‹‹ለህዝባዊ እምቢተኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል›› የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት
በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሁለት አብይት የትግል ስልቶች አሉ፡፡ አንደኛው ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትና ህግጋት ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ የሚደረግ ህዝብን ያሳተፈ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫ ሲባል ዝም ተብሎ ለማስመሰልና የአምባገነኖችን የስልጣን እድሜ ለማራዘሚያነት የሚደረገውን አይጨምርም፡፡ ምርጫ ሲባል ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ያሉት ነው፤ መመዘኛዎችን ባሟላ መልኩ የሚደረግ ምርጫ፣ ምርጫ ሊባል ይችላል፡፡ አምባገነን ስርዓቶች ምርጫ ሲያደርጉ አስተውለናል፤ ግን የይስሙላ ነው፡፡ […]![]()