የዋለልኝ መኰንን አጭር የትገል ታሪክ

Walelign Mekonnen

ዋለልኝ መኰንን በድሮው አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት በደብረሲና ወረዳ ከአባቱ ከአቶ መኰንን ካሣና ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበች ግዛው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓመተ ምህረት ተወለደ። ዋለልኝ መኰንንም በደሴ ከተማ በሚገኘው የንጉሥ ሚካኤል ተምህርት ቤት አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ከዚህም በመቀጠል መስከረም 1954 ዓመተ ምህረት ደሴ ወይዘሮ ስሕን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተምህርት ቤት ትምህርቱን ቀጠለ። በዚህ አጋጣሚ በ 1950 ዎቹ ውስጥ ሎተሪ ለዋለልኝ መኰንን አሥር ሽህ የኢትዮጵያ ብር ደርሶት ነበር ገንዘቡን ግን የተቸገሩ ስዎችን በመርዳት ተጠቅሞበታል። ዋለልኝ የ12ኛ ደረጃ ትምሕርቱን ያጠናቀቀው በ 1958 በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ስር ይተዳደር በነበርው በልዑል በዕደማርያም ቅድመ ዝግጅት ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር። በዚህ ትምህርት ቤት ቆይታው በሥነ ፅሁፍ ዝግጅት የላቀ ሚና ተጫውቷል። የክርክር ክበብ ምክትልና ዋና ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግሏል። በዚሁ ክበብ አማካኝነት በተለይም የሥነ አመክኗዊ /Logic / ውይይት አካሄድን ልቅም አድርጐ እንደተማረ ይነገርለታል። ትምህርት ቤቱ ዋለልኝን ተከራካሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ፀሃፊም እንዲሆን ረድቶታል። በሁለት ዓመት ቆይታው የትምህርት ቤቱ የጋዜጣ ረዳት አዘጋጅ በመሆን አገልገሏል። ጥሩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ችሎታ ያለው ፀሃፊ እንደነበረ ጹሁፎቹ ምስክር ናቸው። የአጻጻፉ ሥልት ከእነ ኃይሉ ገበረዮሐንስና ፀጋዬ ገብረ መድህን ሰልፍ ላይ እንደ ነበር ጓደኞቹ ይናገራሉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተቀላቀለ በኋላ፣ በ ሕዳር 18, 1961 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በተደረገው የሥነ ጽሁፍ ውድድር “የአዚናራው እሥረኛ” በሚል አርእስት ኢትዮጵያውያንን ከጣሊያን ወታደር ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ፣ መስዋዕትነት፣ ጀግንነት፣ ለአገር ታማኝነትና ፍቅርን የሚያሳይ ሰነ ጽሁፍ ጽፎ ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የአንደኝነት ማዕረግ በመጐናጽፉ ሽልማት አግኝቷል። በየዓመቱ በሚከበረው የዩኒቨርሲቲው ቀን ላይ በመወዳደር ካሸነፉት ስመጥር ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች አንዱ ዋለልኝ መኰንን ነበር። በዚህ ጽሁፍ ምክንያት አገርና ሕዝብን ለመበጥበጥ በሚል ክስ ዋለልኝ መኰንን፣ ሄኖክ ክፍሌ፣ ታምራት ከበደ፣ ጌታቸው ሻረው፣ ፋንታሁን ጥሩነህ፣ አያሌው አክሎግና ገዘኸኝ መኰንን የተባሉት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች አምስት ዓመት ተፈርዶባቸው አዲስ አበባ ከርቸሌ ከቆዩ በኋላ ተለቀዋል።
ዋለልኝ መኰንን በዚሁ የኢትዮጵያን አርሶ አድሮችና ላበ አድሮች ነፃ ለማውጣት በ60ዎቹ ውስጥ በተደረገው የኢትዮጵያ ወጣቶች ትግል ውስጥ ዓብይ ሚና የተጫወተ ወጣት ነው። ጥላሁን ግዛው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ባደረገው ከፍተኛ የትግል ተሳትፎ ከባድ ክትትል ይደረግበት ነበር። አፍንጮ በር አካባቢ ታህሳስ 19, 1961 ዓ.ም ጥላሁን ግዛው በጥይት ይመታል። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ሲፈጠር ዋለልኝ መኰንን አምስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ቤቱ ከጓደኞቹ ጋር ነበር። አንድ ወጣት ወደ ቤት ይመጣና ስለ ጥላሁን ግዛው በጥይት መመታት ይነግራቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተያይዘው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ይሄዳሉ። ሐኪሞቹ ሕይወቱን ለማትረፍ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ይነግሯቸዋል።