ዛምቢያ በብሄራዊ ደረጃ ለኢኮኖሚ ቀውስ ጾምና ጸሎት የሚከናወንበት ዕለት እንዲሆን አውጃለች፡፡
ዛምቢያ ዛሬ እሁድ በብሄራዊ ደረጃ ጾምና ጸሎት የሚከናወንበት ዕለት እንዲሆን አውጃለች፡፡የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ለኢኮኖሚ ቀውስ ‹‹ጾምና ጸሎት››አዘዋል ቡና ቤቶች ይዘጋሉ የአገሪቱ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ያወጣላቸው ጨዋታዎች ከወዲሁ መሰረዛቸው ለየክለቦቹ ተነግሯል፡፡ዛምቢያ የገንዘብ አቀሟ በመውረዱና ኢኮኖሚዋ በመቃወሱ የአምላክ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገኛል ብላለች፡፡
ፕሬዘዳንት ኤድጋር ሉንጉ ባለፈው ወር አገሪቱ ወደ ውጪ የምትልከው መዳብ ዋጋው በማሽቆልቆሉ የተነሳ የመገበያያ ገንዘባቸው(ኩዋቻ) እጅግ በመውረዱ የጸሎትና የጾም ቀን እንዲታወጅ ጥሪ አስተላልፈው ነበር፡፡
የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ከመናሩም በላይ ለአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጭ የነበረው ካሪባ ሐይቅ የውሃ መጠኑ በመቀነሱ የአሌከትሪክ አቅርቦት እጥረት እያጋጠመው ይገኛል፡፡
‹‹እግዚአብሔር የተአምራት አምላክ በመሆኑ ብንለምነው ሊባርከንና ኩዋቻም ወደ ቀድሞው ጥንካሬው ሊመለስና የምግብ ዋጋም ሊቀንስ ይችላል››የሚሉት የኢንተርናሽናል ፌሎውሺፕ ክሪስቲያን ቸርች ቄስ ሲሞን ቺሃና ናቸው፡፡
ለኤፍፒ ቄሱ በሰጡት አስተያየት ‹‹የእግዚአብሔርን ምህረት ለማግኘት እንጸልይ፡፡ከዚህ ቀደም ይህንን አድርጎ ስለነበር አሁንም ያደርገዋል››ብለዋል፡፡
ከዛምቢያ ህዝብ 85 ከመቶ ያህሉ ክርስቲያን እንደሆነ ይነገራል፡፡የነገው ጸሎት ሉሳካ ውስጥ በሚገኘው የጀግኖቹ (Heroes) ስታዲየም ይከናወናል፡፡
የዛምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነገ ይደረጉ የነበሩ ጨዋታዎችን ማሸጋገሩን ያስታወቀ ሲሆን ቡና ቤቶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በፊት አይከፈቱም ተብሏል፡፡
ተቃዋሚዎች ፕሬዘዳንቱ ያስተላለፉትን የጾምና የጸሎት ጥሪ በመተቸት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በመክተታቸው ይከሷቸዋል፡፡የፋይናንሻል ጉዳዩች ተንታኝ የሆኑት ማምቦ ሃማንዱ ለኤፍፒ ‹‹ፖሊሲዎችን ወጥነት የገደላቸው ማድረግን በማቆም ሁሉንም የኢኮኖሚ መሰረታዊ ነገሮች በተግባር ያውሉና ከዚያ በኋላ መጾምና መጸለይ ይችላሉ››ማለቱ ተዘግቧል፡፡
ላንጉ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ሚካኤል ሳታ ባለፈው አመት በድንገተኛ የልብ ህመም መሞታቸውን ተከትሎ በጥር ወር የፕሬዘዳንትነት መንበሩን መረከባቸው ይታወቃል፡፡