የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት ጉባዬ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ::
Najib Mohammed = ጉባኤው የተሳካ ነበር ጥረታችን ይቀጥላል!
እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው በሃያሉ ፈጣሪ አሏህ ስም
ከተቋቋመ ከአንድ አመት በሗላ የመጀመሪያያዉን ጉባኤ ያደረገዉ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት ከፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን፣ ከሪሣላ ኢንተርናሽናልና፣ ከኦሮሞ ሙስሊም ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር September 20, 2015 ያዘጋጀዉ ጉባኤ በብዙ መስፈርት የተሳካ እንደነበር ከተሳታፊዎችና ከታዛቢዎች አስተያየት መገኘቱ የበለጠ ጠንክረን እንሰራ ዘንድ ብርታት ሆኖናል።
በትላንትናዉ ጉባኤ የመድረኩ ፈርጥ ሆነዉ ያመሹት የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የአለምአቀፍ ጉዳዮች ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ዶክተር አወል ቃሲም አሎና ዶክተር አባድር ኢብራሒም ብቃት እንዳለዉ ሙያተኛና እንደ አንድ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አካል በመሆን የፈጠሩት መነቃቃት ተስፋ የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለወጣቱ ትዉልድ አርዓያ የሚሆን ነዉ። የህዝበ ሙስሊሞን ወኪሎች ጉዳይ ለማጥናት በነጻ (Pro bono) ለማገልገል ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘችዋ ጠበቃ አምበር ሙሪ እንደ ሙያተኛ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ከመላዉ ታዳሚ ጋር ቤተሰብ የሆነችበትን ሁናቴ ተመልክተናል።
ወጣቱ የህግ ባለሙያ አብዱሰላም (የደስደስ) ያሲን እየደመቀ ያለኮከብ ወጣት መሆኑን አስመስክሯል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ የምንጋራዉ መሬትን ብቻ ሳይሆን ደምን መሆኑን በመግለጽ በርቱእ አንደብቱ አስርድቶናል። ወጣቱ ገጣሚ ቦና ሙሐመድ ያላደረግነዉን ልናደርገዉ የሚገባ ቁም ነገርን አሳስቦናል። እዉቁ ዳኢ ሰይፈል ኢስላም፣ የሪሳላ ኢንተርናሽናል ተወካይ ጣሃ ሰመሩ፣ የኦሮሞ ሙስሊም ፋዉንዴሽን ተወካይ አቶ ሙሐመድ ቡሽራ፣ ከህብረቱ አቶ ኡመር ሽፋዉና የቢቢኤን ሬድዮ ተወካዮች ያስተላለፉት መልክት በሙሉ የምንሻዉንና የምንታገልለት አንድነት ነጸብራቅ በመሆኑ ደስተኞች ነን።
የህዝበ ሙስሊሙ አለም አቀፍ የህግ አማካሪና ጠበቆችን ጋር በመሆን ዛሬ ከአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተወካዮች ጋር ስብሰባ አድርገናል። የተደረገዉ ስብሰባ አመሪቂም ነበር። ዉጤቱም በቅርብ ይታያል የሚል እምነት አለን።
የአንድ ቀን ጉባኤአችን የተሳካ ነበር። በቀጣይነት ይህንን ስኬት ለመድገም እንሻለን። በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉ ሙስሊሙ ወገናችን የሚሳተፍበት ታላቅ ጉባኤን በዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ለማዘርጋጀት መሰናዶዎች መጠናቀቃቸዉን ስንገልጽ በደስታ ነዉ። የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት በሚቀጥለዉ አመት ከጁላይ 21 እስከ ጁላይ 24 ድረስ የሚያዘጋጀዉ ጉባኤ ትግሉ የኔም ነዉ የሚል ሁሉ የሚገናኝበት፣ የማይተዋወቀዉ የሚተዋወቅበት ብቻ ሳይሆን አገር ቤት የሚደረገውን የመብት ትግል ለመደገፍ የተላያዩ ህዝባዊ ትእይንዮች የሚደረጉበት፣ የዲፕሎማሲ ስራዎች የሚሰሩበ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበትም ጭምር ይሆናል።
በቀጥዮቹ ቀናት ሰፋ ያለ የጉባኤን ሪፖርት እደምናቀርብ እየገለጽን ለጉባኤዉ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ በተለይ ፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽንን ከልብ ለማመስገን እንወዳለን።
ትግላችን እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! አሏሁ አክበር !!!