በዚህ ወቅት ዋለልኝና ጓደኞቹ የጥላሁንን አስከሬን ከሆስፒታሉ በመውሰድ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ቅጥር ግቢ Morgue ውስጥ በስርዓት ያስቀምጡታል። ከዚህ በኋላ የተቃውሞ ትዕይንትና የቀብሩን ሥርዓት ዝግጅት ያደርጋሉ። ለኮሌጅና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። የጥላሁን ሞት ትግላቸውን እንደማይገታው፣ ጥላሁን ቢሞት ሽህ ጥላሁኖች እንደሚፈጥሩ በመግለጽ ጽሁፎችን በሕዝብ መሃል ያሰራጫሉ። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን የጥላሁንን አስከሬን ለመውሰድ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገባሉ። በዚህ አጋጣሚ ዋለልኝ ከፎቅ ላይ ሆኖ በድምፅ ማጉያ ጥላሁንን የሚቀብሩት የትግል ጓዶቹና ሕይዎቱን የከፈለለት ሕዝብ እንጂ ገዳዮቹ መቅበር እንደማይችሉ ይናገራል። የክብር ዘበኛ ወታደሮች በተማሪዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተው አበበ በርሔ፣ ስብሃቱ ውብነህ፣ ጀማል ያሲን የተባሉ ተማሪዎችን ይገላሉ። በዚያን በሽብር ወቅት ዋለልኝ መኰንን ይተርፋል ያለ ሰው አልነበረም። ነገር ግን ዋለልኝና ጓደኞቹ ወደ ኮልፌ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይታሰራሉ። ዋለልኝ ከአሁን በፊት በገደብ ስለተለቀቀ እንደገና ወደ ከርቸሌ እስር ቤት ይላካል። በአዲስ አበባ ዩኒበርስቲ ማህበርና(USUAA) በብሔራዊ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማህበር(NUEUS) በከፍተኛ አመራር አባልነት ሚና ተጫውቷል። ከአንድ ጓድኛው ጋር በተደረግ ቃለ መጠይቅ ስለዋለልኝ ይህን ተናግረዋል። በጽሁፍ ችሎታ ይደነቅ የነበረው ዶክተር እሸቱ ጮሌ ነበር። ቀጥሎ በጸሃፊነቱ የማስታውሰው ዋለልኝ መኰንን ነበር ። የቃላት አጠቃቀሙና የሐሳብ ፍስቱ(Flow) ልዩ ነበር ብለዋል። ዋለልኝ መኰንን ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ የተማሪዎቹ ልሳን የነበረው ታገል መጽሄት ታገደ። ዋለልኝ መኰንንም እንደዚሁ!! ከትምህርት ቤቱ እገዳ በኋላ፤ በወቅቱ የመንገድ ማመላለሻ አስተዳደር ተብሎ ይጠራ የነበረው መንግሥታዊ ድርጅት ሥራአስኪያጅ አቶ ሽመልስ አዱኛ ሥራ እንዲጀምር ዕድል ይሰጡታል። በዚሁ ድርጅት ሥራ እየሰራ እያለ ብርሃነ መስቀል ረዳና ሌሎች የትግል ጓዶቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ድርጅት መሥራች ጉባዔ ስብስባ በርሊን ላይ በመጥራታችው፤ ዋለልኝም በዚህ ስብስባ ላይ ለመገኘት ወሰነ። ወደ ስብሰባው ለመቀላቀል አውሮፕላን ከመጥለፍ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። ሕዳር 29, 1965 ዓመተ ምሕረት ከጥዋቱ አንድ ስዓት ተኩል ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ (በአሥመራ በኩል ወደ አቴንስ ሮም ፓሪስ) ለመሄድ የተነሳውን የበረራ ቁጥር 708 ቦይንግ ጄት አውሮፕላን፣ ዋለልኝ መኰንን፣ ማርታ መብራቱ፣ታደለች ኪዳነ ማርያም ፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ ጌታቸው ሀብቴ፣ ዮሐንስ ፈቃዱና ተስፉ ቢረጋ ሊያስገድዱት ሞክረው ባለመሳካቱ ታደለች ኪዳነ ማርያም ስትተርፍ ዋለልኝ መኰንን እና ሌሎቹ በጸጥታ አስከባሪዎች በተተኮሰ ጥይት ሕይዎታቸው አልፏል።
አባቱ አቶ መኰንን ካሣ ከአዲስ አበባ በልጅ ልጃቸው ስለአደጋው ሁኔታ ስለተገለጸላቸው ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከቀዳማዊ ምንሊክ ሆስፒታል አስከሬኑን ተረክበዋል። ከአዲስ አበባ እስከ ደሴ ባለው አውራጐዳና ላይ ችግር ቢፈጥር ሃላፊነቱን አቶ መኰንን ካሣ እንደሚወስዱ በጊዜው የፀጥታው ክፍል ሃላፊ የነበሩት ባለስልጣናት ግዴታ አስፈርመዋቸው ነው ጉዞ ወደ ደሴ የጀመሩት። በደሴ ከተማ የነበረው የፀጥታ አጠባበቅ የተጠናከር ቢሆንም የወይዘሮ ስሕን ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትግል ጓዶቹ፣ ዘመድ አዝማድ በተገኘበት በመድሃኒ ዓለም ቤተክርስቲያን በክብር አርፏል።የሚገርመው ነገር በመንግሥት ላይ ያመፅ በመባል ፍትሃት አልተደረገለትም። ዋለልኝ መኰንን በአንዳንድ ግለስቦች እንደ ተራ አወሮፕላን ጠላፊ ቢታይም በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት በተደረገው ትግል ታሪክ ውስጥ ያደረገው ግንባር ቀደም ተሳትፎውና የብዕሩ ለዛ ሚዛናቸው የደፋ ነው።

10 Comments on “የዋለልኝ መኰንን አጭር የትገል ታሪክ”

  1. No mention of Eritreans, no mention of the cause of his struggle (Africa wide rejected tribalism) and no mention of foreign contacts.

