በዶክተር አክሊሉ የሚመራው ቡድን በህገወጥ መንገድ የተቆጣጠረውን  ቤተክርስቲያን ለቆ እንዲወጣ ተፈረደበት

በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የምትገኘውን ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን ወያኔ በሚቆጣጠረው ሲኖዶስ ስር በቀጥታ ለማስገባት ስውር አጀንዳ አሸምቀው የተለያየ ምክንያት በመስጠት ምዕመንና በማወክና በማወናበድ ሲበጠብጡ የነበሩ ግለሰቦች በዛሬው ዕለት ሰብርው ገብተው የያዙትን ቤተክርስቲያን ለቀው እንዲወጡ የተበየነባቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። (የተቆለፈውን የቤተክርስቲያኗን በር ሰብረው መግባታቸውን የዘገብንበትን ዜና ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) http://www.mereja.com/amharic/468218

በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ መሪነትና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦችና በተለያየ አስተዳደራዊ ጥፋት ከቤተክርስቲያን የተባረሩና ስር የሰደደ የግል ቁጭትና ምቀኝነት ያለባቸው እንደ ቀሲስ አብርሐም ሐብተስላሴን የመሰሉ ግለሰቦችንም እንደሚያጠቃልሉ የደብሩ አባል ምዕመናን አስታውቀውናል። ከእነዚህ በጥባጮች ጀርባ በመሆን በስልታዊ መንገድ አውደ ምህረት ላይ ለረዥም ዓመታት በማስተማር ከምዕመናን ጋር ግንኙነት ያላቸውና በስውር ከወያኔ ሹሞች ከአባ መላኩ (ፋኑኤል) የጠበቀ ግንኑነትና ተጠሪነት ያላቸው ቤተክርስቲያኗን ከውስጥ ሆነው ለራሳቸው ገንዘብ ማደለቢያነት ሲጠቀሙ የነበሩ እነ መምህር ተስፋዬ መቆያም እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ አዲሱ አበበ፣ዶክተር አክሊሉ ሐብቴና አንዳንድ የደርግ መንግስት ከፍተኛ ባለስጣኖች የነበሩና ወያኔን ፈርተው ለረዥም ዓመታት  ኢትዮጵያ ለመሄድ  ያልቻሉ እንዲፈቀድላቸው  ከወያኔ ጋር ለመታረቂያ ቤተክርስቲያኗን በገጸ በረከትነት ለማቅረብ በብጥበጣውና በረብሻው ሂደት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል። ህጋዊውን የባለአደራዎች ቦርድ በአድማና በረብሻ አውርደናል በማለት ታላቅ የህግ ጥሰት የፈጸሙት ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ካላቸው የስራ ልምድና የእድሜ ተሞክሮ አኳያ “እንደ ገለባ ቀለሉ” በማለት በርካታ ምዕመና እንደሚናገሩ ለመረዳት ችለናል። ከዚህም በተጨማሪ የዶክተር አክሊሉ በበላይነት የሚመሩት ይህ ቡድን የቤተከርስቲያኑን  ዘማሪዎችን በአደንዣዝ  ቅስቀሳ ናላቸውን በማዞር አውደ ምሕረትን እንዲዳፈሩ ማስድረጋቸውንና ይህንን ጥፋት ለማስቆም የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ አማረ ወጣቶቹን ቢገዝቷቸውም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና በጣሰ መንገድ ሌላው ካህን ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ግዝቱን እዛው ሽሬያለሁ ብለው ለበጥበጮቹ የሰጡት ሽፋን ከክህነት አገልግሎት የሚያስፍቃቸውና የሚያስወግዛቸው እንደሆነ እየተነገረ  ነው።

ከዚህም በላይ አንዳንድ ሁኔታውን በጥልቀት የሚከታተሉ ምዕመናን እንደሚናገሩት ከሆነ በደብሯ ውስጥ ለተነሳው አድማና ብጥበጣ ተጨማሪ ምክንያት የሆነው የደብሩ አስተዳዳሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ላይ በወያኔ የሚደርሰውን ግድያ፣ እስርና ሰቆቃ ማጋለጣቸውና ይህ እንዲቆም ፈጣሪን መለመናቸው እንዲሁም ቤተክርስቲያን ከተበደለውና መከራ ከሚወርድበት ጋር እንጂ ከአራጆችና ከኣሳሪዎች ጋር መቆም እንደሌለባት ማስተማራቸው በድብሯ ውስጥ የተሰገሰጉትን የወያኔ ጆሮ ጠቢዎችና ወሬ ለቃቃሚዎችን እንቅልፍ እንደነሳ ታውቋል። በተለይም ለሊቢያ ሰማዕታት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ በዋሽንግተን ሞኑመንት የተደረገው ዝግጅት የወያኔን የውስጥ አርበኞች በእንደዚህ ዓይነት መድረክ ላይ ቤተክርስቲኗ መሳተፏ “ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው” በማለት ቤተከርስቲያኗ ስራዋ የሆነውን ለተጠቁትንና ለተበደሉት መከራከሯንና መጸለይዋን በማጥላላት ሲተናነቋት መክረማችው የሚታወቅ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰን ጥቆማ መሠረት ባለፈው ዕሁድ አውደ ምህረት ላይ በመቆም “የባለአደራዎች ቦርድ  አባላት የሆኑ ስድስት ሰዎች $300,000 ከባንክ አውጥተው ተሰውረዋል” በማለት ትልቅ ውሸትና ቅጥፈት የተናገረው ዘላለም የተባለው ቄስ አውደ ምህረቱ ላይ በምዕመናን ፊት በመዋሸቱ ከካህንነት አገልግሎት መታገድና አስፈላጊው ቀኖና ሊሰጠው እንደሚገባ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል። እሱ ተሰውረዋል ያላቸው የቦርድ አባላት በዛው ቀን ከህግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን የፍርድ ቤት መጥሪያ ለሱና ለመሰሎቹ ሲያሰጡ መዋላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ቄስ ዘላላም ከሽመገለ ክህነት ከአቡነ ማቲያስ ያገኘ ቢሆንም ይህ ዓይነት ወራዳ ስራው ለቅስና አገልግሎት ብቃት የሌለው መሆኑ ያረጋግጣል የሚሉም አሉ። በዚሁ ዛሬ ስለተሰጠው ፍርድና ስለደብሯ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃዎችን አጠናቅረን እናቀርባን።