ሰበር ዜና፤ የፕሬዝዳንት ኦባን የኢትዮጵያ ጉብኝት በመቃወም ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ በዋይት ሀውስ ተካሄደ

በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ሊያደርጉት ያቀዱትን ጉብኝት በመቃወም እጅግ ደማቅና የተዋጣለት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። እነዚሁ ሰልፈኞች ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ ሥልጣን ከመውጣታቸው በፊት በአፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲያዊና የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እንደሚያደርጉ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ በአጽንኦት ጠይቀዋል። ኢትዮጱያ ውስጥ የወያኔ አገዛዝ በ90 ሚሊዮን የአገሪቱ ሕዝብ ላይ የጫነውን አፋኝና አምባገነን አገዛዝ የአሜሪካ መንግሥት መርዳት እንደሌለበት ሰልፈኞ ቁጣቸውን ገልጸዋል። ከዚህም በማያያዝ ሰልፈኞቹ በፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጭፋ፣ ሰቆቃ መፈጸም፣እስር፣ከስራ መፈናቀልና የተለያዩ በደሎች በመዘርዝር የአሜሪካ መንግሥት መቆም ያለበት ከተበደለውና ከተጨቆነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንጅ ከገዳዩና ከአራጁ ከወያኔ ጋር መሆን እንደሌለበት አበክረው በመግለጽ ፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ሊያደርጉ ያቀዱትን ጉብኝት እንዲሰርዙ ጠይቀዋል። በዚህ ታሪካዊና ደማቅ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ የተነሱ ፎቶግራፊችን ይመልከቱ።

80 70 60 50 40 30 20 10