ከነጻነት ትግሉ ጎን በማጎሪያ ካምፕ የታሰሩ የሕሊና እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ትግሉ ይቀጥላል::

ወያኔ ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ብቻ ወደ ወሕኒ የወረወራቸው የዞን ዘጠኝ አባላት ከጅምሩ ነጻ ቢሆንም ነጻ ለቀናል በማለት የተደረገበትን ጫና መቋቋም ስላቃተው ለቀቃቸው እንጂ ፍትህ በወያኔ ኮሮጆ ውስጥ አለች ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው::የተፈቱትን እንኳን ወደ ሰፊው እስር ቤት ተቀላቀላችሁ እያልን ለነጻነት ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን በየማጎሪያ ካምፑ የታሰሩ የሕሊና እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ትግላችንን እና ጫናችንን እንቀጥላለን::

ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ለወገናቸው ያላቸውን ተቆርቋሪነት ስለጻፉ ካለምንም ወንጀል ብሃሰት ክስ በየማጎሪያ ካምፑ ያሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ተመስገን ደሳለኝ ውብሸት እና ሌሎች ጋዤጠኞች የፖለቲካ መሪዎች አንዳርጋቸው ጽጌ እንዱአለም አራጌ ሃብታሙ አያሌው እና የፖለቲካ ጓዶች የመሳሰሉ ጠንካራ የለውጥ ሃይሎች የሃይማኖት ነጻነት ስለጠየቁ በሃሰት ወንጀል ወህኒ የተቆለፈባቸው ኡስታዝ አቡበከር እና የኮሚቴው አባላት እንዲሁም የሕዝቦች መብት ይከበር ስላሉ ብቻ ካለምንም ወንጀላቸው ወደ ወህኒ የተጣሉት መምህራን ተማሪዎች እና ሰራተኞች ገበሬዎች በሙሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ከነጻነት ትግል ጎን ለጎን ለወገኖቻቸን ያለን ድጋፍ ሳናቋርጥ የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል::

ከወያኔ ጋር የተያዘው እልህ አስጨራች ትግል ድሉ እየቀረበ እና እየደረሰ መሆኑን የሚታዩት የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊው መስክ የለውጥ ስኬቶቻችን ያረጋግጣሉ::አምባገነኖች እድሜያቸው አጭር ነው::ከየትም የአለም ሃገራት ያየነው ነገር ቢኖር አምባገነኖች ለጊዜው ሊዘርፉ ሊዋሹ ሊያስሩ እና ሊገሉ ሊያሳድዱ ይችላሉ በዚህ ሁሉ መስዋትነት ላይ የሕዝቦች ነጻነት ይረጋገጣል:: ድል የሕዝብ ነው!!! Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)