አግብቶ ወልዶ ዝሙት ሰርቶ ቆሞስ መሆን አዎን ሁሉ ይቻላል በተሃድሶ ይህንን እኮ ነው እናድሰው ስርአቱ ወጉ ይስተካከል የምትሉት ምን ታደርጉ እንደልባችሁ ለመሆን ለዚህም አባ መላኩ(አቡነፋኑኤል) ሹመት እንደልብ ምግባርና ስምን ለመሸፈን ይጠሩበት። ታዲያ ሌላው ቢቀር ቆሞስ ታደሰን ስታከብሩ ስማቸውን ስትጠሩ ምነው የአባታችን ትንሿን የማእረግ ስማቸውን ቀሲስ አማረ ቀሲስ አስተራይ ማለት ከበዳችሁ? ይገርማችሗል እኔ አንድ ተራ የቀድሞ ሰንበት ተማሪ ነኝ ቀሲስም አስተርይ አይደለሁም እሳቸውጋ የእግር ጥፍራችውምጋ አልደርስም ግን የሚሰማኝኝ ጽፌያለሁኝ። ዳንኤል የንዋየቅዱስ ሻጭ እንዴት ብለህ እመቤታችንን እንደተጠጋህ ታው ቃለህ እኛም ቅድስት የቀድሞዋንም እንዴት እንዳስለቀስካት ታዲያ ምን አገኘህ ወንድሜ እንደዛ እሁድ ስትነፋ የዋልከው? መንገሻስ ስንት እህቶችንነው ያስለቀስከው? አሁንማ አልሳካልህ ብሎሃል ገና የአጎትህ እንባ ይጠብቅሃል ገነትስ አንቺ የቀድሞ ህይወትሽን እረሳሽው አባታችን በጸሎት በእመቤታችን አማላጅነት ያሁላ የቤተሰብ ጣጣ የወጣልሽ ውለታውን መክፈያ ይሄ ነው ያውም በስተርጅና እኛ እኮ እናከብርሽ ነበር እስካሁኗ ሰአት ምነው ታዲያ? ( ገነት ፈቃደ)። ሶስናስ ብትሆኚ በጋብቻ ስንት መከራ በልተሻል ምነው አሁን በድለላ ነው እንዴ ያገኘሽው አቅበዘበዘሽ እኔ አንችን ብሆን ተመስገን ብዬ በጸሎት አሳልፈው ነበር ቤቤተከርስቲያን በር ላይ ቆሞ ታላላቆችሽን ከመዝለፍ ለአሁኑ ይብቃኝ ወደልቦናችን እንመለስ ።

  33. Amen እኔ ልጠይቅህ ከ10 ቃላት ቤተክርስትያን ይዘጋ የምለው የቱ ጋር ነው? ማንም ሰው ሐጥያት ብሰራ ለሁሉም የስራውን እከፍለው ዘንድ ዋጋው ከእኔ ዘንድ ነው ይላል አይደል አንተስ ስለሰዎቹ ሀጥያት ማውራትህ እኔ ማነኝ ብለህ እራስህን ጠይቀሀል? ባይሆን ሐይማኖታችን የምያስተምረን ከቤተክርስትያን የራቁትን ማቅረብ ማስተማር መለወጥ ነበር ዛሬ እየተደረገ ያለው ግን ከቤተክርስትያን ማባረር ክርስትና ልያስነሱ ስመጡ እዚህ አንተ ማንሳት አትችልም የግል ቤት ከሆነኮ ቆይታል ዛሬ መቼም ገንዘብ ማያመጣው ነገር የለም ሁሉም ጉድ ወጣ አሁን የምያዋጣው ያለውን ገንዘብ ሰብስቦ ሌላም ባይሰራ እንኳን ያለው ቤተክርስትያን ታድሶልን በሰላም ማምለክ እንድንችል ነው ድሮም ሌባ ስሰርቅ ይስማማል ስካፈል ይጣላል እመቤታችን መቼም ቤታን ታጥራው ለበላተኞችም በላተኛውን ይዘዝባቸው የአሜሪካን ገንዘብ ላባችንን ነው የበሉት።

  34. I don’t think this is your mission.
    Stay away from our church please. This is derogating our right. You are forcing us to be govern and administered by people who do not even follow parliamentary procedure during general meetings. Restrain your self from intervening in our church. I presume you have been created in support of our struggle for democracy and freedom, and now you are running against people’s freedom. You are acting against our patriotic movement. Please stay away and do not creat conflict between our patriotic opposition parties and the people. Your just spilling water over our struggle for freedom democracy and the rule of law. So please stay away from our church. You have the right to come and pray but don’t intervene in our process to clear dictators.
    Thank you in advance for respecting our rights

  35. አቶ ወይ ክርስትና ክል ነህ አዎን እኔም የምለው እያደሳችሗት ነው አንተም ብለሀል ምድረ ግሪሳ ተሃድሶ ሁላ ደግሞ የሰው ሀጥያት ማውራት ማለት ከላይ ሌሎቹ የሰጡት ኮመንት ለአባቶቻችን ቅቤነበር የሚቀቧቸው ማለት ነው እኛ እንሳደብ እንዋሽ ወዘተ ግን እናንተ ምንም አተንፍሱ ማለትነው የያዛችሁት እኛን ግን ልታፍኑን አትችሉም እዛው እንደተደፈነባችሁ ተቀመጡ ግሪሳ ሁላ ተንጫጫ እመቤታችን እንደሆን የውሸታምና ሌባ ሰብሳቢ አትሆንም ። ይቆያል እንጂ እውነቱን ታወጣዋለች እስከዛው ከትስፋዬ መቆያ ጋር እያጭበረበራችሁ ኑሩ።

  36. ከመጋቢ ሃይማኖት ተስፋዬ መቆያ ደጋፊዎች ያቀረቡት አስተያየቶችን ለተመለከተ ሁሉ ይህንን ሊል የሚችል ሰይጣንን የሚጋልበው የወያኔ አማካሪ ያለው ብቻ ነው።

  37. በልሁ በትክክል ብለሃል። ይህ ወያኔአዊ መንፈስ የተቆራኘው ለመሆኑ እስከአሁን የሚሆኑትና የሚፃፉት በትክክል ያሳያሉ። እስከአሁን ያልነቃ ወያኔን ተቃዋሚ ነኝ የሚልና የተስፋዬ መቆያን ቡድን የሚከተል በጊዜ ብነቃ ይሻለዋል።

  38. እኔ እመበተ ማርያምን አደራ የምላት ከሰይጣን አንደበት ጠብቂኝ ነው። የተሰፋዬ መቆያ ደጋፊዎች ከእብደት ያለፈ የዲያብሎስ ባህረ የመሰለ የስድብ ናዳ ብያወርዱብንም የነሱን ባህረ ላለማሳየት ብርታቱን እንዲሰጠን ከልጅሽ ከጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ።

  39. “ሆቼ ጉድ፣ ይገርማል
    አህያ ከጅብ የከርማል” አለ ገጣሚ። ተስፋዬ መቆያና አበሮቹ የተያያዙት ክርስትና ከሆነ በውነት ይገርማል።

  40. I read all the comments above and I have been following the tireless lies, insults, threats, name calling, insult at the level of Satan. Are these people actually the religious people are followers of hired Woayne Cadres doing a satan work among the diaspora church members?