    He failed to attend the meeting that founded the EPRP in Berlin (West Berlin ?) , Germany in 1972. Did foreigner play a role here, or were they even the initiators ?

  2. የሆስፒታሉ አስተዳደር ተገቢውን ፈቃድ ሳይሰጠው ሬሳ ከሆስፒታል አውጥቶ መውሰድ ወንጀል ነው ። ይህንንም የወንጀል ስራ ለሌላ ወንጀል ጠጠቅሞበታል ። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አመጽ በማስነሳት የሌሎች ተማሪዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል ። ከዚያም እንደ ፅሁፉ በርሊን ወስጥ ሊደረግ ታሰበ በተባለው ስብሰባ ላይ ራሱን ለማሳተፍ ሲል አውሮፕላን ጠልፎ የሌሎችን ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል ይህም ሌላ ወንጀል ነው ። ይህ ሰው ጀግና ነው ለማለት ይቸግራል ። የዚህን ፅሁፍ ርእስ የዋለልኝ መኮንን አጭር የትግል ታሪክ ከምትለው የወንጀል ታሪክ ብትለው የተሻለ ይገልፀዋል ።

  3. The fool guy, who had an Eritrean girlfriend at the time, appears to have been used by the Eritreans.

    But was he also used by foreign powers ?

    Regarding the United Nations General Assembly Resolution 2758 eyewitnesses reported that Africans, who were crucial in the voting and where Haile Selassie was the person who mobilized the African bloc, celebrated the admission of the People’s Republic of China to the UN and that the western powers, above all USA, who suffered a defeat threatened to revenge against Haile Selassie, someone regarded as an ally of the USA and the West.

    Was Walelign linked to that voting without knowing it ?

    https://en.wikipedia.org/wiki/United_Nations_General_Assembly_Resolution_2758

  4. He was not nonsense, and born to eat like you. He was brave and bright minded to bring vibrant changes to his country and the people that he loved. It is not a surprise the existence of trash people like you.

  5. I am glad from the above 4 comments it was only one who supported Walelgni that even could be shabians. His peers evaluate Wallelgni as attention seeker, adventurist and a loaded gun that can be fired by some one clever. What surprise me is the people who are trying hard to make him a hero. If he is a hero to us so does Afworki. In short Wallelgni and those who share his pholosophy are responsible for the destruction of Ethiopia and should be tried in absentia.

  6. Sid adeg shabia,
    you self-destructive people used him and other like minded Ethiopians. But even Eritreans dont like the outcome today, the reason 1/3 of Eritreans now live as refugees. Also most Eritreans now regret to have separated from Ethiopia. So what Walelign did did not benefit the fool Eritreans.

  7. But why are Eritreans self-destructive ?

    The answer is, they are possessed by italian demons.

    We know what Eritreans call Tigrians: primitive, uncivilized, they eat with their hand instead of with fork and knife, etc.
    The Eritreans got those italian demons and the self-hatred ( think about African American self-hatred and how they look down at Africans ) during colonisation.

    When Haile Selassie allowed Eritreans to live and thrive in Ethiopia those italian demons also arrived in Ethiopia and at the university in Addis Abeba where Walelign was enrolled.

    So the Eritrean students “infected” the other Ethiopian students with their demons and self-hatred and then we had the students movement.

    Had the Haile Selassie government anticipated that poisonous Eritrean influence, thanks to italian demons, and warned the Ethiopian students we would have less problems today.

  8. He and his comrades are responsible for the current massacre of Amhara people. They imitated it after all. Pls can you define hero for me? Mengestu Neway kills a lot of people with out a fair trial . is he a hero? Do we have to follow his example like Mengestu Hailmariam did. I think we have to redefine our heroes and not follow the 60s student movement .

  9. ታሪካዊ ስህተትን ለማረም ብቻ፤
    የታዘዙት የክብር ዘበኛ አባላት መጥተው በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተኩስ በመክፈት ተማሪዎቹን የገደሉት፤ ታህሣሥ ፲፱ ቀን ፲፱፻፷፪ እንጂ፤ እንደተዘገበው ፲፱፻፷፩ አይደለም። የተጠለፈውም ጄት ሳይሆን ዳኮታ ነበር። የተለጠፈውም ከባህርዳር ነበር።

  10. If you have a ball like Walelign Mekonnen, When do not you fight Wayane. He devoted what he has and his life for the Ethiopian people including the oppressed Amahar peasants.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*