በእግዚያብሔር ህግ ላይ ድርድር የለም!
በእግዚያብሔር ህግ ላይ ድርድር የለም
“………..እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥ ……..” የይሁዳ መልዕክት 1፡12
ሰሞኑን ከእምነቱ ተከታዮች እውቅናና ውክልና ውጭ ለወያኔ ባደሩ “አስታራቂ” ተብየዎች አማካይነት በሚስጢር ፊኒክስ ውስጥ በህጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ሲኖዶስና በህገውጡ የአባ ገብረመድህን “ሲኖዶስ” መካካል ሲካሄድ የነበረው ውይይት ለወያኔ በሚያመች ሁኔታ መደምደሙን ከስፍራው የሚናኙ ወሬዎች ያመለክታሉ። ከሁሉም በላይ የእግዚያብሔር ህግ እንደ ዓለማዊ ህግ በፖለቲካ ድርድርና ሰጥቶ መቀበል እንዲሁም “በእከከኝ ልከክልህ” የሚለወጥና የሚሻር ነገር እንዳልሆነ እየታወቀና “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም” የሚለውን የወንጌል ቃል ደፍጥጠው በቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ እንደ አርዮስ ክህደት የሚቆጠር ከፍተኛ ክህደትና ደባ ፈጽመዋል። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ህግንና ቀኖና ጥሰው በነፍጥ አንጋቾች መንበረ ፓትርያርኩ ላይ የተቆናጠጡት አባ ገብረመድህን ወርደው ንስሃ ይግቡ፣ ትክክለኛው ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው ይመለሱ በማለት ፋንታ የተጭበረበር የፖለቲካ ውሳኔ ማሳለፋቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤተክርስቲናኒቷን አማኞች እንደሚያበሳጭ ይታወቃል።
በአገራችን የተጣላ ሰው ለማስታረቅ እንደምሳሌ ሲነገር የኖረ ብሂልን እዚህ ላይ ማቅረብ ይጠቅማል። ይኽውም አንደ ሰው ሌላው ሰው በድሎት፣ ጎድቶት፣ ገንዘቡን ቀምቶት ከኖረ በኋላ በዳይ ለመታረቅ ቢፈልግ በመጀመሪያ ማድረግ ያለበት የቀማውን ገንዘብ መመለስ፤ ከዚያም ይቅርታ መጠየቅ በመጨረሻም መካስ ናቸው። አባ ገብረመድህን የቀሙትን መንበረ ፓትርያርክነት ሳይመልሱ ምን አይነት እርቅ ነው ሊደረግ የሚችለው? አታራቂዎችስህ ይህ ተራ ጸብ አለመሆኑን እያወቁና የእግዚያብሔር ህግ መጣሱን እየተመለከቱ አለማዊና ፖለቲካዊ መርዛቸውን ለምንድን ነው በየኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ላይ ለመርጨት የሚፈልጉት? በእግዚያብሔር ህግ ላይ ድርድር የለም። ወንጌሉ የሚያስተምረን “ እውነቱን እውነት በሉ፤ ሀሰቱንም ሀሰት በሉ” ነው። እርቅና ሰላም የቤተክርስቲያናችን የማዕዘን እራስ ናቸው። እርቅና ሰለም ግን እውነቱን ይዞ፣ ፈሪሃ እግዚያብሔርን ተመልክቶ እንጅ መካሄድ ያለበት በስልጣን ላይ ያለውን ለማስደሰት የሚደረግ ግን ቤተክርስቲያኒቷን በእጅጉ የሚጎዳና የህዝበ ክርስቲያኑን እምነት የሚያቀጭጭና የሚያጨልም ነው። በቅርቡ በዚህ ርዕስ ላይተጨማሪ ዘገባ ይቀርባል።
እነዚህ በስደት ያሉ አባቶቻችን ሃይማኖታችንነን እንድንጠብቅና በተስፋ እንድንኖር ያደረጉን ነበር። አሁን ምን ተገኝተቶ ነዉ በእርቅ ሰበብ ምእመናኑን የሚበትኑት? እርቁ አባገብረመድህን በጠመኝጃ የያዙትን መንበር ከመልቀቅ ዉጭ ምን የሚያስማማን ነጥብ ይኖራል? አባ ገብረመድህንና መለሰ ደግሞ ወንበር ከሚለቁ ሞታቸዉን ይመርጣሉ። የሚገል ወንድ ጠፍቶ ነዉ እንጂ….አባቶች ከሰይጣን ጋር ተደራድራችሁ ንስሃ አስገብታችሁ ዓለምን ብታድኑ ይቀላል። ከአባ/አቶ/ ገብረመድህን ጋር ስምምነት ከመድረስ ይልቅ በቋፍ ያለዉን ምእመን ከቤተክርስትያን አታርቁት። ለመናፍቅነትም አትዳርጉት!!!!!!!!!