  41. እኔ የምለው ተስፋዬ መቆያ እኮ አንድ ሰው ነው የናንተ ቤተክርስትያኑን እናዘጋለን ማለት ደግሞ ያንን ሁሉ ምእመናን ህልውና ላይ ነው እየተረባረባችውት ያላችውት እባካችው በትናትናው እለት ፓልሶች ልትጸልዩ ከሆነ ትገባላችው ሌሌላ ነገር ግን መግባት አትችሉም ብለው ከደጅ ስመልሱ ምን ይሆን የምሰማችው እነሱ እንካን ለቤተክርስትያናችን ምን ያህል ክብር እንደሰጡ እናንተማ በስጋ ደሙ ሰዐት ትጮሀላችው ትሳደባላችው እኔ የካቶልክ ቤተክርስትያን በቁርባን ጊዜ ያላቸውን ክብር ሳይ እንዴት እንደቀናው ማናችውንም በስም በመልክ አላውቅም ግን የምታደርጉትን ለብዙ ሳምንታት ስከታተል ሀይማኖታዊ ስረዐት የጎደለው ጋጠወጥ በድርጊት ነው ያየሁት አንዳንዴ እነዝህ ሰዎች ፓለትካ ቦታ ያሉ ይመስላቸዋል እንዴ እላለው እንደው ውስጥ ስላለው አዛውንቶች ምንም ሼም አይሰማችውም ስራችው በጣም አሳፋር ሀይማኖታዊ ስረአት የለለው ስለሆነ እባካችው ተቆጠቡ እስከ መቼ በፓልስ ተጠብቀን እንጸልይ በናንተ የተነሳ እግዚአብሔር። መቼም ልብ ይስጣችው ሁላችውም ህፃን አይደላችውም ትልልቅ ሰዎች ናችው የስጋችውን ስታሳድዱ የነፍሳችውን እያጣችው ነው ትናት ግን ቅዱስ ማካኤል ስራውን ሰራ ለአሜሪካን ፓልሶች አጠቃላይ እግዚአብሔር ይባርካቸው ሰላም ሰጡን GOD. BLESS AMERICA

  42. እባካችሁ የሰውን ትታችሁታል ተንሽ እንኴን ፈሪሀ እግዚአብሔር ቢኖራችሁ።የአምላክ ቸርነትና ትእግስት ብዛት የለም ብላችሁ የአሰባችሁ ነው የሚመስለው በጣም ከመጠን ያለፈ መቅደስ መድፈር በዛ ማስተዋል ስለሌላችሁ ነው እንጂ እግዚአብሔር በየእለቱ እያሳያችሁ ነው በትናንትናው እለት እናንተ ቤቱን ለማዘጋት ስተጠሩ እሱ ደግሞ የሀይማኖቱ ተከታይ ያልሆነችው ለክብሩ ጫማዋን አውልቃ ገብታ እውነታውን አይታ ተመለሰች የሰይጣንም ፉከራ ከሸፈ እባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ ትግላችሁ ከቤቱ ባለቤት ከአምላክ ጋር ስለሆነ አትችሉትም ብቻ ይቅር ባይ አምላክ ልቦና ይስጣችሁ።

  43. November 23, 2015

    የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ እውነታ ይህ ነው

    ህዝበ ክርስቲያኑ በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰባሰበው ከንጋቱ 6:00 AM ነበር። እንደ ህዝበ ክርስቲያኑ ነጫጭ የሀገር ልብሱና እንደ አባቶች አልባሳት፤ጥምጥምና ልብሰ ተክህኖ፤ ሁለት ነጫጭ የሰላም ርግብ በሚመስሉ ትላልቅ አውቶቡሶች ሞልቶ ፍርድ ቤቱ ወደ 8:35 AM ደረሰ። በአባቶች መሪነት ህንፃው ውስጥ ገብቶ ሶስት ትላልቅ ክፍሎች ውስጥ የዳኛውን መመርያ ይጠባበቅ ጀመር። በቀሲስ አማረ ካሣዬ በኩል እንደወትሮው የመጡ ሰዎች በግምት 25 ይሞሉ ነበር። ዋናው የፍርድ ቤት ክፍል ውስጥ የቀኙን የመቀምጫ ረድፍ ይዘው የተቀመጡት፤ከቀሲስ አማረ በኩል ሲሆኑ፤ 30 ሰዎች ይሆናሉ። በመሃላቸው ከልጃቸው፤ከሚስታቸው እህት ልጅ፤ከቦርዱ የቀድሞ አባላቶች በስተቀር ሌላ አዲስ ፊት አይታይም። ቀሲስ አማረ፤ሴት ልጃቸው (ባለፈው ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ተጎዳሁ ብላ አምቡላንስ ያስጠራችውና፤ ቤተ ክርስቲያኑን Fire Marshal እንዲዘጋው ስለነበር ሃሳቧ፤ አለመሳካቱን ስታይ፤ በራሷ መኪና እቤቷ የሄደችው)፤ ሰለሞን፤ጥሩንባ በህፃን ልጅ አስመስሎ ስትሮለር ላይ እየገፋ ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ይዞ ይገባውና በኋላም ላይ በፖሊሶች ተይዞ የወጣው፤የሚስታቸው የእህት ልጅ ባል••• ለምስክርነት ስለሚፈለጉ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ተቀምጠዋል። ያ ሁሉ ካህናት በተሰየመበት ክፍል ውስጥ ቀሲስ አማረን አብሮ ማስቀመጥ የህሊና እረፍት መንሳት ስለሆነ የጠበቃቸው ውሳኔ ለቀሲሱ ከመሳቀቅና ከህሊናቸው ጋር እዛ ተቀምጠው ሙግት ከመግባት አድኗቸዋል።

    የፍርዱ ሂደት የተጀመረው አርፍዶ ነው። በመጀመርያ የከሳሽ ጠበቃ ቤተ ክርስቲያን አላስገባ አሉን ብሎ ምስክር እንዲሆነው አንድ የፖሊስ ሰርጀን ለምስክርነት አምጥቶ ነበር። ፖሊሱ ሲጠየቅ፤ በርግጥ አላስገባ ተብለው እንደነበር፤እሱም እንዳይገቡ ከከለከሉት ውስጥ እንዱ እንደነበር፤ እና ጥቂት የሚሆኑ ግለሰቦች በብዛት ቆሞ ይጸልይ የነበረውን ህዝብና ህጻናት በማሰብ አላስገባ እንዳለ ገልጾ፤ ውሳኔው በወቅቱ ትክክል እንደሆነና አሁንም ጸብ ሊነሳ ይችል ይሆናል ብሎ እንደሚያምን አስረድቷል። ፖሊሱ በኛ ጠበቃ ሲጠየቅ፤ህዝቡ ሰላማዊ እንደሆነና፤ አንዲት በነሱ ወገን የሆነች ልጅ ሰው መትታ እስር ቤት እንደገባች መስክሯል። ምስክርነቱ በአጠቃላይ ሲታይ፤ ከነሱ ይልቅ የኛን ሰላማዊነት ያረጋገጠ ይምስላል። የነሱ ጠበቃ ግፊት ግን አሁንም ቤተ ክርስቲያኗን ሰላም የለም ብሎ ለማዘጋት እንደሆነ ግልፅ ነበር!
    ከእረፍት በኋላ ዳኛው በሁለቱም በኩል ያሉት ጠበቃዎች ስምምነት እንዲያደርጉ ጊዜ ቢሰጥም፤ ሊሳካ አልቻለም። በኛ በኩል፤ የነሱ ወገን እስካልረበሹ ድረስ ገብተው ማስቀደስ እንደሚችሉ ቢስማማም፤ የቀሲስ አማረ ካሣዬ ግን መመለስ አሁን ከእምነቱ ጋር ስለሆነ ጥርጥራችን፤ፈፅሞ ተመልሶ ማገልገል እንደማይችል ገልፀውላቸው፤ በነሱ በኩል ያሉት ሁሉ በንዴት አብደው፤ ስምምነቱ በዚህ ፈረሰ! የሚገርመው ነገር፤ ለወራት ሲለመን የነበረው ሰው፤ አሁን የሃይማኖቱም ነገር አጠራጣሪ ሆኖ አረፈው። በህዝቡ ሁሉ እባክህ እየተባለ ይለመን የነበረው ሰው እራሱ ለምኖ እንኳን እምቢ ተባለ! ይህ ታዲያ የሰው አሰራር ነው ትላላችሁ?!

