ኢህአዴግ ያቋቋመው መንግስት መፍትሄ አይሰጥም ::

ኢህአዴግ ያቋቋመው መንግስት መፍትሄ አይሰጥም ተባለ:: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለው ረሃብ የገዥው ፓርቲን ፖሊሲ ውድቀት ያሳያል ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ፡፡ኢህአዴግ ያቋቋመዉ አምባገነን መንግስት ለኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ ሊሰጥ አይችልም ሲል ታቃዋሚዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታወቀ።የ2007ቱን የምርጫ ሂደት የተቹት አመራሮቹ ህግ ወጥ የሆነ ነገር እየተንከባለለ መጥቶ መንግሥት ምስረታ ላይ ደርሷል ብላል።

በተያያዘ ዜናም የፊታትን ቅዳሜና እሁድ በጠቅላይ ሚንስትር ደሳለኝ ኃይለማሪያም ሰብሳቢነት የሚካሄደው የእድገትና የለውጥ ሽግግር እቅድ ስብሰባ ላይ ቢጋበዙም የማይገኙ መሆናቸውን የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየገለጹ ነው።መድረክ የሰጠዉን መግለጫ የተከታተለው እስክንድር ፍሬዉ ተከታዮን ዘግቧል። ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።
http://amharic.voanews.com/audio/2997488.html

 

14 Comments on “ኢህአዴግ ያቋቋመው መንግስት መፍትሄ አይሰጥም ::”

  1. ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል።አየ ጉድ ! ! ! ! ኢሃድግ የምትይው ምኑን ነው ? ? ኢሃድግ እኮ አባይን ሲሻገሩ ይለበሱት ማደናደሪያ ነው።ለምንድን ነው tplf የማትያቸው ? ? ኢትዮጵያ የምታሰሪው ቤት አለሽ ? ? እነሱ ራሳቸው የሚኮሩበትን ስም ወያኔ ብለሽ ባለመጥራትሽ የሚቀየሙብሽ ይመስለኛል።የኢትዮጵያ መንግስት እያለ ሰው አፉን ሞልቶ ሲናገር ጉድ ይሰኛል ! ! ! የአንድ አገር መንግስት ኑ እና አገሬን በዘር፥በቁኣንቁኣ፥በሃይማኖት •••።ወዘተ ከፋፍሉልኝ ብሎ United Nation ን ይጋብዛል ? ? የሚያስተዳድረው አገርስ በጎረቤት አገር ሲወረር ሄዶ በወራሪው አገር ጎን ተሰልፎ ከባዕድ ወታደር ጋር ተሰልፎ የራሱን ሕዝብ የሚወጋ ነው መንግስት ተብሎ የሚጠራው ? ? የጎንደርን ሕዝብ ከሱዳን ወታደር ጎን ሁነው ቁም ስቅሉን እያሳዩት አይደለም ? ? right now as we speak.የኢትዮጵያ መንግስት•••• እኔ በግሌ አልሞትኩም ብየ አልዋሽም።25ኛው የሙት ዓመቴን እያከበርኩ ነው።እስቲ ይሁን እንቆዝም ! ! ! ለመሆኑስ አርበኞችግንቦት ሰባት ጩኽቴን እየስማ ንው ? ? መዋጮየስ ደርሶታል ? ?

  2. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ለማጥመድ መሞከር…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*