ልማት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ ልማት ነኝ! ዕድገት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ እድገት ነኝ!

ልማት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ ልማት ነኝ! ዕድገት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ እድገት ነኝ! Yohanes Molla

ወገን በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ፥ እነሱ የስልጣን ዘመናቸውን ላጠናቀቁ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በ150 ሚሊዮን ብር ወጪ 6 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እየገነቡ፥ ከ50 ዓመት በላይ፣ በሶስት የመንግስት ለውጦች፣ “ከብዙ ደንበኛ በሚገኝ ሽያጭ ትንሽ ትርፍ ማግኘት እንጂ ከጥቂት ብዙ ማትረፍ አይደለም” በሚለው የአባታቸው መርህ መሰረት፥ በጽናትና በታማኝነት ቆሞ ምርጥ ኬኮችን በቅናሽ ዋጋ ሲያቀርብ የኖረውን፥ እንደ ቅርስ ሊንከባከቡት የሚገባውን ባለውለታ በላይ ተክሉ ኬክ ቤትን ማፍረስ ነውር ነው።

[በነገራችን ላይ “ላለው ይጨመራል” ካልሆነ በቀር፥ ግንባታውን በየትኛውም ዓይነት መለኪያ የምስማማበት ጉዳይ አይደለም። ይህን ዜና ስሰማ፥ መጀመሪያ ትዝ ያለኝ ለድርጅታቸው መኖሪያ ቤታቸውን በስጦታ ያበረከቱ ባለስልጣን ናቸው። መቼም ባለስልጣኑ አንድ የመኖሪያ ህንጻ ለድርጅታቸው ሲያበረክቱ፣ እሳቸው ቢያንስ ሌላ የመኖሪያ ህንጻ አላቸው ማለት ነው። ግን እንኳን ሁለቱን አንዱንስ ከየት አመጡት?? 10,000 ብር በማይሞላ ደመወዛቸው ገንብተውት ነበር? በየሁኔታው የሚያደርጓቸው ውድ ስጦታዎችስ ከየት የመጡ ናቸው?]

ልማት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ ልማት ነኝ! ዕድገት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ እድገት ነኝ!

በላይ ተክሉ ኬክ ቤት፥ ቢያንስ የከተማን ረኀብ በማስታገስ ረገድ የተጫወተውን ሚና ያየውና የኖረበት ብቻ ነው የሚያውቀው። በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ብዙ ዓለም አይተናል። በልጅነት የሆያ ሆዬ ብር ስንካፈል ሮጠን በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ተሰይመናል። የእሁድ መዋያ ሲሰጠን አጠራቅመን በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ከቤተሰብ ተደብቀን በልተናል። ከቤት ከትልልቅ ሰዎች ጋር ስንወጣ በላይ ተክሉ ኬክ ቤትን ባልዋለችበትም ፈልገናት ተቅበዝብዘናል። በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ስብርባሪ ኬክ በነጻ ተሰጥቶን በልተናል።

ጎርመስ ስንል ኬክ በመደጋገም ግዙ በበላ ቁማር ተጫውተናል። በወጣትነት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ፍቅረኛችንን ይዘን ሄደን ተዝናንተናል። በጉልምስና በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ሄደን ምሳና ቁርስን ሸውደናል። በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ውስጥ ታሪክና ትዝታችን ተመዝዞ አያልቅም።

በላይ ተክሉን ማንሳቴ፥ የማፍረስና የመገንባት ነገር እዚህና እዚያ መሆኑን ለማሳየት ነው።

“ሕዝብን መርዳት፣ ብዙኃኑን መጥቀም ከሁሉ የበለጠ ቀደምት ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት ታላቅ ስህተት ነው። ስለዚህ ሁሉ መንግስት መሠረቱና ዓላማው ለሕዝብ አገልግሎት መሆን አለበት። በሕዝብ ያልተደገፈ፣ ለሕዝብ ያልቆመ መንግስት መሰረት የለውምና ዘላቂ ሊሆን አይችልም፤ ጠፊ ነው።” – ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም “ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)”

5 Comments on “ልማት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ ልማት ነኝ! ዕድገት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ እድገት ነኝ!”