    ስምምነቱ ስለፈረሰ ቀጥታ የገባነው፤ የፀሃፊዋ ‘የወሰን’ መስቀልኛ ጥያቄ ላይ ነበር። የኛ አዲስ ጠበቃ፤ ሴትየዋ እስኪያልባት ድረስ መስቀልኛ ጥያቄ ሲያወርድባት፤ መጨረሻ መልስ አጥታ ጠባቃችን ዳኛውን እንድትመልስ እንዲያስገድዳት ድረስ የጠየቀበት ወቅት ነበር። ጠበቃችን ደጋግሞ ደጋግሞ ይጠይቃት የነበረው፤ ቦርዱ ጊዜውን አሳልፎ ስልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው፤ህገ ደንቡን የሚደነግገውን (2/3 የአባል ቁጥር) መገኘት አለበት የሚለውን የአንቀጽ ክፍል ሳያከብር ነውና እናንተ ህገ ወጥ ናችሁ የሚል ሲሆን። ህገ ወጥ ነን ላለማለት፤1/3 የአባል ቁጥር ብቻ ነው የሚያስፈልገን፤ ህዝቡም በዚህ ተስማምቷል ብላ ድርቅ አለች። 2/3ኛ ሳይገኝ ነው ያጸደቅነው ብላ ለመመለልስ ግን ምላሷ ተሳሰረ። በዚሁ ወደ ቤቱ ለመሄድ የቸኮለው ዳኛ ዳግመኛ አሁንም ለስምምነት እንዲነጋገሩ መክሮ ለ
    ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱን አጠናቀቀ።

    ጠቅላላ ሁኔታውን ስናየው፤ ለኛ በጣም ጥሩ ነበር፤ አሁንም የሚረብሸንን የቤተሰብ መንጋ ሳናስገባ (በአንበሶቹ የወጣቶች ግብረ ሀይል) እዛው በሩ ላይ ተገቶ፤ህዝበ ክርስቲያኑ በሰላም እምነቱን ያኪያሂዳል ማለት ነው። ውስጥ ሳይታይ ገብቶ ከፀሎት ሌላ ሊረብሽ የሚሞክር፤ ወንድም ሆነ ሴት፤ አሮጊትም ሆነ ህፃን፤ የድሮ ዲያቆንም ሆነ አስተዳዳሪ፤ የቀድሞ የቦርድ ፕሬዚዳንትም ሆነ ምክትል፤ ፀሃፊዋም ሆነች፤ገንዘብ ያዥ፤ጥሩምባ ያዥ ሆነ፤ስትሮለር ገፊ፤ለመጮህ ጥርሱን ፍቆ የመጣም ሆነ፤ ያልፋቀ፤ እንደ ረባሽ ህፃን ልጅ፤ ሁለት እጅና ሁለት እግሩ እንደ ወላንሳ ተይዞ ከበር ውጭ ይጣላል። ይህን ሁሉ የምናደርገው ህግን ተከትለን ስለሆነ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ ባለፈው አስተላልፈን ያላከበሩ ምን እንደደረሰባቸው አይታችኋል፤ አሁንም ፖሊሶች የሰጡዋችሁን ማስጠንቀቂያ አስታውሳችሁ፤ አንዳዶቻችሁ የእድሜና የአቅም ጉዳይ ሆኖ ልትረሱ ስለምትችሉ፤ ኢንተርኔት ላይ ገብታችሁ እራሳችሁን አፕዴት አድርጉ፤ ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለውን የአባቶቻችንን መርሆ ተከትላችሁ፤ ብርድ ላይ አፋችሁ ፍሪዝ ከሚያረግ በሰላም ውስጥ ገብታችሁ ተቃቅፈን አብረን እመቤታችንን እናመስግን! በቤተ ክርስቲያናችን እና በእምነታችን ላይ ግን ‘አንበሳው የወጣቶች ግብረ ሀይል’ ዘወትር እንደሚሉት አ ን ደ ራ ደ ር ም !!!

  44. የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ እውነታ ይህ ነው

    November 23, 2015

    ህዝበ ክርስቲያኑ በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰባሰበው ከንጋቱ 6:00 AM ነበር። እንደ ህዝበ ክርስቲያኑ ነጫጭ የሀገር ልብሱና እንደ አባቶች አልባሳት፤ጥምጥምና ልብሰ ተክህኖ፤ ሁለት ነጫጭ የሰላም ርግብ በሚመስሉ ትላልቅ አውቶቡሶች ሞልቶ ፍርድ ቤቱ ወደ 8:35 AM ደረሰ። በአባቶች መሪነት ህንፃው ውስጥ ገብቶ ሶስት ትላልቅ ክፍሎች ውስጥ የዳኛውን መመርያ ይጠባበቅ ጀመር። በቀሲስ አማረ ካሣዬ በኩል እንደወትሮው የመጡ ሰዎች በግምት 35 ይሞሉ ነበር። ዋናው የፍርድ ቤት ክፍል ውስጥ የቀኙን የመቀምጫ ረድፍ ይዘው የተቀመጡት፤ከቀሲስ አማረ በኩል ሲሆኑ፤ 30 ሰዎች ይሆናሉ። በመሃላቸው ከልጃቸው፤ከሚስታቸው እህት ልጅ፤ከቦርዱ የቀድሞ አባላቶች በስተቀር ሌላ አዲስ ፊት አይታይም። ቀሲስ አማረ፤ሴት ልጃቸው (ባለፈው ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ተጎዳሁ ብላ አምቡላንስ ያስጠራችውና፤ ቤተ ክርስቲያኑን Fire Marshal እንዲዘጋው ስለነበር ሃሳቧ፤ አለመሳካቱን ስታይ፤ በራሷ መኪና እቤቷ የሄደችው)፤ ሰለሞን፤ጥሩንባ በህፃን ልጅ አስመስሎ ስትሮለር ላይ እየገፋ ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ይዞ ይገባውና በኋላም ላይ በፖሊሶች ተይዞ የወጣው፤የሚስታቸው የእህት ልጅ ባል••• ለምስክርነት ስለሚፈለጉ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ተቀምጠዋል። ያ ሁሉ ካህናት በተሰየመበት ክፍል ውስጥ ቀሲስ አማረን አብሮ ማስቀመጥ የህሊና እረፍት መንሳት ስለሆነ የጠበቃቸው ውሳኔ ለቀሲሱ ከመሳቀቅና ከህሊናቸው ጋር እዛ ተቀምጠው ሙግት ከመግባት አድኗቸዋል።

