ግንቦት ሰባት ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡

ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› […]