የፓሪስ ጥቃት ፈጻሚዎች አንዱ ታወቀ::የአንዱ ቤተሰቦች ተይዘዋል::የተጠቀሙበት መኪናም ተገኝቷል::
#Parisattacks : የፓሪስ ጥቃት ፈጻሚዎች አንዱ ታወቀ::የአንዱ ቤተሰቦች ተይዘዋል::የተጠቀሙበት መኪናም ተገኝቷል::
የፈረንሳይ ባለስልጣናት እንዳሉት በፓሪስ ግድያ ከፈጸሙት አንዱ የሆነውና መሳሪያ ታጥቆ ጥቃት ሲያደር ነበር ያለውን ግለሰብ ማንነቱን ማወቁን ይፋ አድርገዋል
::በወቅቱ በሙዚቃ ድግሱ አከባቢ የነበሩትን ምርመራዎች ተከታትሎ ደረስኩበት ያለው ግለሰብ ሶሪያዊው የ29 አመቱ ኦመር መህመድ ነው::የተጠቀመበት መኪናም በቁጥጥር ስር ውላለች::
ይህ 89 ሰዎች ከተገደሉበት ቦታ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ሽብሩን ካቀናበሩት እና ከፈጸሙት አሸባሪዎች አንዱ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉት አቃቢ ሕግ ይናገራሉ::ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቃቱን ከፈጸሙን አንዱ ቤተሰቦቹ በፖሊስ እጅ መግባታቸው ሲታወቅ አስፈላጊው ምርመራ ተጀምሮባቸዋል::በፓሪስ ከተማዋ ዳርቻ የሚኖሩት ፈረንሳይ ውስጥ የተወለዱ እንደሆነ ቢነገርም ማንነታቸው አልታወቀም::ለጊዜው ምርመራ ላይ ስለሆኑ ዝርዝር ጉዳዩን ለመናገር ፖሊስ ፈቃደኛ አልሆነም::የቤልጄም ፖሊሶችን ከዚሁ ጥቃት ጋር ተያያዥነት አላቸው ያሏቸውን ሰዎች ሁሉ ሰብስበው በማሰር ልይ ይገኛሉ::
