መንግስት ዳግም የመጅሊስ አመራሮች ማንነት ስለተጋለጠ ህገ-ወጦችን በአዳዲስ ህገወጦች ለመተካት ፍላጎት እንዳለው ፍንጮች እየታየ ነው

የህገወጡን የመጅሊስ ጸሃፊ አቶ አራጋው አሊን ውክልና የጋምቤላ ክልል መጅሊስ ማንሳቱ ታወቀ
መንግስት ዳግም የመጅሊስ አመራሮች ማንነት ስለተጋለጠ ህገ-ወጦችን በአዳዲስ ህገወጦች ለመተካት ፍላጎት እንዳለው ፍንጮች እየታየ ነው
ቢቢኤን ፡- ጥቅምት 27/2008
በፌድራል መጅሊስ ውስጥ እየሰሩ የሚገኙት አቶ አራጋው ከፍተኛ የገንዘብ ዝርፊያ እና ሴቶችን ሃራም ለሆነ ተግባር ሲጠይቁ የነበሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሴቶቹ የቀረበላቸውን የሃራም ጥያቄ እምቢ በማለታቸው ምክኒያት ከስራ ገበታቸው መታገዳቸውን ቢቢኤን ላይ ቀርበው መናገራቸው ይታወቃል፡፡
ይሄው ግለሰብ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከሃጅ ጉዞ መዝረፉን በማስረጃ ጭምር ማጋለጣችን ይታወቃል፡፡ ክልላችንን እያሰደበ ነው ያሉት የጋምቤላ ክልል መጅሊሶች በትላንትናው እለት ጁምአ ከጠዋቱ 3 -6 ሰአት ድረስ ባደረጉት ስብሰባ የአራጋውን ውክልና ማንሳታቸውን በስብሰባቸው ላይ ወስነዋል፡፡
ምንም እንኳን ህገ-ወጡ መጅሊስ በመንግስት ደህንነቶች ና ባለስልጣን የሚዘወር ቢሆንም በደንቡ መሰረት አቶ አራጋው ከፌድራል መጅሊስ ስልጣናቸው ይወርዳሉ፡፡ በምትኩም ለፌድራል መጅሊስ የጋምቤላ ክልል ወኪሉን ይልካል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የህገ-ወጥ መጅሊስ አመራሮች ከአዲስአበባ መጅሊስ ጋር ፍጥጫ ላይ ሲሆኑ የአዲስአበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ዶክተር አህመድ ከልል መጅሊሶችን በማስተባበር ውክልናችንን ሊያስነሳብን ነው በማለት ለፌድራል ጉዳዪች መክሰሳቸው ታውቋል፡፡
ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም በተቀነባበረ ድራማ የነ ኪያርን ቡድን በማንሳት የነ ሙሃመድ አሚንን ቡድን መተካቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ ዘራፊነታቸው እና መጥፎ ስነ-ምግባራቸው እየተጋለጠ በመምጣቱ መንግስት መጅሊሱን በአዳዲስ ህገወጦች ና ስነምግባር የለሾች ለመተካት እየተንቀሳቀሰ ነው ይላሉ የቢቢኤን ምንጮች
ህዝበ ሙስሊሙ የሚፈልጋቸው የመጅሊስ አመራሮች እንዲመረጡለት ያነሳውን ጥያቄ ህወሃት መራሹ መንግስት አሻፈረኝ በማለት ከበፊቶቹ የባሱ የመጅሊስ አመራሮችን በቦታው ላይ በማስቀመጥ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ህዝበ ሙስሊምም ከምንጊዜውም በላይ አንድነቱን በማጠናከር የሚፈልገው ህዝባዊ መጅሊስ እስኪተካለት ድረስ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ታውቋል፡፡ ቢቢኤን ለህዝብ ያልደረሰ የሃዋሳ የመጅሊስ ጉባኤ የድምጽ ማስረጃ የደረሰው ሲሆን በቅርብ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል

Abdurehim Ahmed's photo.