በዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ አባ መላኩ ሠራዊታቸውን አሰለፉ

በአቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ፊታውራሪነት የሚመራው “”ዘመቻ አባ መላኩ” የተሰኘው ሁሉ አቀፍ ዘመቻ ሰሞኑን በአትላንታና በዋሺንግተን ዲሲ ከተማዎች ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። የዘመቻው ትልቁ ግብ ስለሰባዊነትና ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆሩትን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማዳከም እንደሆነ ይታወቃል። ይህ በተለይም በዲያስፖራ ያለውን ተቃውሞ እንዳይጠነክር ለማፈን የታለመ ዘመቻ ነው። ለዘመቻው አፈጻጸም የተነደፈው ስትራቴጂው ሦስት አማራጮችን ጎን ለጎን አድርጎ መንቀሳቀስን ያካተተ ነው። እነዚህም፤
● ከተቻለ እያንዳዱን ቤተክርስቲያን በአባ መላኩ ቁጥጥር ስር ማዋል፣
● ካልተቻለ ደግሞ ሥርዓተ አልበኝነትን በማስፈን መበጥበጥ። በተለይ የጸረ-ወያኔን ጎራ በትርምስ ማወክና ስለወገኑና ስለ እምነቱ የሚቆረቆረው ሁሉ በተረጋጋ መንፈስ መኖር እንዳይችል ማድረግ ነው። ይሄ በአገር ቤት የሚደረገው አይነተኛ መገለጫው ነው።
● በአንድ ከተማ ውስጥ ሌላ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ስም በየማእዘኑ መክፈትና፣

በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠናቀረውን ሪፖርታዥ ሙሉ መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዘመቻ አባ መላኩ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