የኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት አረፉ

Ali Sirajየኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል  በመሆን እያገለገሉ የቆዩት አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት አረፉ፡፡ አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት ያፉት ዛሬ  ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ/ም ማለዳ በአዳማ በኦህዴድ ስብሰባ ላይ አንዳሉ በድንገት ህመም ተሰምቷቸው ወደ ሆስፒታል እየሄዱ እንዳለ ሆስፒታል ሳይደርሱ ህይወታቸው ሊያልፍ እንደቻለ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አቶ አሊ ሲራጅ የ 46 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ኦህዴድ/ኢህአዴግን ወክለው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ  ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድረው ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