    የፍርዱ ሂደት የተጀመረው አርፍዶ ነው። በመጀመርያ የከሳሽ ጠበቃ ቤተ ክርስቲያን አላስገባ አሉን ብሎ ምስክር እንዲሆነው አንድ የፖሊስ ሰርጀን ለምስክርነት አምጥቶ ነበር። ፖሊሱ ሲጠየቅ፤ በርግጥ አላስገባ ተብለው እንደነበር፤እሱም እንዳይገቡ ከከለከሉት ውስጥ እንዱ እንደነበር፤ እና ጥቂት የሚሆኑ ግለሰቦች በብዛት ቆሞ ይጸልይ የነበረውን ህዝብና ህጻናት በማሰብ አላስገባ እንዳለ ገልጾ፤ ውሳኔው በወቅቱ ትክክል እንደሆነና አሁንም ጸብ ሊነሳ ይችል ይሆናል ብሎ እንደሚያምን አስረድቷል። ፖሊሱ በኛ ጠበቃ ሲጠየቅ፤ህዝቡ ሰላማዊ እንደሆነና፤ አንዲት በነሱ ወገን የሆነች ልጅ ሰው መትታ እስር ቤት እንደገባች መስክሯል። ምስክርነቱ በአጠቃላይ ሲታይ፤ ከነሱ ይልቅ የኛን ሰላማዊነት ያረጋገጠ ይምስላል። የነሱ ጠበቃ ግፊት ግን አሁንም ቤተ ክርስቲያኗን ሰላም የለም ብሎ ለማዘጋት እንደሆነ ግልፅ ነበር!

    ከእረፍት በኋላ ዳኛው በሁለቱም በኩል ያሉት ጠበቃዎች ስምምነት እንዲያደርጉ ጊዜ ቢሰጥም፤ ሊሳካ አልቻለም። በኛ በኩል፤ የነሱ ወገን እስካልረበሹ ድረስ ገብተው ማስቀደስ እንደሚችሉ ቢስማማም፤ የቀሲስ አማረ ካሣዬ ግን መመለስ አሁን ከእምነቱ ጋር ስለሆነ ጥርጥራችን፤ፈፅሞ ተመልሶ ማገልገል እንደማይችል ገልፀውላቸው፤ በነሱ በኩል ያሉት ሁሉ በንዴት አብደው፤ ስምምነቱ በዚህ ፈረሰ! የሚገርመው ነገር፤ ለወራት ሲለመን የነበረው ሰው፤ አሁን የሃይማኖቱም ነገር አጠራጣሪ ሆኖ አረፈው። በህዝቡ ሁሉ እባክህ እየተባለ ይለመን የነበረው ሰው እራሱ ለምኖ እንኳን እምቢ ተባለ! ይህ ታዲያ የሰው አሰራር ነው ትላላችሁ?!

    ስምምነቱ ስለፈረሰ ቀጥታ የገባነው፤ የፀሃፊዋ ‘የወሰን’ መስቀልኛ ጥያቄ ላይ ነበር። የኛ አዲስ ጠበቃ፤ ሴትየዋ እስኪያልባት ድረስ መስቀልኛ ጥያቄ ሲያወርድባት፤ መጨረሻ መልስ አጥታ ጠባቃችን ዳኛውን እንድትመልስ እንዲያስገድዳት ድረስ የጠየቀበት ወቅት ነበር። ጠበቃችን ደጋግሞ ደጋግሞ ይጠይቃት የነበረው፤ ቦርዱ ጊዜውን አሳልፎ ስልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው፤ህገ ደንቡን የሚደነግገውን (2/3 የአባል ቁጥር) መገኘት አለበት የሚለውን የአንቀጽ ክፍል ሳያከብር ነውና እናንተ ህገ ወጥ ናችሁ የሚል ሲሆን። ህገ ወጥ ነን ላለማለት፤1/3 የአባል ቁጥር ብቻ ነው የሚያስፈልገን፤ ህዝቡም በዚህ ተስማምቷል ብላ ድርቅ አለች። 2/3ኛ ሳይገኝ ነው ያጸደቅነው ብላ ለመመለልስ ግን ምላሷ ተሳሰረ። በዚሁ ወደ ቤቱ ለመሄድ የቸኮለው ዳኛ ዳግመኛ አሁንም ለስምምነት እንዲነጋገሩ መክሮ ሌላ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱን አጠናቀቀ።

    ጠቅላላ ሁኔታውን ስናየው፤ ለኛ በጣም ጥሩ ነበር፤ አሁንም የሚረብሸንን የቤተሰብ መንጋ ሳናስገባ (በአንበሶቹ የወጣቶች ግብረ ሀይል) እዛው በሩ ላይ ተገቶ፤ህዝበ ክርስቲያኑ በሰላም እምነቱን ያኪያሂዳል ማለት ነው። ውስጥ ሳይታይ ገብቶ ከፀሎት ሌላ ሊረብሽ የሚሞክር፤ ወንድም ሆነ ሴት፤ አሮጊትም ሆነ ህፃን፤ የድሮ ዲያቆንም ሆነ አስተዳዳሪ፤ የቀድሞ የቦርድ ፕሬዚዳንትም ሆነ ምክትል፤ ፀሃፊዋም ሆነች፤ገንዘብ ያዥ፤ጥሩምባ ያዥ ሆነ፤ስትሮለር ገፊ፤ለመጮህ ጥርሱን ፍቆ የመጣም ሆነ፤ ያልፋቀ፤ እንደ ረባሽ ህፃን ልጅ፤ ሁለት እጅና ሁለት እግሩ እንደ ወላንሳ ተይዞ ከበር ውጭ ይጣላል። ይህን ሁሉ የምናደርገው ህግን ተከትለን ስለሆነ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ ባለፈው አስተላልፈን ያላከበሩ ምን እንደደረሰባቸው አይታችኋል፤ አሁንም ፖሊሶች የሰጡዋችሁን ማስጠንቀቂያ አስታውሳችሁ፤ አንዳዶቻችሁ የእድሜና የአቅም ጉዳይ ሆኖ ልትረሱ ስለምትችሉ፤ ኢንተርኔት ላይ ገብታችሁ እራሳችሁን አፕዴት አድርጉ፤ ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለውን የአባቶቻችንን መርሆ ተከትላችሁ፤ ብርድ ላይ አፋችሁ ፍሪዝ ከሚያረግ በሰላም ውስጥ ገብታችሁ ተቃቅፈን አብረን እመቤታችንን እናመስግን! በቤተ ክርስቲያናችን እና በእምነታችን ላይ ግን ‘አንበሳው የወጣቶች ግብረ ሀይል’ ዘወትር እንደሚሉት አ ን ደ ራ ደ ር ም !!!

