ወያኔዎች ተረት ተረት ባወሩ ሰአት ሁሉ የኛ እየተነፋረቁ ማጨብጨብ ምን ይሉታል? (ምንሊክ ሳልሳዊ)
አትኩሮት ለመስረቅ; አቅጣጫ ለማሳት; ለማዘናጋት; በስሜት ለመንዳት ወዘተ ተመሳሳይ የሆኑ የፖለቲካ እኩይ ስልቶችን በመፍጠር ፕሮፓጋንዳ ደረጃ ወሬ በማናፈስ እና በማንፈስ ሰዉንም በማስነፈስ እና በማስተንፈስ ልምዱና ስልቱ የተካኑትን ወያኔዎች ተረት ተረታቸውን ባወሩ ሰአት ሁሉ የኛ እየተነፋረቁ ማጨብጨብ ምንም ፋይዳ የለውም::የኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ ነጻነታችንን እና መብታችንን ገፎን በፖለቲካ ጫና እና በኢኮኖሚ ድቀት እንዲሁም በማህበራዊ ዝቅጠት እያሸን ያለውን ወያኔን ተዋግተን ከጫንቃችን ላይ ማውረድ ሕዝቡም ለነጻነቱ እንዲታገል ማስተማር ዋና ስራችን መሆን አለበት::
ከዚህ በፊት እንዳልኩት አትኩሮት ለሚገባው ትግል አትኩሮት እንስጥ::ወያኔዎች በሚሰጡን የቤት ስራ እና የወሬ ንፋስ እየሾርን አንገዳገድ:;እርስ በርሳችን አንባላ::አንድ እና አንድ ጠላት አለን እሱም ወያኔ ነው::ይህን የበሰበስ ስርአት ለማጣል በጋራ ትግሉ ላይ አተኩረን ትግሉን እንስራው::ወያኔዎች የውስጥ ጉዳያቸው ሲያጨናንቃቸው መፍትሄ አልባ የሆነ ችግር ሲገጥማቸው መፍትሄው እስኪገኝ አሊያም የድርጅታቸውን መፈረካከስ ለመጠገን ከራሳቸው በሚፈጠር ራሳቸው ላይ በሚቀልድ እና በሚሟርት ሃሰተኛ ወሬ አዘናጊ እና አታላይ አጨቃጫቂ እና አስገራሚ የቤት ስራዎችን እና አጀንዳዎችን ለተቃዋሚው ጎራ አሸክመው ዞር ይላሉ::የተቃዋሚው ጎራ ያሸከሙትን የቤት ስራ እና አጀንዳ እየቧጠጠ ዳገታቸውን ለመውጣት ሲዳክር በነፈሰበት ሲነፍስ እነሱ የውስጥ የቤት ስራቸውን አጠናቀው ወደ ግድያ እና አፈሳቸው ይሰማራሉ::
ይህ ሁላ የራሳችን ድክመት የፈጠረው የራስ ጠላትነት ውልደት አካል መሆኑን ልናውቅ ይገባል::ዋና አትኩሮታችን መሆን ያለበት በየደቂቃው የሚፈጠሩ ንፋሶችን ሳንከተል ወያኔን በሚያስወግዱ የትግል እንቅስቃሴዎች ላይ በማተኮር በጋራ እየታገሉ ለሕዝብ እያስተማሩ ነጻነትን ለመቀዳጀት መገስገስ አበይት ጉዳይ ነው::ወያነዎች ተረት ተረት ባወሩ ሰአት ሁሉ የኛ እየተነፋረቁ ማጨብጨብ መፍትሄ አይሆንም::መፍትሄው ከላይ እንደተቀመጥው ለወሬ ጆሮ ሳንሰጥ በትግሉ ላይ አተኩሮ ትግሉን መርዳት ማቀናጀት ማደራጅት ማስተማር መቀስቀስ ወዘተ መሆን አለበት::