  1. መቼ ቀን ነው ስለ ልማት በጎ አስበሕ የምታውቀው? ያንተ ልማት ጦርነት፣ደም፣መከራ ፣ስቃይ አይደል እንዴ ዛሬ ምነው ምን ተገኘ “ልማት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ ልማት ነኝ! ዕድገት እንዲህ ከሆነ፥ አዎ ጸረ እድገት ነኝ!” ለመሆኑ መቼ ነው ስለ እድገት አውርተሕ የምታውቀው? አባቶችሕ ዘረኝነት፣ጥላቻ፣ፀብ አስተማሩህ በእርግጥ ልክ ነሕ አንተም እንደመሰከርከው በፍርፋሪ ማደግሕ ለዛሬው ሕይወትሕ ተጽእኖ እንዳለው አውቃለሁ፡፡ ግን ስንቶች በድህነት አድገው ዛሬ ሃገራቸውን ይገነባሉ፡፡ አንተ ምን ቤት ነሕ አሁን ከሶስት አስርተ ዓመታት በፊት ስለተገተረ ሕንጻ የምተወራው? እንትንህ አይገተር!! ኪኪኪኪኪኪከ ለነገሩ አይምሮሕ በየትኛው የለውጥ ሂደት ታነፀና!!! ዛሬም ለሃገራችን ውድቀት መከራ እየተመኘሕ አንተ ስለ አንድ ፎቅ ብታወራ ምን ያስገርማል? እውቅትህና ጭንቅላትሕ ከፍርፋሪ ኬክ አያልፍም፣

  2. Satenaw- yegna zer (Tigre) eyegeza new kemilew mikniyat
    Besteker, you don’t have any reason to support this dividing rule, hateful and revenge government. When condition going worst and worst. We fear for your zer…

  3. እውነት ኢትዬጵያ ውሥጥ አርክቴክት አለን?

    እሥኪ አውሮፓን ወጣ ብላችሁ እዩ ዘመናዊ ህንፃና እድሜ ጠገብ ህንፃዎች እንዴት ተዛምደው እንደሚገነቡ ለምን ባለሞያን አያማክሩም እውነት በሀይለሥላሤ ዘመን የተሠሩት ህንፃዎች ውበታቸውና ጥንካሬያቸውን ይዘው ይገኛሉ በወያኔ ግዜ ያሉት ግን ለትውልድ የመተላለፍ እድላቸው ከጥራት ጋር ተያይዞ በቂ ፖርኪንግ የሌላቸው መካን ህንፃዎችን በከፍተኛ ሙሥና እያሥገነባ ሀገሪቱ አድጋለች ይሉናል እድገት በሙሥና እንጂ በናተ 11 በመቶ የምትሉት ፈሊጥ ግብርና ኢንደሥትሪውን መምራት አቅቶታል እየተንገራገጨን ነው ገለመሌ መፍትሄ የለውም።

    ነብሣቸውን ይማረውና በላይ ተክሉ ደሥታ በፓርላማ የተከበሩ ኤርትራዊና ኢትዬጵያን ወዳጅ አባትነበሩ ባልሣሣት የመጀመሪያው ኬክ ጋጋሪ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች አሉ ታድያ ይህን ታሪካዊ ቤከሪ ወያኔ ለማፍረሥ ለምን ወደደ ኤርትራዊ ሥለሆኑ ነው ወደሚል ድምዳሜ በግሌ ወሥጃለሁ እንጂ ህንፃውን መልሦ upgrade ማድረግ እጅጉን ቀላል ነው ግን የወያኔ ጅቦች ይህን ቁልፍ ሥፍራ ለማግኘት የማይምሡት ጉድጓድ የለም ።