ከኢትዮጵያ የመጡት የወያኔ ሰራ አስፈጻሚዎች እንጅ የሐይማኖት ሰዎች ናቸው ማለት አይቻልም። እነዚህ የአባ ገብረመድህን አጃቢዎች መስቀሉን፣ ካባውን፣ በትረሙሴውን፣ መጠሪያውንና ሌላም ሌላውን ይዘዋል ግን ከሚናገሩትና ከሚሰሩት ስንመለከት ምንም የሃይማኖት አባትነት የላቸውም። ለአለማዊ ገዥዎች ለሆዳቸውና ለጥቅማቸው የተንበረከኩ እንጅ። በዚህም ምክንያት ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የሚፈይዱት አንዳንችም ነገር የለም። ማፈሪያዎች ናቸው።
ማንን እንመን:ተቸገርን:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ከሁሉም በላይ ፈጣሪን አመሰግናለሁ:: ከፖለቲካ አንጻር ሳይሆን እውነቱ ግን የወደፊቱ የቤተ ክርስቲያን አመራር እንዴት ይሁን የሚለው ላይ ነው:; እንደሚታወቀው ሁለቱም አባቶች በድሜ ገፋ አድርገዋል ታዲያ በዚሁ አሁን ባለው የተከፋፈለ ሁኔታ መቀጠል የለበትም ብየ ፍጹም አምናለሁ:: አባቶች አሁኑኑ ተነጋግረው መስመር ካልያስያዙት ነገ ጸጸት ነው እንዲሁ ወያኔ እንደዘለለበት መቅረቱ ነው እንዲያውም ከበርሃ ይዞት እንደመጣው ለማፍረስ ወደሁዋላ አይልም:: ስለዚህ ያባቶች አንድ እርምጃ ሊመሰገን የሚገባው ነው ብየ አምናለሁ:: እኛው ካልታረቅን ማንም ላስታርቅ የሚል ጳጳስ ከውጭ አናገኝም ማለት እህት ቤተ ክርስቲያናት ፍላጎት ያሳዩ አልመሰለኝም ስለዚህ እኛው እንታረቅ ነው የምለው::ለማስታረቅ መከራ ያደረጉት ወገኖች ከልባቸውም ሆነ ከሆዳቸው ከኔ የተሻለ አድርገዋልና በግሌ ከልቤ አመሰግናልሁ:: ኣባ ጳውሎስ የሚዎነጀሉበት ሁሉ እውነት ከሆነ ነገ እሳት ይጠብቃቸዋል ይህንን ደግሞ ከኛ የተሻለ ያውቁታል:: እኔ የሚመስለኝ ወያኔ ክሁዋላ ሆኖ ዋ ትለቅና ጉድህን ነው የማፈላው እያለ ባስነካቸው ማኖ እያስፈራራቸው ይመስለኛል:: ለሳቸውም ዸሎት ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል የወያኔ እስረኛ በመሆናቸው:: ለሁሉም ጊዜ አለው እንደተባለው የድንግል ልጅ በቃ ይበለን:: ለሁሉም ወገኖቸ እግዘአብሄር ኢትዮጵያንና ወገኖቻችን ሁሉ ይባርክልን ከዘመኑ የወያኔ የጥላቻና የ እናጥፋው ዘመቻ ይጠብቅልን
