በአርበኞች ግንባር አባልነት የተጠረጠሩ ዘጠኝ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች በአሸባሪነት ተከሰሱ

አንዱ ተጠርጣሪ የፌዴራል የፖሊስ አባል እንደነበር ተጠቁሟል መቀመጫውን ኤርትራ ውስጥ ማድረጉንና ራሱን ‹‹የአርበኞች ግንባር›› በማለት እንደሚጠራ የተገለጸው ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበልና አባላትን በመመልመል ሲሳተፉና ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል የተባሉ ዘጠኝ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች፣ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ […]