የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ለህዝብ ክፍት የሆነ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የስደት መንግስት የምስረታ ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት፤ ቅዳሜ፣ሴፕቴምበር 12፣ 2015 ከቀኑ 3pm ጀምሮ (በዋሽንግተን ዲሲ ሰአት አቆጣጠር) ለህዝብ ክፍት የሆነ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል። በእለቱ የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ተወካዮች፤ የስደት መንግስት ምስረታው ሂደቶችንና የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝርና በጥልቀት ከማቅረባቸውም ባሻገር፤ በሚዲያ ተወካዮችና የተለያዩ በርካታ ተካፋይ ጋዜጠኞች ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች ግልፅ በሆነ መንገድ ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ። ዝርዝሩን ለማንበብና ለመሳተፍ እዚህ ላይ ይጫኑ።