በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ የሚመሩት ጋጠወጦች የተዘጋ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገቡ

 

 

... ) apologized to terrified homeowner for <b>breaking</b> <b>into</b> wrong <b>house</b>

በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በምትገኘው ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክስቲያን ውስጥ በእነ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ የሚመራው ህገወጥ ቡድን (mob) ተቆልፎ የነበረውን በር ሰብረው በመግባት ቤተክርስቲያኑን በዛሬው ዕለት መቆጣጠራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህንን የውንብድና ድርጊት በመምራት ላይ ያሉት ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ መሆናቸውም ብዙ ምዕመናንን እያነጋገረና እያስገረመ ይገኛል። ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ቤተክርስቲያኑን ሰብረው ከግብረ አበሮቻቸው ጋር ከገቡ በኋላ በስፍራው ተጠርቶ ለነበረው የፖሊስ ኃይል “የቦርድ ሊቀመንበር እኔ ነኝ” ብለው  የሀሰት መረጃ ሲሰጡ እንደነበር  ተጠቁሟል። አንዳንዶችም  እንደዚህ ዓይነት የህግ ጥሰት ጨለማን ተገን በማድረግ ሲፈጽሙ በመታየታቸው አበዱ ወይ እስከማለት የደረሱ መኖራቸውንም ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ችለናል።

በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ መሪነትና በጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ተባባሪነት  ባለፈው ዕሁድ  ቤተክርስቲያን ውስጥ የተነሳው እረብሻና ብጥብጥ ተባብሶ በምዕመናን ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል የደብሩ ባለአደራዎች ቦርድ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ለጊዜው ቤተክርስቲያኑ እንዲዘጋ መወሰኑንን መዘገባችን ይታወሳል።የቤተክርስቲያኑ ቦርድ በበጥባጮች ምክንያት የተፈጠረው አደገኛ ሁኔታ እስኪበርድና ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ እንዲሁም የምዕመናን ደህንነትና ሰላም ለማስጠበቅ ለጊዜው ቤተክርስቲያኑ እንዲዘጋ መወሰኑ በሳል እርምጃ መሆኑ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢና አካባቢ አስፈላጊው ክብር ሊሰጠው የሚገባና በደብሩ አስተዳደር ፍቃድ ያልተሰጣቸው የተለያየ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች የብሶት መወጫና የጦርነት አውድማ ሊያደጉት የሚገባ አለመሆኑንን በርካታ ታዛቢዎች ይናገራሉ። በዚህ ቀጣይና በፍጥነት በሚለዋወጥ ጉዳይ ላይ የሚደርሱንን ዜናዎች  ከስር ከስር ስለምናቀርብ እንድትከታተሉን እናሳስባለን።