  45. Memenan በጣም ደስ የምል ነገር ነው እግዚአብሔር ይባርክህ እላለው በቦታው ባልተገኘን ህዝበ ክርስትያን ስም ሁሉ እመቤታችን ሁሉንም ነገር እውነቱን አውጥታ ቤታን ከበዝባዥ አጭበርባር መንጋ ታድን ዘንድ ሁላችንም በጸሎት እንትጋ ። ሌላው ግን በእውነት ነው የምላችው ቄስ አማረ በጣም አሳዘኑኝ ምክንያቱም በኛ እምነት የሐይማኖት አባት ምን ያህል እንደምከበር ሁላችንም እናውቃለን እሳቸው ግን ለስልጣን እና እነኝህ ከጎናቸው ሰይጣን ሆነው ቦርድ በምባል ስም የምጠሩ ሰዎች ስህተት ውስጥ ጨመራቸው በጣም ያሳዝናል እሳቸውም መጥተው በሰላም እንድያገለግሉም ሆነ እንድገለገሉ እመቤታችን ልቦናቸውን ታረጋጋልን በእውነት የተደረገው ነገር በጣም ደስ ይላል ሀይማኖታችን ህልውናችን አካላችን የማንነታችን መገለጫ ነው ሁላችንም እንበርታ እንጠንክር እላለው።

  46. ወይ እኔ ቦርዴ በየዌብ ሳይቱ እናንተው ትጽፋላችው እናንተው ትዋረዳላችው፣ ትከሳላችው ትረታላችው፣ ምስክር ብላችው የወሰዳችውት ፓልስ እናንተው ላይ መሰከረባችው ዘንድሮ መቼም ተዋረዱ ብላችዋል በየቦታው ውርደታችውን ትከናነባላችው ምን አለ የበላችውትን ገንዘብ ሰርታችው የምትከፍሉበት እድሜና ጤና ከፈጣር ብትለምኑ በየሣምንቱ ፓልሶችም እየነገራችው ነው በሰላም ጸሎታችውን አድርጋችው ብትሄዱ ውርደታችው አላበቃ ብሎ እችም አሮጊት ምስክር ተብላ ምላሳ እስከምያልቅ ድርቅ ባትል አሁንስ በቀረብን ሳትሉም አትቀሩም ምክንያቱን ታውቁታላችው ግን ከአመንን በገንዘቡ ይመጡብናል ብላችው ነው እንደዝህ የምትሆኑት ይው ሁሉም በተራ በተራ ከተጠያቂነት አትድኑም ለማንኛውም ለቤተክርስትያና ሰላም ስጡ እስከምቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቸር ይግጠመን።

  47. ለምናገረው ነገር እያስተዋልን ቢሆን ጥሩ ነው ሰዎች ሲጮሁ አብሮ መጮህ ማንነትን ከግምት ውስጥ ይጥላል ዩቲዮብ ሳይ የሺ የምትባል ሴት አይሲስ ናቸው እያለች ትጮሃለቸ በጣም የሚያሳዝን ነው ስሙን የምንጠቀምበትን ቦታ አለማወቅ ስሙ ለድንግል ልጆች የሚሰጥ አይደለም።በጣም የሚገርመው ደገሞ ይቺ ሴት እህቷ ሙታባት ተፅናኚ ስትባል አይ አሁን በርትቼአለሁ የምህር ተስፋሰየን ትምህርት እየተከታተልኩ ተፅናናሁ እያለች ስትመሰክር የነበረች አሁንመምር ተስፋየን ነቃፊና ተሳዳቢ ሆነች።መምህር ተስፋየ ብዙ ፍሬ የአፈሩ የብዙውን ህይወት የቀየሩ አባትም ወንድምም ስለሆኑ የአንቺ አባባል ከምንም አይቆጠር። ለአንቺ ግን በአንዳፍ ሁለት ምላስ አፍ ሲከፈት የራስን ባዶነት ይገልፃል ለሁሉም ይቅር ባይ አምላክ ልቦና ይስጠን።

  48. ይገርማል ግሪሳዬ ተንጫጩ ገና ትንጫጫላችሁ ተስፋዬ አንድ ነው ማለት ያሁላ ተኩላ የማ ውጤት ነው ገና እንደ እንደከብት አሰልፎ ይነዳሗል አሁንም እየተነዳችሁ ነው። ቀድሞም ቢሆን እኮ ቤተክርስቲያኑ አምኖበት መስሎኝ ቋሚ ሰራተኛ የሆነውና ሰንበት ትምህርትቤቱንም የተለቀቀለት አውደምህረቱም ላይ ምንምመጥፎ የሰበከው የለም ግን ውስጥ ውስጡን በስልጣና በደሞዝ ካህናቶቹን አፋጨ እንጂ ይህ ነው የተሃድሶ ሴራና አጀንዳቸው ህዝብ ለህዝብ ማለያየት ሚስትን ከባሏ ወዘተ። ለምን ግራና ቀኝ አትመለከቱም? እውነትን ፈልጉ ነጭ ልብስ በመልበስ ህዝብ በማብዛት ፎቶ በማንሳት ይባስ ብሎ በቤተክርስቲያን ልብሰ ተክህኖ የአለም ፍርድ ቤት ኑና ወረብ ፣ ዝማሬ አቅርቡ የተባለ ይመስል እንደዛ ክብር ማሳጣት ምን ይባላል? ይህ ንቀት ነው ነገ ደግሞ ታቦት ይዛችሁ እንዳትመጡ እሰጋለሁ ምክንያቱም አሁን እያበዳችሁ ነው ። ከሁሉም የገረመኝ ሊቀሊቃውንት ታላቁ አባታችን እንደዛ እድሜያቸውን ለፍተው ይሄን ሁሉ የክህደት የውሸት የስድብ የፋሽን ሾውን መንጋ መምራታቸው ነው የሚያሳዝነው። እግዚያብሄር ያንቃቸው ሌላው በግል ሰርግ ላይ ያውም በቅዱስ ጋብቻ ሰርግ የማይገኙት አባት ፍርድ ቤት ከናንተ ጋር ካፍቴሪያ መጋፋታቸው እፍረት ለሴት ልጃቸውና ለወንዱ ልጃቸው የ7 አመት ምክራቸውን አየነው ። ትዳር የሌላቸው ስራ የላቸውም እንበል እንደ ፅጌና እንዬ አይነቱ ሴተ ገበዝ እዩኝ ያሉት ባለትዳሮቹም ብትሆኑ የሰው ባል ያገባችሁ፣ የሰው ሚስት የቀማችሁ፣ አገር ቤት እየጠበቋችሁ እዚህ መርጣችሁ የምታገቡ(ዲ/ን ተመስገን) መሪጌታ ግርማም እንዲሁ እናኮ ባጠቃላይ ህግን የተላለፋችሁ ምናለበት በማለት የምትጏዙ እኮ ናችሁ አዜብ ዲኮርስ ብትሆን የሰው ባል ቀምታም አይደል እንዴ ከማርያም የጠፋችው? እረ እባካችሁ እራሳችንን እንመርምር መፅዳት ከራስ ነው ከእኔ ጀምሮ የሰው ጉድፍ ከማውጣት የሰውን ማነት ያልሆኑትን ናቸው በማለታችሁ ነው የነካካሗችሁ እራሳችሁ ጀመራችሁት ስለዚህ ልብ ግዙ የትም አያስኬድም ። ዶክተር አክሊሉስ የሳመር ቤታቸውን ዘንድሮ ምነው ዘግተው ቁጭ አሉ የ17 አመቱ የቦርድ ብር በአንድ ፍሎሪዳ ቤት ብቻ አበቃ? ነውስ የጡረታ ብራቸው አልበቃአላቸው እንዴ? ለነገሩ ወያኔና ተሃድሶ ተዝቆ የማያልቅ እንዳፈሰሰ ያደባባይ ሚስጥር ነው ግን ሳይ በሉት እንዳይሸውዱብቻ ። ፍርድ ቤትም ቢሆን ጥያቄው ብሩ በፍርድ ቤት እያለቀ ነው ነበር። ገንዘብ የሰይጣን ስለሆነ የታዘብነው ነው: አሁን ደግሞ ለቅድስት አርሴማ በአል የአበሻ ልብስ አሰፉ የሚል ማስታወቂያ አነበብኩ ምንድነው ነገሩ የካንፓኒ ዩኒፎርም ነውወይስ መንፈሳዊ ተቋም? በጣም የሚያሳዝን ነው ነውስ ትርኢት ወይንም እንደኢሰፓ የመለያ ምልክት ነው? ምናልባት እነ ቢልልኝ ማንደፍሮ የመከሩት ነው? ብቻ የዱባይ ሚካኤል ከሀዲዎች እጣ እንዳይደርስባችሁ እሰጋለሁኝ ልጆቻቸውን ትዳራቸውን እርግፍ አድርገው የነበጋሻው ደንገጡሮች እንደሆኑት እንዳትሁኑ አሁንማ መለኩሲት እናቶችን ሁሉ ነው እየተነዳችሁት ያላችሁት ከዚህ ይሰውረን። ሌላው ህፃናት ልጆችን የእናንተ መጥፋት አንሶ ንፁህ ህፃናት ልጆችን እየመረዛችሗቸው ነው ያላችሁት /አማርኛ ቋንቋና ሃይማኖት የሚማሩትን/ ዩቱብ ላይ ብታወጡ ቆራርጣችሁ ለጣጥፋችሁ ብታወጡ እውነትን ገና አላገኛችሗትም ይልቅ ልቦናችሁን መልሱ ልባችሁን እጠቡት ልብሳችሁን ሳይሆን ስድብ ውሸት አይላከክም እናንተ ግን በነጭ ልብስ ተደለሉ።

