አመዳቸው ቡን ብሏል …. ፊታቸው ሁሉ በድንጋጤ ተውጧል::ያልገባውና ግራ የገባው ሙትቻ ስርአት : (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(ምንሊክ ሳልሳዊ) እስካሁን ወያኔዎች አለመረዳታቸው የሚገርመው እኮ ዘላለም መኖር የለም…ዘላለም መኖር አይደለም ዘላለም ስልጣን ላይ ዘላለም መቀመጥም እንዳሌለ ማወቅ ያስፈልጋል::ቃሊቲን ሳይቀምሱት ቂሊንጦን በካቦነት ሳያገለግሉበት አሊያም ካቦ ሳያንጫጫቸው ወደ ሞት መውረዳቸው ያንገበግበኛል:: አለቅን እኮ ኢሠፓአኮ.. ተባለ:ካለፉት መንግስታት መማር ያልቻለው ወያኔ ራሱን አልፋ እና ኦሜጋ አድርጎ ስለሚቆልል ከፍተኛ ክፍተት እና መንሸራተት እንደተከሰበት በገሃድ እያየን ነው::የዘረፉትን ዘርፈዋል ለምን ስልጣን እንደማይለቁ ያውቁታል የሰሩት ወንጀል የት እንደሚያውላቸው ያውቁታል:: ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት አለ ብሎ ለማመን ያስቸግራል ሕወሓት ከተወገደ ኢሕአዴግ ራሱን ያጠፋል::

ሕወሓትን የሚረከብ ተተኪ እንዳሌለ ይታወቃል::ለጊዜው በተባለው መስመር እንደ ገደል ማሚቱ ነገር እየደጋገም የሚሙልጨለጭ ትውልድ ሕወሓትን ተረክቦ በበረሃ እንደአለፉት ታጋዮች ጥርሱን ነክሶ አንጋፋዎቹን ለማዳን የሚችል ትውልድ አለመኖሩ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል::ወደ እርጅና እና መሰላቸት ውስጥ እየገቡ ያሉት ዘራፊዎቹ የጥጋብ መንፈስ የተጠናወታቸው ሕወሓቶች ስልጣን እስከሞት ድረስ ብለው በመያዝ ለሕዝብ ለማስረከብ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ለሆዳቸው ብለው የተጠጉ ካድሬዎች ሳይቀሩ እያሳሰባቸው ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል::ነገን ለመገመት ግራ በተጋባ ካድሬ የተሞላው ወያኔ መውደቂያ ከመቃረቡም በላይ ሊተካው የሚችል አስተማማኝ ሃይል አለመኖሩ ወደ ክስመት እንዲያዘግም አድርጎታል::

የለውጥ ፈላጊ ሃይሎች የጋራ ፍጥነት በሚጠየቅበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የወያኔ ባልስልጣናት ከነሹምባሾቻቸው ራሳቸውን እያቆለጳጰሱ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርጉት ጥረት በራሳቸው ሽብር ስለሚሸበሩ ውስጣችው መበስበሱ እየታየ ነው::ይህ ወሳኝ ወቅት ሊፈጠር የቻለው የለውጥ ሃይሎች እያቀጣጠሉ ያለው የትግል ነበልባል የፈጠረው ትልቅ ስኬት ተደምሮበት ወያኔን ወደ መጨረሻው ገደል ለመጨመር እየተገሰገስ ይገኛል::ይህ ሁሉ ተጨማምሮበት እርጅናው የተጫጫነው ሞት አፋፍ ላይ ያለው ወያኔ ባለስልጣናቱ አመዳቸው ቡን ብሏል::..ፊታቸው ሁሉ በድንጋጤ ተውጧል::ያልገባው እና ግራ የገባው ስርአታቸው ራሳቸው ግራ አጋብቷችው ዘላለማዊነት እንዳሌለ እየነገራቸው ነው::ሞትም እንዲህ ያደርጋል::

2 Comments on “አመዳቸው ቡን ብሏል …. ፊታቸው ሁሉ በድንጋጤ ተውጧል::ያልገባውና ግራ የገባው ሙትቻ ስርአት : (ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. Please in be half Ethiopian people sovereignty weyane must give up power to the coming brighter generation is better all regime leaders are old trend movement they are following deeply replay what Obama saying about dectatorial leadership corapted and berocracy every time seen rime against humanity.

    Please join and support G7 today!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*