ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !

የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ። ጋዜጠኛ ግሩም ላለፉት

Samuel Abebe Mekonnen's photo.

ሶስት ቀናት ሲታደን መቆየቱን የጠቁሙኝ ምንጮች ዛሬ ማለዳ በፖሊስ
ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውልኛል !


የጋዘጠኛ ግሩም መታሰር እንደሰማሁ ወደ የመን ስልክ በመደዎል ያነጋገርኳት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ በየነንየጋዜጠኛ ግሩምን መታሰር አረጋግጣልኛለች ።ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ከዚሁ ጋር አያይዛ ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት ” ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎችስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ ” የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።


በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተውበማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያንየስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ “የሞት ጉዞ ” የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም !


(ምንጭ ነብዩ ሲራክ)