  49. አይ እነ ዮዲት ጉዲት ምነው ቤተክርስቲያን መዝረፍ ቀረ አይደል ሙዳዮን ምፅዋት ስታዮ ለቅሶ ትጀምራላችሁ ያ በጡት መወሸቅ ቀረ ።ስለሰው ስትቀባጥሩ ከምትኖሩ ህገ ቤተክርስቲያንን ያፈረሱ በሚስታቸው ላይ ሲማግጡ ትዳራቸውን ያፈረሱ እንደ ፍሬው አይነቱን ቦርድ አድርጋችሁ ዲያቆን አላችሁን እነትጓደድን ሲያንጓድዱ የሚያድሩትን እንደነአለምሸት ያሉትን። እነፖስተር ዘነበች በሱሪ ተወጥረው እርጅናቸውን እረስተው የሰኞ ትምህርትን ሲካፈሉ የነበረው ትምህርት ፍለጋ አልነበረም ለካ አይ መዋረዳቸው ባል ስለሌላቸው እንደነአለም እሸት ለመጣል ነበር አላማቸው ። የወንጌሉ አርበኞ አልሰናከል ቢላቸው ተሀድሶ ነው አሉ ባይሳካላቸው ። ተሀድሶ እማ ሴት ቤተመቅደስ እንድትገባ የሰደደው አስተርአያና በ
    ቡችሎቹ ናችሁ ።

  50. አይ እነ ገንዘብ ጣኦታቸው ምነው ቤተክርስቲያን መዝረፍ ቀረ አይደል ሙዳዮን ምፅዋት ስታዮ ለቅሶ ትጀምራላችሁ ያ በጡት መወሸቅ ቀረ ።ስለሰው ስትቀባጥሩ ከምትኖሩ ህገ ቤተክርስቲያንን ያፈረሱ በሚስታቸው ላይ ሲማግጡ ትዳራቸውን ያፈረሱ እንደ ፍሬው አይነቱን ቦርድ አድርጋችሁ ዲያቆን አላችሁን እነትጓደድን ሲያንጓድዱ የሚያድሩትን እንደነአለምሸት ያሉትን። እነፖስተር ዘነበች በሱሪ ተወጥረው እርጅናቸውን እረስተው የሰኞ ትምህርትን ሲካፈሉ የነበረው ትምህርት ፍለጋ አልነበረም ለካ አይ መዋረዳቸው ባል ስለሌላቸው እንደነአለም እሸት ለመጣል ነበር አላማቸው ። የወንጌሉ አርበኞ አልሰናከል ቢላቸው ተሀድሶ ነው አሉ ባይሳካላቸው ። ተሀድሶ እማ ሴት ቤተመቅደስ እንድትገባ የሰደደው አስተርአያና በ
    ቡችሎቹ ናችሁ ።ተሀድሶማ ከተወገዘ ጋር የሚሰራ ነው። አይ የጨለመባችሁ ይህ የነጭ ልብስ ነገር ቅጥል ድብን አደረጋችሁ ገና እንለብሳለን አምረን ደምቀን ታየንበት አደለ ወይ ቅናት እኞን የእጁን ስራ ፍርድቤት ስታቆሙን ያልተሰማችሁ እናት ፈሪሳውያን ወገኞች ስለወጋችሁ የሸማኔ የእጅ ስራ አቃጠላችሁ አይ ግብዞች ፈሪሳውያን ። አይገርማችሁም አዎ ለቅድስት አርሴማ ደምቀን የምንታይበት እናተን ግብግብ ያላችሁበትን የሸማኔ የእጁ ስራ የሆነውን ነጭ ልብስ ልናሰፋ ነው አይናችሁ ቀላ በገዛ ገንዘባችን አይ የዲያብሎስ ፍሬዎች ገና ለብቻችሁ ስታወሩ እናያችኋለን መቼም ዲያብሎሰ አባታችሁ መጨረሻው ያ ስለሆነ በናተ ላይ ያለው አላማ። በሉ መቼም አንዴ አብዳችኋል እበዱ አልላችሁም እንደነ መበለትዋ ሐረጓ ጥቅም ስለቀረባች በአደባባይ እንደአበደ ውሻ እየጮሁ ስትወጡ ታያችሁ ወይ ዶላር !!!!! አይ ወሰን የለሽ ጉድዋን ልትደብቅ ስትቀበጣጥር ዱቄት የላሰች መስላ ዋለች በምድራዊ ዳኞ ፊት ያጀብዋት እነስንዝሮ እነስም አይጠሬ ያ የዘረፉት ዶላር ሚስጥሩ ሲወጣ ስለታያቸው ከፍርድቤቱ መውጣት ሞት መስሎ ታያቸው።እኞ በነጭ አሸብርቀን እግዚአብሔር በዝማሬ እያመሰገንን ድል ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ እያልን በልበ ሙሉነት ተመለስን ወደ ደብረ ሰላማችን ።

  51. አይ ቄስ ሃይሉ ጉድ ገና ይወጣል ወርቁ የት ገባ? ተሃድሶ እንደሆን ብር አይጠግብም ለዚሁ ነበር በስማቸው ጨዋ መሳይ በሸንጎ ቤተክርስቲያን የተበጠበጠው ? ገና ተስፋዬ ከነንበጋሻው ጉባኤቀላቅሎ ዳንኪራ ባያስጨፍራችሁ ለወንጌል ሳይሆን ለንዋይየሞታችሁ ቦርዱማ አላቀምስም አለ ምን ትሆኑ ግን የህይወት ወርቅ በዚህ መሀል እየጠፋ መሆኑን አልተገነዘባችሁም ሀራጥቃ ሁላ እውነት ትወጣለች ገና እስከዛው በተስፋዬ ፈረስ ጋልቡ ።

  52. ይህን ያውቁ ኖሯል? እኛም ዝም አንልም!

