11 በመቶ እድገት ያስመዘገበ አገር እንዴት 9,7 በመቶ ካስመዘገበ አገር ልምድ ይቀስማል? (ምንሊክ ሳልሳዊ )
11 በመቶ እድገት ያስመዘገበ አገር እንዴት 9,7 በመቶ ካስመዘገበ አገር ልምድ ይቀስማል? (ምንሊክ ሳልሳዊ )
የካደውን የረሃብ እና ድርቁን አደጋ ወያኔ ባመነበት ሰአት ላይ አሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ በቻይና ተገኝቶ ከቻይና የኢኮኖሚ እድገት ልምድ ለመቅሰም እንደሚፈልግ ሲደሰኩር ተሰምቷል ፡፡ ጃፓንን ከርብታ በአለም ሁለተኛ ደረጃ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበችው ቻይናን በሁለት በመቶ የሚበልጠው ወያኔ በየትኛው ሞራሉ ልምድ እንደሚቀስም ቢገርምም ምን ያህል በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ከባድ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ በተደጋጋሚ እየተጋለጠ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰተው ረሐብ እና ድርቅ በኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ሲክድ ከርሞ በግብርና ሚኒስትሩ በኩል አምኖ የለጋሽ አገሮችን እርዳታ መለመን ጀምሯል ፡፡
በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በአፋር እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሆነ ረሐብ እና ድርቅ በመከሰቱ ከ4,5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ እርዳታ እንደሚፈልግ ወያኔ በሆዳም ባለሥልጣናቱ በኩል እርዳታ ከመለመን አልፎ በይፋ አምኖ በምግብ እህል ራሱን ቻለ እየተባለ ለሐሰት ፕሮፓጋንዳ የዋለው ሕዝብ ረሐብ ባስከተለው ችግር ለጤንነት ችግር በመዳረጉ የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልግ መነገሩ ያለው የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ ለሕዝቡ ግድ እንዳሌለው ማሳየቱን ቀጥሏል ፡፡ የተካደውን ረሐብ ሳምንት ሳይሞላ ማመን ስርአቱ ምን ያህል እንደበሰበሰ ያሳያል ፡፡
አሻንጉሊቱ ሐይለማሪያም በቻይና ስለ ልምድ መቅሰም ማላዘኑ የተካደው ድርቅ መታመኑ ስርአቱ ያለበትን አጣብቂኝ ያመለክታል ፡፡ ያልተመዘገበው እድገት በሐሰት በተቀነባበረ ፕሮፓጋንዳ እንደተመዘገበ ማውራት እንዲህ ያጋልጣል ፡፡ የትም ላለመድረስ መፍጨርጨር መጨረሻው እውነት ለመጋፈጥ ጋሬጣ ይሆናል ።
ይህንን የበሰበሰ አገዛዝ እያየን እንዳለነው መውደቂያ ላይ መሆኑ እና ስልጣናቸውን በሐሰት ፕሮፓጋንዳ እንደገነቡ ስለሆነ የለውጥ ሐይሎች ሕዝቡን በማስተባበር በማደራጀት በጋራ ልዩነትን አቻችሎ በመታገል ወያኔን በመደምሰስ ታሪክ መስራት አለብን ፡፡ለመጪው ትውልድ ከዘረኝነት እና ከሐሰት የፀዳች ኢትዮጵያን ለማስረከብ የተነጠቅነውን ነፃነት በትግል እናስመልስ፡፡ #ምንሊክሳልሳዊ