ጤፍ በርበሬ ቡናና የተለያዩ ምርቶች ወደ ጎረቤት ሃገሮች በሕገወጥ መንገድ እየወጡ ነው::

በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ለዋጋ መናር ዋነኛው ምክንያት በሕገወጥ መልኩ ከሃገር ስለሚወጡ እና የምርቶቹ በቂ አቅርቦት አለመኖር መሆኑ ተጠቆመ::ራሱ አስታጥቆ ባሰማራቸው ሕገወጥ ደላሎች እና ነጋዴዎች ራሱ እያጭበረበረ ራሱ እያስጠና ራሱ የሚነግረን የወያኔው መንግስት ጥናት እንደሚጠቁመው በርበሬ ጤፍ ቡናና የተለያዩ የኢትዮጵያ ምርቶች 75% የሚሆኑት በሱዳን በኩል በመውጣት እስከ ኤርትራ እንደሚሻገሩ ታውቋል::15% የሚሆኑት በሰሜን ሶማሊያ እንዲሁም 10% የሚሆኑት ደግሞ በኬንያ እና ጅቡቲ በኩል በሕገወጥ መልኩ እንደሚወጡ ተገልጿል::

የቡና የጤፍ የጥራጥሬ እና በርበሬ ምርቶች ዋጋ መናር አስመልክቶ በተደረገ ጥናት፣ ምርቱ በደቡብና በሰሜን የሚገኙ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሚገኙ ሕወሓት ባሰማራቸው ደላሎች አማካኝነት በህገወጥ መንገድ በሱዳን ኬንያ እና ሰሜን ሶማሊያ እንዲሁም ጅቡቲ ድንበር ሾልኮ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ በህጋዊ መንገድ ታክስ እየተጨመረባቸው ወደ ውጭ አገር ተልከው የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙት ምርቶች የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት አለመመለሱ በሃገር ቤት ከኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ እንደሞተ ታውቋል::ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ የሚሆኑት እነማን ናቸው ለሚለው ተሽከርክሮ የወያኔ ባለስልጣናት ላይ ስለሚያርፍ ጉዳዩን እየሸፋፈኑት ሃገሪቷን ባዶ አድርገዋታል::