የተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋምና አማራጭ መርሆዎች

ኢትዮጵያ ለአምስተኛዉ ብሔራዊ ምርጫ መሰናዶዋን እያገባደደች ነዉ።በየማሕበረ-መገናኛዉ ዜዴዎች የምናነባቸዉ አንዳድ ፁሁፎች «ዉጤቱ አስቀድሞ የታወቀ» እያሉ ቢተቹትም ገዢዉ ፓርቲም፤ ተቃዋሚዎቹም፤ አስመራጭ መራጮችም ለምርጫዉ መዘጋጀት፤መከራከር፤መነጋገራቸዉ እንደቀጠለ ነዉ።