የፊሽካው መነፋት ለወያኔ መሞት፤
ከመኖር መስታዎቱ
ከኮሎራዶ
ኢትዮጵያን በቁሟ ስትቸበችብ ኑረህ
ቆራርሰህ በጣጥቀህ ድንበር አሳጥተህ
የሃገርን ክብር አሳልፈህ ሰጥተህ
ህዝቡንም ለስደት ካገሩ አስወግደህ
ዜጎችን ጨቁነህ ጨፍልቀህ እረግጠህ
በዘር በኃይማኖት በጎሳ ሸብበህ
ባህሉን ትውፊቱን ቅርሱን አደብዝዘህ
እምየን ለማጥፋት ተማምለህ መጥተህ
ሃያምስት አመታተ አቁስለህ አንድደህ
ለብልበህ አቃጥለህ ምሁሩን ጨርሰህ
ታሪክ እንዳይገኝ መጻኅፍት አጥፍተህ
ህዝቦቿን አውድመህዶግአመድ አድርገህ
አንድ ህዝብ አንድ ሃገር እንዳይኖር ወስነህ
ጥቂት ግብስብሶች ሆድ አምላኩን ይዘህ
ወያኔ ልንገርህ አንተ እኮ ጨካኝ ነህ
በጠራራ ጸሃይ ሕጻን ትገላለህ
ባንክ ቤት ሲዘርፉ አገኘሁ ትላለህ
እርጉዞች ሳይቀሩ ታስጨነግፋለህ
የወሊድ ማምከኛ መርፌ ተወጋለህ
የዘር ማጥፋት መርህ ባገር ታስፋፋለሀ
ጎጠኛ መሆንህ በገሃድ ታየብህ፡፡
አንድ ለአምስት ቡድንን ጠርንፍ አዘጋጅተህ
ሰቅዘህ ጨምድደህ መላወሻ ነስተህ
መናገር መሰብሰብ እንዳይኖር አድርገህ
ሰብአዊ መብትን ፍጹም ታፍናለህ፡፡
በረሃብ በእርዛት ህዝብን እየፈጀህ
ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ላይ ስትኖር ተንደላቀህ
ጊዜውን ጠብቆ ፊሽካው ተነፋብህ
እንደ አረብ አብዮት ጠራርጎ ሊጥልህ፡፡
የጣር ምልክቶች በገሃድ እያየህ
የውሸት አቅማዳ ስልቻውን ሁነህ
ፍሽካውን የነፋው ሻቢያ ነው ትላለህ፡፡
ወያኔ በእውነቱ እባክ አዳምጠኝ
ውሸታም መሆንህ አሁንስ ትዝ አለኝ
ኢትዮጵያን ስትወር መሪህ የነገረኝ
ቧልቱንና ፌዙን በቀሉን ሲያስረዳኝ
አዲሲቷን ኢትዮጵያ እሰራታለሁኝ
ህዝቦቿንም ሳይቀር በቀን ውስጥ ሶስት ጊዜ እመግባለሁኝ
ብሎ በመወሽከት በይፋ አበሰረኝ፡፡
ከጫካ መምጣቱን ከቶውን ዘንግቸ
ሶስት ጊዜ ልበላ አፌንም ከፍቸ
እድገት ብልጽግና ስራን ተመኝቸ
ብራወጥ ብራመድ ብጥር ብንቀሳቀስ
ከሞሰብ እነጀራ ሌማት እሚቆረስ
በፍጹም ከቤት ውስጥ ጠፍቶ እሚቀመስ
ይሄው አሳለፍኩት የህይወቴን ገሚስ፡፡