ኣሜን
ይህ ድርድር የተካሄደው በቀድሞ የደርግ ባለስልጣናት በነበሩ ኮሙኒስት አቀንቃኞች ጠንሳሽነት ስለሆነ የሰፊውን የአኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት አያንጸባርቅም። ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ በአንድ ታዋቂ ካቴደራል ውስጥ ሲካሂድ የሰነበተው ድራማ ፍንጭ የሰጠ ነበረ። የሲኖዶሱን መቀመጫ ና መንብረ ፓትርያርኩን ወደዚያው ማሽጋገራቸው፣ እንዲሁም አፍቃሪ ደርግ/ወያኔ የሆኑ የቦርድ አባላት በማስመረጥ ምዕመናን በመከፋፈል እያደረጉ ያለው ሥውር እንቅስቃሴ ለስደተኛው ህዝብ በቂ የማንቂያ ደወል ሊሆን በተገባ ነበር። ኮሙኒስቶች ጸረ እግዜብሄር አቋማቸው የት እንዳደረሳቸው እየታወቀ የኛዎቹ ዘመናዊ ጓዶች/ታጋዮች ‘ዶሮ ማታ’ ሊሉን እየቃጣችው ነው። …
በሃገራችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ቀንና ማታ እያነባ ቀኖናውን የሚጠብቅለት አጥቶ በናንተ ይጽናና ነበር። አሁን እናንተም ከወያኔ ካበራችሁ እግዚአብሔር ለእኛ ሰው ይሰጤናል። ከሁሉም የሚበልጥ አለና! አሁንም አስቡበት የበለጠ ትቆስላላችሁ እንጂ ምንም መብት አታገኙም። የበለጠ ጤናችሁን ታዉካላችሁ:: እንደ ባሪያ ሊገዙዋቹ ፈልገው ነው። ያላችሁን ነጽኣነት አታስረክቡ፡ ያገኘነውን ፅጋ አታስረክቡ:: የሚያሳዝን ስራ አትስሩ። ህዝቡን አታሳዝኑ:: ነገር ግን አባ ገብረ መድህን ጵጵስናው ለቀው ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚረከቡ ከሆነ ጥሩ ነው፡ ያለበለዚያ ቆስሎ ማቁሰል ነው። ዕድሜ ማሳጠር ነው:: በጣም ጥንቃቄ ያሻል:: በስደት ያላችሁት የኢትዮጵያ ህዝብ መከታ ናችሁና አታቃልሉት::
እውነት ከላይ ያነበብኩት እና የሰማሁት እውነት ሆኖ ከሆነ በእጅጉ ከማሳዘንም አልፎ እጅግ አደገኛ ክህደት አድርጌ እወስደዋለሁ:: ምክንያቱም ችግሩ እስከ ዛሬ የእግዚያብሔር ህግን ማክበር ሳይሆን ስልጣን ብቻ ይፈለግ እንደነበረ ነው የሚያሳየው….ለማንኛውም የመጨረሻውን ድምዳሚያቸውን በጉጉት እጠብቃለሁ::
እግዚአብሂር ኢትዮጲያን ይጠብቅልን !!
