በኬንያ ስደተኛው መሃል ሰርገው በመግባት የሚሰልሉ የወያኔ ሰላዮች አዲስ አበባ ከትመዋል::

Minilik Salsawi – ሰሞኑን የዲያስፖራ ሳምንት በሚል የወያኔ በዓል ላይ ለመገኘት ወደ አስር የሚጠጉ የወያኔ ሰላዮች ከኬንያ ናይሮቢ በዳያስፖራ ስም ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል።እነዚህ በስለላ ስራ ተሰማርተው ለረጂም አመታት በናይሮቢ መንግስትን ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰቦች በተባበሩት መንግስታት ስደተኛ ኤጀንሲ(ዩኤነኤችሲአር)ተመዝግበው የቆዩና የስደተኛ ወረቀት ያላቸው ናቸው። ሲሉ ኬንያ የሚገኙ በወያኔ ግፍ ተማረው የተሰደዱ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በውስጥ መስመር ለምኒሊክ ሳልሳዊ ያደረሱት መረጃ ይጠቁማል::

በኬንያ የሚገኙ ንጹሃን ስደተኞች እንደተናገሩት ግለሰቦቹ ወደ ሀገር ቤት ከመመለሳቸው በፊት በናይሮቢ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሰዎቹ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ጋር ያላቸው ግንኙነት ያሳስባቸው እንደ ነበረ በተለያዩ ተቋማት ፍርሀታቸውን ሲገልጹ የቆዩ መሆናቸው ተዘግበዋል። እነዚህ ሰላዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አካባቢ አገልግሎት በማድረግ የሚታወቁ ሲሆኑ ቤተክርስትያኒቷን እንደ ሽፋን በመጠቀም የተለያዩ የስለላ ስራዎችን ሲሰሩ እንደቆዩ ታውቋል።ኬኒያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሲሆን ከነዚህ መሀል ሀምሳ የሚሆኑት ጋዜጠኞችና የሰብ አዊ መብት ተሟጋቾች መሆናቸው ይታወቃል።

ንጹሃንኑ ስደተኞች ያላቸውን ተጨማሪ መረጃ በማጣቀስ እንደገለጹት ወያኔ የዲያስፖራ በዓል ብሎ በሚያከብረው ሳምንት ላይ ለመገኘት ወጪያቸውን ሸፍኖ ከኬንያ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ ከጎረበት አገሮች ወደ 5000 ተላላኪ ጆሮ ጠቢዎችን ዲያስፖራ ናቸው በሚል ሽፋን ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዙ ሲታወቅ መሬት እና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸውዋል:;በጎረቤት አገሮች በስደተኛ ስም ተመዝግበው የሚገኡ እነዚህ የወያኔ ተላላኪዎች ንጹሃኑን ዜጎች አሳልፈው በመስጠት ስራ ላይ የተሰማሩ የነበሩ እና ተመልሰው ወደነበሩበት የጎረቤት አገር ከመምጣታቸውም በፊት በጆሮ ጠቢነት እና መረጃ አቀባይነት ስልጠና እና መመሪያ እንደሚሰጣቸው ታውቋል::ዲያስፖራ ማለት በውጪ ሃገር የተማሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ስያሜ መሆኑ ሲታወቅ በኬንያ እና በተለያዩ የጎረቤት ሃገሮች ወያኔ ጭኖ የወሰዳቸው ግለሰቦች ዲያስፖራውን የማይወክሉና የዲያስፖራን ስያሜ የማያሟሉ የወያኔ ተላላኪዎች እንደሆኑ ንጹሃኑ ስደተኞች ይናገራሉ::