    ወ/ሮ ነገደ ግርማ የአማረ ሚስት ወይም ባላንጣ አይታወቅም፤ ወ/ሪት ጽጌሬዳ የምትባለውን ሴት መጀመርያ ከአማሪቾ ጋር ጠርጥራት እቤቷ እንዳትመጣ ስትነግራት፤ ቢሮው ውስጥ እየመጣች ስላስቸገረቻት፤እነ ታደሰ፤ሃረገወይን፤ወሰን••• ባሉበት ነገደ የአማሪቾ ቢሮ ድረስ መጥታ ቦታውን ቀውጢ አደረገችው! ፅጌሬዳንም እንደገና ከቢሮው ውስጥ አባራ ድራሿን አጠፋቻት! ለዚህም ብዙ ታዛቢዎች ቢኖሩም ለሚሰራው ብልግና አንድም ሰው አማሪቾን ተው ያለው፤ ወይም ሰለብልግናው ቦታውን እንዳረከሰ፤ለተቀሩት አባቶች ቀርቦ የተናገረ አለመኖሩ እጅግ በጣም ቢያሳዝንም፤ መጨረሻ ‘ እኔና አንተ ብቻ የምናውቀው የአህዛብ ሀጢአት መቅደሴ ውስጥ ሰርተሃል’ ብሎ እግዚአብሔር እስኪያባርረው ድረስ በሀላፊነት ላይ አለን የሚሉ ግለሰቦች ለጥቅማቸው ሲሉ ዝም ብለው ማየታቸው በሰውም በፈጣሪም ዘንድ የሚያስጠይቃቸው ነው! አሁንም እነ ታደሰም ሆኑ ሌሎቹ፤ ለአባቶች ቀርበው ቢናዘዙ መልካም ነው።
    ይህች ፅጌሬዳ የምትባል ሴትም ብትሆን አባቶች ዘንድ ቀረባ ንስሃ ብትገባ መልካም ነው! ሁሉን ይቅር የሚል ጌታ ይቅር ያላታልን ወደ ልቦናዋ ተመልሳና ተፀፅታ ምህረትን እንድታገኝ የእርሱ ፈቃድ ይሁን።
    ይህ ይሉኝታ እና ሽንግልና ግን ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዳግመኛ ሊታይ አይገባውም! አማሪቾ ከመጀመርያው እነ ታደሰም ሆኑ እነ ወሰን፤ እነ ሀረገወይንም ሆኑ እነ አለምእሸት••• የሚሰራው ስራ ትክክል አይደለም ቢሉ ኖሮ እዚህ ችግር ላይ ቤተ ክርስቲያኗም ሆነ አማሪቾ አይደርሱም ነበር። ሆኖም የራሳቸውም አኗኗር ከአማሪቾ የተሻለ ስላልሆነ ሀጢአቱ አይታያቸውም፤ ሊያውም ፅድቅ ሆኖ ሳይታያቸው ይቀራል ብላችሁ ነው?!
    ድንግል በተአምሯ ከቤቷ ከአባረረችው በኋላ ሁላችንንም እንደምናየው አማሪቾ እንደ እብድ ሲቀበጣጥር እያየነው ነው።
    ቤተ ክርስቲያን አርክሶ፤ ባረክሁ፤
    ህዝበ ክርስቲያኑን አባሮ፤ አበዛሁ፤
    ገንዘቧን አጥፍቶ፤ ሚሊዮን ሰበሰብሁ፤
    ቅጥሯን አፍርሶ፡ የውሃ መጠራቀሚያ አድርጓት፤ ቤተ ክርስቲያኗን ገነባሁ፤
    እያለ በአይን የሚታየውን ‘እውነት’ ሁሉ፤ እየካደን ነው።
    እቅዱ ሁሉ አልሰራ ስላለው፤አንደኛውን እንደ ጓደኛውና ቅጥረኛው፤ እብዱ ሽመልስ፤ ማጉያ ይዞ መንገድ ላይ ሳይለፈልፍ የሚቀር አይመስለኝም። በቅርብ የለቀቀው ቪዲዮ የሰራ አልመሰለኝም!!!
    እነዚህ የሃሰት ምስክሮችስ እሱን ከማዋረድ በስተቀር ምን ይጠቅሙኛል ብሎ ነው የሚያስለፈልፋቸው? አለምእሸት ሚስቱን ፈቶ ቤተ መቅደስ ገብቶ መቀደሱ ነው ለአማሪቾ ውለታ ሆኖበት እንዲመሰክርለት ያደረገው? አማሪቾ እንደዚህ በማድረጉ ፍርፍት አላጎረሰህም፤ ገሃነም እንድትገባ ነው በሩን የከፈተልህ! ሳትውል ሳታድር ንስሃ ግባ! የእመቤታችንን ማደርያ ስታረክስ ኖረሀልና ሀጢአትህን ተናዘዝ። ጅላ ጅሌ ማሞ ቂሌ ስለሆንክ ይህን ታደርጋለህ ብዬ ባላስብም፤ ምክሬን ግን ከመለገስ ወደ ኋላ አልልም። አማሪቾ በመጨረሻው ቀን ስትጠየቅ፤ እንኳን ላንተ ለራሷ መልስ የላትም። አውደ ምህረት ላይ የጮኸችውን፤ መብራት ያጠፋችውን፤ በር የዘጋችውን፤ የውሸት ቪድዮ የለቀቀችውን፤ከማይረቡ የሴት መንጋ መሃል ገብታ አባቶችን ሰድባ ያሰደበችውን•••ሁሉ ምላሷ እየተንቀጠቀጠ ስትመልስ፤አለምእሸት ብትባል ‘ኸረ እኔ ፈፅሞ አላውቀውም’ ነው የምትለው!
    ሁሌ የሚገርመኝ፤ በእኛ የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሴት ጉባኤ አትመራም፤ ይህች እንደ ጤነኛ ሳይሆን እንደ ተለከፈ አጋንንት፤ የምትለፈልፈውን፤ መያዣና መጨበጫ የሌለውን ወሬ የምታዘንበውን፤ አማሪቾን እንደ ህፃን ልጅ ተናገር፤ አትናገር እያለች፤ የምታዘውን፤ ሲፈልጋት እንደ ጴንጤ ሼህ ሲያሻት እንደ ሴተኛ አዳሪ አሽከለሌ የምትወርደውን ሟርተኛ ሴት፤ አምሪቾ እራሱ ላይ ዘግቶ ከወጣ በኋላ በርሮ ሴትየዋ ጉያ ገብቶ አልወጣ ማለቱ የጤና ነው ትላላችሁ? ‘አባታችን በፀሎት ይክፈቱልን’ ብላ፤ አማሪቾም እንደታዘዘችው ከፍታ፤ ዝናቧም የድፍረትና የስድብ ኑዛዜዋን አዝናባ፤አባቶችን ሁሉ ሰድባ፤ ምዕመናኑን ሁሉ አዋርዳ፤ ቤተ ክርስቲይኗን ሁሉ በስድብ ፀበሏ ረጭታ፤ ‘አባታችን በፀሎት ይዝጉ’ ስትል፤ አማሪቾ ካልተኛች፤ ወይም ካለችበት ተፈልጋ መጥታ እሺ ታዛዥ ነኝ ብላ፤ ሊጠፋት አንድ እሁድ የቀረውን የመዝጊይ ፀሎት በእንቅልፍ በተጣበቀ አፏ አድበስብሳ ትዘጋለች። አሰዳቢ•••ይህ ነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያስተማረህ?! ይህ ነው የ27 አመት ትምህርት?! ይህን ነው አባቶች ያስተማሩህ ቀኖና?! በእውነት የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንተን ‘መናፍቅ ‘ ሲሉ ያዳላሉ፤ አንተ በቁምህ የምትለብሰው ልብስና ቆብህ ተነጥቆ፤ ሁለተኛ የኦርቶዶክስን ልብሰ ተክህኖ በእጅህ እንዳትነካ ተደርጎ፤ ወያኔን በኦባማ በኩል ሀገር እንድትገባ አስፈቅዶ፤ እራቁትህን እስከምትሞት ድረስ በዝዋይ ባህር መሀል በምትገኝ ገዳም፤ አምልጠህ ብትወጣም ውሃ እንዲበላህ፤አባቶችን እያገለገልክ እንድትኖር ነበር መገዘት የነበረባቸው፤ ይህን ማዳላታቸውን ግን ያቁሙ!
    ኸረ ለመሆኑ ‘ግዝት’ ምን እንደሆነ ታውቃለክ? አባቶቻችን እኮ ‘ግዝትን’ ያንተ መጫወቻ ለማስደረግ አይደለም ያመጡት? አይ መሃይም! ቅዳሴውን አጥርተህ አታውቅ ግዝቱ ላይ ተንጠለጠልክ! ያንተን ሀጢአትና ወንጀል በህዝብ ዘንድ እንዳይገለጥ የቤተ ክርስቲያናችን አይን የሆኑ ወጣቶችን፤ በግዝት ለማቆም መሞከርህ፤ የሚያስደንቅ ዘዴ ነው! ግን በሰውም ዘንድ፤ በአማላካችንም ዘንድ ሞገሥን አላገኘም፤ እንዲያውም በድፍረትህ ተገርሞ አንተኑ ከላይ ገዝቶህ ይኸው ውጭ ቆመህ እንደ ጓደኛህ ትዘባርቃለህ። የኛ ወጣት ልጆችማ በሚያስደንቅ የእግዚአብሔር ፀጋና ሞገስ ተሞልተው አንተ ያረከስከውን የእመቤታችንን ማደርያ ከካህናቱና ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር በሽበሸባ፤ በምስጋናና እና በእልልታ እየቀደሱት ይገኛሉ!
    የጥጋብህ ጥጋብ፤ በቪዲዮህ ላይ እራስህን ከክርስቶስ እና ከሙሴ ጋር ታመሳስል ጀመር?! ወይ ያንተ መሃይምነት እና ድፍረት ወሰን አጣ እኮ! አንተ መመሳል ያለብህ

