ሊቢያ ውስጥ የተገደሉት ኢትዮጵያዉያን ሰማዕታትን አስመልክቶ የተደረጉ ሁለት መታሰቢያዎችን በተመለከተ አጠር ያለች ዘገባ

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያኖች የተለያዩ የፀሎትና የመታሰቢያ ዝግጅቶችና አገልግሎት ሰትተዋል። ነገር ግን በሊቢያ የተሰውትን የኢትዮጵያውያ ሰማእታትን ምክንያት በማድረግ፤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሪቬው ባደረገው ተጨማሪ ክትትልና በሰጠው ዘገባ ብዙ ሌሎች አስገራሚ ክስተቶች ታይተዋል። በ May 10, 2015, ዋሽንግተን ዲሲ ብሔራዊ አደባባይና በ June 14, 2015 በKena Temple የተደርጉት ሕዝባዊነትንና ሰባዊነትን ያመላክታሉ የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቶት ነበር። ለዚህም ቅድመ ግምት ምክንያቱ የተለያዩ የሃይማኖትና ማህበራዊ ተቋማትን የሚወክሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኙበታል የሚል ነበር።

የመጀመሪያው ዝግጅት ( May 10, 2015) ፣ ዋሽንግተን ሞኑመንት አደባባይ ላይ ሲደረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። ይህንን ያልፈለጉ የወያኔ ተላላኪዎች ለማደናቀፍ ማስታወቂያውን ወደ ቆሻሻ በመጣል፣ “የፖሊቲካ ነው” የሚል የሐሰት ወሬ በማስወራት ሙከራ አድርገዋል። በመጀመርያ ባደርገውነው ማጣራት በዋሽንግተን አካባቢ ያሉ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት አብረው ዝግጅቱን ለማድረግ የሚል ሀሳብ ነበር። በዝግጅቱ ሂደት ላይ አንዳንድ ካህናት “የኢህዴግን መንግስት የሚነካ ከሆነ ከመንግስት ጋር ያገጨናል”። ስለዚህ መታሰቢያው ስለ ሰማእታቱ ISIS ን መርገም ብቻ እንጂ ሰማዕታቱ ከሀገር እንዲወጡ ያስደረገውን መንግስት መንካት ለአንድነት መጥፎ ነው በሚል ማደናገሪያ ምክንያቶች ተለዩ።

ሁለተኛ ደግሞ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ጉባኤ በሚል ስም በዋሸንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የተቋቋመው አዲስ ድርጅት በዶ/ር መምህር ቀሲስ ዘበነ ለማ የሚመራ እንደሆነ ነው። በ 9001 Arlington Blvd Fairfax VA, Kena Temple የተደረገውን June 14, 2015 የመራው ራሱ መምህር ዘበነ እንደሆነ ነው።

አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን አባት “እኔ ቆራቢ ነኝ። ያልሆነ ነገር በጭንቅላቴ ቋጥሬ መዋልና ማደር ህሊናዬ አይፈቅድም። ባለፈው በዋሽንግተን ሞኑመንት ላይ በተደረገው ላይ ተስፋየ መቆያና አንተ (መምህር ዘበነ) እኛ አገር ቤት የተለየ ስራ አለን፣ ይህ ስራችንን ያበላሽብናል ብላችሁ እንዳልተገኛችሁ ስማቻለሁ። ይህ የሰማሁት እውነት ነው? ወይስ ውሸት ነው?ብለ ጠየቁት። ጥይቄና መልሱን በጥሞና ለማዳመጥ የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ። http://www.mereja.com/amharic/456601 ከላይ እንደሰማችሁት መምህር ዘበን የአዛውንቱን ጥያቄ አፍኖና ደምስሶ ለማምለጥ ሞከረ። እኒህ አዛውንት ተልእኴቸው እውነትን ማወቅ ነውና “ይህ ለሁሉም የሚጠቅም ነውና አድበስብሰህ ልታልፈው አይገባም” በሚል አባታዊና ክርስቲያናዊ በሆነ ድምጽ ተቋቋሙት። የሚገርመው የመምህር ዘበነ መልስ የሰማእታቱን ጉዳይ እሱው ጀማሪና እሱ ብቻ እውነተኛ እንደሆነ ለማሳመን ሞከረ።
ስለዚህ የመጀመሪያውን መታሰቢያ ( May 10, 2015 ዋሽንግተን ሞኑመንት ) ላይ የተደረገው የቪድዮ ቅንብር እና ሁለተኛውን በመምህር ዘበነ የተቀነባበረውን በJune 14, 2015 በKena Temple የቪድዮ ማስረጃዎች በማነጻጸር የትኛው የቤተ ክርስቲያናችን ድምጽ፣ የህዝቡን ብሶትና የእግዚአብሄርን ክህነታዊ ተልእኮ የሚያሳየው የሚለውን ለመፍረድ ይቻል ዘንድ
በዕለቱ (May 10, 2015, ዋሽንግተን ሞኑመንት) የተደረገውን ቪድዮ በመመልከት ተመልካች ይችላል። የተቀረፀውን ሁለት ክፍል ቪድዮ ይመልከቱ።
ዋሽንግተን ብሔራዊ አደባባይ ላይ የተደረገው ዝግጅት: ክፍል 1

ዋሽንግተን ብሔራዊ አደባባይ ላይ የተደረገው ዝግጅት: ክፍል 2

የዶ/ር መምህር ቀሲስ ዘበነ ለማ ንግግር ( በ 9001 Arlington Blvd Fairfax VA, Kena Temple) ቀጥሎ ያለውን ሰንሰለት በመጫን ይመልከቱ:-
https://www.facebook.com/misikir.tadele.1/videos/912237365500211/

ይቀጥላል:-