ከዝንጅብል ጥቅሞች በጥቂቱ

Fresh, dried and powdered ginger
በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም

1) ሕመም የመከላከል አቅምን ይጨምራል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዝንጅብል ሕመም የመከላከል አቅምን ከመጨመር ባለፈ ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡
2) የደም ዝውውርን ይጨምራል
የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ ለልብ ሕመም፤ለስትሮክ እና ለደም ግፊት ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡ እንዲሁም የኮሌስትሮል መጠንንም ይቀንሳል፡፡
3) የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል
ማቅለሽለሽን ከማስታገስ ጥቅም ያለው ዝንጅብል ለምግብ መፈጨትና የሆድ ሕመምን ለማስታገስ ይጠቅማል፡፡
4) ሕመምን ያስታግሳል
በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሠቱ ሕመሞችንና እብጠቶችን ይቀንሳል፡፡ለመገጣጠሚያ ላይ ሕመም፤ለአስም፤ለራስ ምታት፤ለማይግሬን ለጉንፋን እና ለጉሮሮ ሕመም ዝንጅብልን በመጠቀም ሕመምን ማስታገስ ይቻላል፡፡

Source: Honeliat.com