በጣም የሚያንገበግበኝና የሚያናድደኝ ነገር አለ። “አስታራቂ” ነን ብለው እራሳቸውን የሰየሙ ጥቂት ግለሰቦች ከአርባ ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላትን ቤተክርስቲያን ህልውና ለመወሰን ማነው የፈቀደላቸው? Who gave them the mandate? እነዚህ አስታራቂ ተብዬዎች ምእመናን አልመረጧቸውም፣አልወከሏቸውም፣አይቆጣጠሯቸውም። እንደምንሰማው ከሆነ ከአስታራቂ ተብዬዎቹ ከፊሎቹ ከወያኔ የጥቅም ተቋዳሽ የነበሩ የውስጥ አርበኞች ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ከወያኔ ለጥቅማጥቅም ተስፋ የተገባላቸው ናቸው። ምእመናንም አስታራቂ ተብዬዎችን እራሳቸውን ስለደበቁ ማንነታቸውን ለማወቅ አልቻልንም። የእነሱን አጀንዳ ጠንቅቆ የሚያውቅ የለም።ከዚህም በተጨማሪ ድርድሩ ከህዝብ ተለይቶ በሚስጢር መካሄዱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ያደርገዋል።የዚህ ድርድር ትልቁ ውድቀትና ጥፋት በነዚህ ምክንያቶች ይመስለኛል።
ይድረስ ለብጹእ አቡነ መልከጻዲቅ፣ ለብጹእ አቡነ ኤልያስ፣ ለመላከ ገነት ገዛኽኝ፣ ለሊቀ ክህናት ምሳሌ
እውጭ ያላችሁ አባቶቻችን የህጋዊው ሲኖዶስ አባላት እናንተም አለወንጀላችሁና ጥፋታችሁ “ቀኖናውን ጥሰናል ብላችሁ ፈርማችኋል ወይ??? የተደበቀ ሳይገለጽ የሚቀር የለምና ጊዜ ሳትወስዱ ለምዕመናን እውነቱን ግለጹልን። የማሸነፉን እውነት እግዚያብሔር በእጃችሁ ሰጥቷችሁ፤ በዚህም ምክንያት ከአገር ተሰዳችሁ እንደ ውዳሴ ማርያም ለሃያ ዓመታት እውነት ነው ብላችሁ ስትደግሙት የኖራችሁትን ያን የመሰደድ እውነት የሆነውን የቀኖና መጣስ አሳልፋችሁ “አር ይዞና” ሄዳችሁ ለአውሬው ሰጥታችኋል እየተባለ እየተወራባችሁ ነውና በአስቸኳይ እውነቱን ከእናንተ አንደበት መስማት እንፈልጋለን። በነጻነት አገር እየኖራችሁ እውነት እንዳትናገሩ አዳካሚው ቡድን የመለስ ዜናዊን ልጓም አፋችሁ ውስጥ አስገብቶባችሁ ከሆነ አሁንም ጨለማ ውስጥ ናችሁና ፈጥችሁ ወጥታችሁ እውነቱ ግለጹት። ‘ከምን ጋር የዋለች ምን ተምራ መጣች’ እንደሚባለው ከከሃዲዎች ሸንጎ መዋል እናንተንም እንዳያሰምጣችሁ እንማጸናችኋለን። ሌላው እንኳ ቀርቶ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ንስሃ ሁኗቸው እውነቱን ሲገልጹት “ፓትርያርኩን በእኔ ፊርማ አባርሬያለሁ” ብለው እየመሰከሩ ይህንን እውነት ማጣፋቱን ምን ትሉታላችሁ? እረሳችሁት እንዴ በየአንዳንዷ ንግግራችሁ “ንቡረዕድ” ተብየው ስልክ እየደወለ ከአባ ጳውሎስ በእጅ አዙር አመራር ስትቀበሉ ምን ተሰማችሁ? እርቅን ማንኛችንም እንፈልገዋለን። ነግር ግን የቤተክርስቲያኑዋን ህግ የጣሰ፣እውነትን ያዳፈነ እርቅ ሳይሆን “ምርቅ” ነው ። አይ? “አር ይዞና” ????