    ከእብዱ ሽመልስ ጋር፤በጩኸታችሁና በመሃይምነታችሁ
    ከወሰን ጋር፤ በተንኮላችሁ
    ከእብዱ ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ጋር በተግባራችሁ
    ከውለታ ቢሷ ጋር በሌብነታችሁ
    ከዳንኤል አሸናፊ እና ቀዳዳው ሽመልስ ጋር በውሸታችሁ
    ከቀድሞው ዲ/ን አለምሸት ጋር በጩኸታችሁ•••
    እኔ የምፈራው ነገ ተነስተህ ‘መሲህ’ ነኝ እንዳትል ነው። ደሞ አውጅና ጅዎቹ ገነጣጥለው ነው የሚበሉህ። አንተንም፤ ሚስትህንም፤ ልጆችህንም፤ ቢበሉልን፤ ለዲዘርት ደግሞ የሀረገወይን ባልን ቢጨምሩልን ትንሽ እርፍ እንል ነበር። ሀረግወይን እንኳን ለዲዘርት አትሆንም ለሜይን ኮርስ እንጂ!
    ሌሎቹን እንደ ምንም ብለን እብዱ ሽመልስ እንዲባላቸው እንከፍለው ነበር። ያው አንተ የምትሰጠውን $200 መክፈል ነው፤ እኔ ውለታ እና ዶ/ሩን ለማስበላት $500 እሰጣለሁ ብያለሁ! ኸረ ምንም ችግር የለ፤ አንድ እሁድ የምንሰበስበው እነሱንም ሌላውንም ይሸፍናል!!!

    በመጨረሻ ሳልመክርህ ፅሁፌን ባቆም ስለምትቀየም፤ ይሉኝታና ሽንግልና የሌለበትን ምክሬን ልለግስህ፤
    1 መናጢ ደሃ ሆነህ መጥተህ በእመቤታችን ፀጋና ቸርነት አምረህ ከብደህ ነበር፤ ለዘመናት የሰራኸውን ሀጢአትና በደል ይቅር እንድትባል አባቶችን ቀርበህ ይርዱህ፤
    2 ብዙዎቹ ስላንተ መጥፋት እያሰቡና እየተጨነቁ ነው፤ ግብዝነትህን አቁመህ ምክራቸውን፤ ፀሎታቸውን ተቀብለህ ጊዜ ሳይጨልብህ ተቀላቀል!
    3 የሰራኸውን አስነዋሪና አፀያፊ ስራ ይቅር እንዲልህ ተንበርክከህ እግዚአብሔርን ተማፀን።
    4 ለዚህ ፈተናና ችግር ከዳረጉህ ሴቶችና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳትል ራቅ። ገና መሬቱን ሲምሱልህ ተነግሮህ ነበር አልሰማህም፤ አሁንም አፈር እያለበሱህ ነው፤ ጨርሰው ሳይቀብሩህ በፊት ነፍስህን አድን። ያንተ ድንፋታ ድሮም ሆነ አሁን አልጠቀመህም።
    ያንተ እውነት፤ የታወረ ነው፤ የሚሄድበትንም አያውቅም!
    በትዕቢት የተሞላ ነው፤አይረባም፤
    በውሸት የተሞላ ነው፤ እውነት የለበትም፥
    ህዝብን የሚለያይ ነው፤ ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ለወገን አይጠቅምም!

    ኮሌጅ ያለችው ልጄንም እንዲህ አልመከርኳትም! አንተን በየጊዜው መምከር ድካም ነው የሆነብኝ! በሉ ሁላችንንም ቸር ይግጠመን፤ አንተም ያንተ የሆኑትም ክፉ አይንካችሁ፤ መጥታችሁ ግን አትበጥብጡን፤ምን አሁንማ ውጭውን ነው የምትጮሁበት፤ አይ የኔ ነገር፤ እረስቼው ነው እኮ። ለመሆኑ ብርዱ እንዴት እያረጋችሁ ነው? አቤት ውስጥ ያለው ሙቀቱ፤ እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ!

    በሌላ ፕሮግራም እስከምንገናኝ ለዛሬ ይብቃኝ፤ አሊቨደርቼ•••

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*