ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
(የኤዲተሩ አስተያየት) የወያኔ ጉልቻዎች ቦታቸውን ተለዋወጡ ነው የሚባለው ። ከመላዋ ኢትዮጵያ 547 የወያኔ ፓርላማ መቀመጫዎችን ሙሉ በሙሉ ፤ አባሪ ተባባሪ በመሆን ሁለት ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ያዘረፈ ግለሰብ ነው ነው አሁን የሰብአዊ መብት ለማስጠበቅ የተሾመው ? እንዴት ያለ ቀልድ ነው ? ወግ ወጉ ተይዞአል ፤ ከመቼ ወዲህ ነው ወያኔያዊው ስርአት ሰባዊ መብት አስከብሮ ወይም አክብሮ የሚያውቀውና ነው ። ሰባዊ መብትን የመሰለ ታላቅ ስራ ፤ ለድምፅ አዘራፊ የሌባ ተባባሪ ሹመኛ አሳልፎ መስጠት ማለት ፤ገንዘቤን ጠብቅልኝ ብሎ ለሌባ መስጠት ማለት ነው ። የሰባዊ መብት ጥበቃ አከናወነ ተብሎ ስሙ ተነስቶ የማያውቀውን ጉልቻ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ፤ በሌላው የወያኔ ጉልቻ ድምፅ አዘራፊ ፤ ኮሮጆ አስገልባጭ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ለወጡት ። ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም የሚባለው ለእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ነው ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡
ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ያለፉትን ሁለት አጠቃላይ ምርጫዎች ያገለገሉ</>የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡ ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ 547ቱንም የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉበትን የ2007 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ በመምራት በሕግ የተፈቀደላቸውን የሥልጣን ዘመን አጠናቀዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የዶ/ር አዲሱን፣ የምክትል ኮሚሽነርና የኮሚሽን አባላት ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በዶ/ር አዲሱ ተተክተዋል፡፡