በተገኘበት አብሮ መውቀጥ ለምን ? በነፈሰበት መንፈስ እስከመቼ ? በሚገባቸው ቋንቋ እናናግራቸው!!! (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እስክመቼ ድረስ እያወራን እንደምንኖር አላውቅም::ይህን ሰሞን የሕወሓትን ስብሰባ ተከትሎ አስር ጊዜ የባለስልጣኖቹን ስም በመጥራት ወሬ እያጣፈጡ የሚነግሩን ተቃዋሚ ነን ባዮች በተገኘበት አብሮ መውቀጥ በነፈሰበት አብሮ መንፈስ ለምን? እስከመቼ? ልላቸው ወደድኩ::አሁን ጊዜው የአርከበ ምንቸውት ገባ የአዜብ ምንቸት ወጣ እያልን የሕወሓትን ጉዞ የምንደሰኩርበት ሳይሆን በሚገባቸው ቋንቋ የምንነግርበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አንዘንጋው:;እረ እስከመቼ ? እንንቃ !!!

የሃገሪቱን የማፊያ መንግስት በበላይነት የሚመራው ሕወሓት መሆኑ እሙን ነው:: ሕወሓት ከስሙ ጀምሮ እንደሚያሳየን ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የማይተኛ ድርጅት ነው:: ከሕወሓት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን አሊያም የሕዝብ ስልጣን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመጠበቅ ነው::ይህ ድርጅት ከበረሃ ጀምሮ ይዞ የመጣውን ጸረ እትዮጵያ አቋሙን ለመተግበር ሃገርን እና ሕዝብን አደጋ ውስጥ ጥሎ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በመስራት ላይ ነው:: አመራሮቹም ቢሆኑ የሚሰሩት ግፍ ዘረፋ እና ይቅር የማይባል ተንኮል ሕዝቡን ለድህነት ሃገርን ለውርደት ዳርጓል::

የሕውሓት አመራሮች ተናከሱ አልተናከሱ ተተካኩ አልተተካኩ የሕወሓት አመራሮች ተፋቀሩ አልተፋቀሩ ዋሹ አልዋሹ ለሃገራችን እና ለሕዝባችን የማይተኙ እባቦች መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል::ማወቅ ያለብን እነዚህን ተኩላዎች ማስወገድ ብቻ ነው በሚገባቸው ቋንቋ ልንነግራቸው ይገባል ለአለም የሚሰሩትን ግፍ በሎቢ ልናዳርስ ይገባል::ስለ ሕወሓት የፓርቲ ስራዎች ከምናፏጭ ይልቅ ለትግሉ መሆን ያለበት ተግባር በመፈጸም ሕወሓቶችን በምናስወግድበት ላይ ሁሉ ልንረባረብ ይገባል::

3 Comments on “በተገኘበት አብሮ መውቀጥ ለምን ? በነፈሰበት መንፈስ እስከመቼ ? በሚገባቸው ቋንቋ እናናግራቸው!!! (ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. “ስለ ሕወሓት የፓርቲ ስራዎች ከምናፏጭ ይልቅ ለትግሉ መሆን ያለበት ተግባር በመፈጸም ሕወሓቶችን በምናስወግድበት ላይ ሁሉ ልንረባረብ ይገባል”

  2. የሕውሓት አመራሮች ተናከሱ አልተናከሱ ተተካኩ አልተተካኩ የሕወሓት አመራሮች ተፋቀሩ
    አልተፋቀሩ ዋሹ አልዋሹ ለሃገራችን እና ለሕዝባችን የማይተኙ እባቦች መሆናቸውን
    ልናውቅ ይገባል:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*