6 Comments on “በኬንያ ስደተኛው መሃል ሰርገው በመግባት የሚሰልሉ የወያኔ ሰላዮች አዲስ አበባ ከትመዋል::”

  1. Ejig betam new yazenkut bante. Min aynet hlina yelileh endehonk ligebagni alchalem. Wshetim eko lik ena leket alew wendmi. Ante gin ye Ethiopia hizib yaltemare denkoro,yemayaneb meslo yitayhal? Yesew lij 1 yiwashal 2 gizi yiwashal,ante zelalemkin endewasheh litnor new? Lijin biteseb haymanot kalehu bebitesebih sim yihunibih bemitamnew fetari ebakih wede hlinah temeles. Eski bichahin sithon asibew 5000 diaspora abalatin ticket korto hotel askemito mengist liyatalilen new sitil ayseketitihim? Sewech eko nen enasibalen, enanebalen, ke diasporaw ga new emininorew ena washteh atadenkuren.lezariw altesakalihim belila hunitana gizi lila wshet yizeh kireb,temeker ewnet awra. ETHIOPIAN FETARI YIBARK LANTEM LIBONA ENA EMIYASIB HAYMRO YISTIH.

  2. ይህ የወያኔ እኩይ በዲሞክራሢ ጭምብል ተሸፍኖ መድረኩ እንዲጠብና በአሸባሪ ሥም መጠረፉን ተያይዛል በነባር ሀይማኖት ገብቶ ማተራመሡን ቀጥሏል ፈንጂው በጁ አፈንጁው የራሡ ደህነቶች መሆናቸውን በቅርቡ ይፋ ለህዝቡ ይደረጋል
    የማፈኛ ተሽከርካሪዎቹም ኮድ 2 የሆኑ ነጭDX xli corolla yaris 5L minibus ናቸው በፖለቲካ አመለካከትህና እንደሠው ከተናገርክ ይህ ይጠብቅሀል ።

    ይህን የወየበ ወያኔ ወጊድ ብለን ውድቀቱን አናፋጥናል እንበርታ
    ድል ለግ7

  3. እነዚህ ዲያሥፓራ የተባሉት የወያኔ ካድሬዎች የትራንፓርት ወጪ ሸፍኖ ለፕሮፖጋንዳ ጠርፎ ያመጣቸው ናቸው ምነው በህዝቡ ብር ባይጫወታል ረሀብና ድርቅ ከፊታችን ተደንቅሮ.

  4. markeshaw: you are a pig may be you are one of them to spy behind the real ETHIOPIANS the whole country hate eprdf. you are the one lying up to your head if you have one. all hotels are under weyanes and ETHIOPIAN air lines is controlled by weyanes and you are pretending as if they couldn’t do it. they did it before they can do it now. so it is better for you to spit somewhere else.

  5. Besew samba silemotitenefis alferdibihim. Be ergitegndaney titsetgfetaleh betenagerkew. I am not pig I am Markeshaw. A houman like you who was born in Eothiopia. Endit poletican awkalehu bilo comment kemiset ethipiawi endih aynet tseyaf kal yisebezeral? GOD BLESS ETHIOPIA

  6. Marketshaw you seem one of the woyane blood sucker who tries to confuse people who have enough of the woyanes evil doings . The woyane is super mafia and merciless bunch of criminals who have enriched themselves robbing the national coffer. Unless you are kind of stone headed surrendered to woyane and become one of the woyane drag net or inside informer with mission to assassinate Ethiopians , you would not have the gut to completely deny the truth what we see daily in our eyes . The woyane leave no stone unturned to ensure its survival . This was evidence d from the fact that woyane reported to have bribed Yemeni government million dollars to accomplice in the hijacking of Andargachew Tsgie . So why not woyane can not do the same and pay whatever amount , since the money not coming out the woyanes pocket. We have noticed how woyane lavishly and deliberately squandered our national resource . The flag day, nation nationalities days are the few pretexts woyane flush our money just only for propaganda purposes. In fact no one knows how much money is being squndered . But it is estimated over a billion birr being spend in the name of festivities from which chunk of the money directly goes to fatten the pocket of core woyaneS. I think it is not a big deal to woyane if it foot transportation bill to its 5000 Bandas and informers. Woyane means thief.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*