የቀድሞ ዴምሕት አባላት በወያኔ ፎቶገጭ ቤት
ነፃነት ዘለቀ

እንደምን ሰነበታችሁ። እንኳን ለአዲሱ ዓመት የ2008 ዓ.ም. ሁለተኛ ወር “ለጥቅምት አንድ አጥንት” በሠላም አደረሳቹ። ጥቅምት ብርዳምና ንፋሳም ነው። ዘንድሮም እንደዛው ነው። የአዲስ አበባ የሰሞኑ ብርድ ሚስት ያሳቅፋል። ግን ስንገናኝ ሠላምታ የማንለዋወጠው ለምንድነው? ብዙ መጣጥጥፍ ጸሐፊዎች ይህን ወግ ልማድ ረስተው በቀጥታ ሊያስተላልፉት ወደሚፈልገጉት ቁም ነገር ይገባሉ – ያበሳጩኛል። “እንዴት ሰነበታችሁ” ማለት ማንን ገደለ?