    ልማቱ ያረጅ የመንግሥት ቤቶችን ሣይሆን ታሪካዊ ህንፃዎችን ማጥፋት ነው አላማቸው

    **********************************************

  4. mnew yesew lj ke enssa yemileyew bastesasebu new yemibalewn saynsawi anegager atrsu hewehat weyani ye ethiopiyan ehzb ende essa eyabala 25 amet yaterefew tlachan new edget fok bemesrat kehone enkan kedngay bewerkm biserut eNa ethiopiyanoch kehulum neger befit yesew ljna neSanetach slehone hwehat yemibal nekersa metfat alebet beterefe hwehat yhnn kik bet lemafres ketenesam ertrawi slehonunew yemilewn ankebelm mknyatum ethiopiya lay betgri sm gub yalut telatochachn kemeles zinawi eske sbhat nega bereket smon endihum hulum zerachn tgri nen yemilu le ertrana letgri motn yemilu yetgrin zer hlwna lemaskeber yeamarana yeoromo enatna abat memot alebachew bemalet amharan ena oromon bezer sileyayu siyatefu tenkol siseru amharan teltew oromon yewededu ymesl huletunm lemekber kankachu and slalhone btwaledum zer masdat alebachu bemil dgaf yezer lhikanochn enkan lezerachew lerasachw endayhonu bemadreg eyepeweze hwehat banda tetekem enji ertrawiyannma ena and nen telatachun enatefalen bemalet neber gub yalebn bergt new ertrawiyanochm honu hulachnm beza mdr yetefetern kankachn bileyaym demachn and new zerachn and new ato belay teklu ertrawi honew weyani liyafers yefelegew be ergteNnet ertrawi slehonu sayhon weyanin yemikawemu demachew ethiopiyawinetn yemiyashet bemahonachew yhonal weym mnm smit lemayset yezer poletika bota yelachw yhonal weyanima bandawoch eko nachew drom lefashisht etaliya abatochachew ertriyan asalfew yesetu hayleslasi enezih fashishtochn temasnew bezedi ertrawiyanun wede enat agerachew ethiopiya biyasmelsu amhara slehone letkmu sil new bemalet mdre banda ager lebaed eyasalefe lehulachn nekersa lemehon melsew ertriya nesa mewtat alebat bemalet taliyann lemewgat yetederegew yabatochachn tegadlo bemawared ethiopiyawiyan ers bers endibalana ertriya ethiopiya eyetebale enditelalek tederege bandawoch sltan yzew ertriyan neSanet asmelesn bemalet ethiopiyan be tekarani keabatocha yagenechwn nesanetnan le baed asalfew lemestet chalu kebaed gar serten ethiopiyanun nesanetun kalnefegn yetgri zer bebhir bhireseboch sr tkmun ayatam alu yh sirachew zari ke 25 amet behala yesew dem tettew sga beltew fok eyeseru yesekeru bandawoch melsew ertrawiyan shabiyawoch ye ethiopiya telat nachew blun lemehonu wegenochchnn ers bers abaltew ethiopiyan lemafres bezer mannetachew yetechfechefut ena endihum be ethiopiyawinetachew yetechfechfut zigoch beweyani yetebelut ykrna betaliyan yetechfehcefutn begaz terkefkfew yetekatelu abatochachnn anresam kezam balefe eNa ethiopiyanoch be ethiopiyawinetachn tarikachn tetebko yetnt hager teblen nesanetachn yastelalefu be graN mehamed zemen yemotutn ethiopiyanoch anresam enesu motew agerachnn astelalfewal ethiopiyawinetachnn awrsewl weyani zari ye ethiopiya hzboch lay yeseraw bedel endiresana ethiopiyanoch sle ethiopiya yekedeme tarik endaynorachew lemadreg wanawochu motew ahun edmiw be30 akababi yale hzb slehone sle ethiopiya ayawkm sle wedeb aychnekm endafelegen argen lemegzat enchlalen yemil slitm alachew

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*