አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ወንጅለዋል::

አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ወንጅለዋል::

Minilik Salsawi የሕወሓት ሆድ አደር ሹመኞች በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ላይ አንሳተፍም ሲሉ አጉረመረሙ:: – በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ:: በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ግምገማ አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት መረጃዎችን በግል ጥቅም በመለወጥ አሳልፋቹ እየሸጣችሁ ናቸው በሚል መገምገማቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።እንደ ምንጮቹ ከሆነ መረጃን ያለምንም ርሕራሔ እየቸበቸባቹ የድርጅታችንን ምስጢራዊ ጉዳዮች የያዘ መረጃው በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጠላት እጅ ገብቶ ያገኘነው ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ተናግረዋል።በዚህ ግምገማ የተከፉት የደህንነት አባላት በመንግስት ባለስልጣናቱ እየተናጡ ቢወረፉም ዝምታን መርጠዋል።

የሕወሓት ሆድ አደር ሹመኞች በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ባለመሳተፋቸው ማማረራቸው ተሰምቷል በሃገሪቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መንግስት እንቅስቃሴ ውስጥ ከወያኔ ባለስልጣናት ውጪ ለበታች ተከታይ ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደቆመ ሲታወቅ ማንኛውም ሃገራዊ ጉዳይ አልቆ እና በአፈጻጸም ደረጃ ላይ ሆኖ እንደማንኛውም ሰራተኛ እንደሚሰሙ ባለስልጣኖቹ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ::የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ በሕወሓት የጦር እና ደህንነት ክፍሎች ውስጥ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል ሲሉ ውስጥ አውቂዎች ይናገራሉ::

ክዚህ ቀደም ተሞክሮ እንዳልተሳካ እና አሁንም ከባለፈው አካሄድ እና ግምገማ በተሻለ መልኩ በወያኔ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣጠር የሚረዱ ግምግናዎች እና የማጣሪያ ስብሰባዎች በስፋት መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ክፍሉ ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተደረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

5 Comments on “አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ወንጅለዋል::”

  1. I dont know for how long can you lie. I have been reading most of your Breaking news ( seber zina) and the news you earn from your informats but i was loughing when i read them. Do you think will you get those top secrets fron INSA? why do you lie and why you think that Ethiopian diasporas are stuped? I think most of the diaspora knows about Ethiopia and got full information. We dont wish to war for our people we need peace and divelopment we need our people to feed him self ,we dont need the people of Ethiopia to harvest bullets. War is enough by our fathers and ancisters pleas pleas stop talk about war and agration. Come back to your normal mind, GOD BLESS ETHIOPIA AND BLESS YOU TO WITH THE PEOPLE OF OUR HOLLY LAND.

  2. ከነባሮቹ፦
    INSA በሪሞት የሚልካት ትንሿ በራሪ ግ7 ያለበትን የሚያሣይ ሥትሆን በቀላሉ በወንጭፍ የምትወድቅ መሆኑን ወዳጄ የሥርአቱ ሀላፊ ገልፅዋል ።

    G7 ተጠንቀቁ መረጃ አሠባሥቡ

  3. አፈናው በነጭ minibus
    5L pickup
    DX
    v8
    yaris
    vitz
    በመሆን ተቃዋሚዎችን እያሣደዱ እየገጩ ይገኞሉ ማን?
    የወያኔ ደደብ ቅጥረኞች በድፍኑ ተዋጊ የነበሩ የትምህርት ደረጃ የለሌላቸውን ታጋይዎች ወያኔ በዚህ መድቧቸው ይገኛል።

    ምንጭ
    ሳሙኤል ክንደያ
    አባቱ ደህንነት የነበሩ

  4. SATCON ኮንሥትራክሽን ከዮቴክ እና ሡር ከተባሉ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በፋይናሥ ወያኔን እየደገፋ ይገኛሉ ።

    ALL WE HAVE FINACIAL STATEMENT EFFORT ORGANAZATIONS INCLUDING WEYANE BANKS TO SHOW U SOON.

  5. እነዚህ ምልምሎች
    በታክሢ
    በማደያ
    በካፌ ወዘተ…ወያኔ በመረጠው አቅጣጫ ህዝቡ ላይ የሽብር ፕቃት ፈፅሞ ጠላቴ የሚላቸው ተቃዋሚ ድርጅቶችን በተለይ አዲሦችን ለማፈን ያነጣጠረ ሤራ መኖሩን እነኚሁ አባሎች መሥክረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*