ህጋዊና ህገ ወጡ ሲኖዶስ በማለት ያልተከፈለችውን አንዲት ሃይማኖትና ተክታዮቹዋን መነጣጠል ከሁለቱ የአንዱ ደጋፊ ወይም ተከታይ መሆንን ያመለክታል። ሕጋዊ ተብዬዎች በአውሮፓና በአሜሪካ የሚንቀባረሩት ጳጳሳት ማን እውቅና ሰጣቸውና ማን መረጣቸውና ነው ራሳቸው በፈጠሩት ሲኖዶስ ራሳቸውን በራሳቸው ሹመው እያውደለደሉ የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆን የሚያናፉት? አባ ገብረመድህንና ተከታዮቻቸውስ በራሳቸው ህልም ቅዠት ዉስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የራሳቸውን ፊልስፍና ፈጥረው ለሆዳቸው አድረው እንዲህ የሚበጠብጡን። የቱን ያህል ቢሩዋራጡ የትም ቢሰበሰቡ ሁለቱንም ማን ፈለጋቸውና እንዲህ መከራቸውን የሚያዩት?
ከሁለት ተከፍሎ፣ የውስጥና የውጭ በመባባል ተራርቆ ያለ ፍቅር፣ ያለ ሰላምና ያለ እርቅ ለሃያ ዓመት መኖር፣ ሌሎች እልህ አስጨራሽ የቤተ ክርስቲያኗና የኢትዮጵያ ችግሮች ታክለውበት ይቅርና፣ ብቻውንም እንኳ ቢሆን ለአደጋው ጥልቀትና ስፋት በቂ ምክንያት ይሆናል። ጊዜው እየረዘመ በሄደ ቁጥር ችግሩ የአስተዳደር ብቻ ሳይወሰን፣ በኢትዮጵያና በውጭው ዓለም በአያሌ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናን ያሏትን፣ የአንዲት ርትዕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ ዕምነት ሊያሰጋ ይችላል። ቀኖናው የዛሬ ሃያ ዓመት ተጥሷል። ከዚያም ወዲህ በየምክንያቱና በየቦታው እየተጣሰ ነው። የባሰ ጥፋት ሳያደርስ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ ሊቀጥል ይችላል? በኢትዮጵያም ሆነ በውጭው ዓለም የቤተ ክርስቲያኗን ዕምነትና ሥርዓት ማስከበሪያው፣ ደኅንነቷና አንድነቷን መጠበቂያው፣ ትምህርቷንም ማጠናከሪያውና ማስፋፊይው ሠዓት አሁን ነው።
የሚስሩትን አያውቁምና ይቅር በልዋችው ለዝያውም የሃይማኖት አባቶች ሆነው እግዚኦ የሚያሰን ዘመን መታብን ሃትያታችን በዛ ይሆን?ይቅር ይበለን….
Please lets give some credits to the Fethers in the West for giving us the spiritual truth for over 20 years, we need to suport them so they can do more. These Fathers have given us all they can for NOTHING or reward. (it is so easy for us to judge).
እነዚህ አባቶች ማለቲም በዚህ አገር ሃገር ያሉ ምንዚም ሃይማኖታችውን አይክዱም አይዞትችሁ እንበላችው. ሃይማኖት አንድ ነው
Many of us happy to hear the good news to bring the Church to peace and reconcilation. In the end the woyane appointed aba paulos and derg appointed merkorewos should realise they are gambling over 45 million orthodox christians.
The challenge for peace and reconciliation seems to me both preached hate over the last 20 years and divided the innocent followers into different camps. Lots of work needs to be done between now and July if these guys are serious. Among many they should encourgage their followers, prists and sunday school group from the two camps to work together such as celebrate big feasts together. Without these ground work its impossible to bring true reconciliation! I doubt whether or not these guys work on these.
Thank those who work hard to bring these groups together for the sake of the future generation.
እረ እባካችሁ የሆነውን ሳንረዳ ተሳስተን ሰው አናሳስት:: ምንም የተደረገ ስምምነት የለም:: ላለመስማማት ነው የተስማሙት. ሁለቱ ሊስማሙ የሚችሉት መፈንቅለ መንበር ያካሂዱት መንበሩን ለባለ መንበሩ ለአቡነ መርቆሪዎስ ሲለቁ ብቻ ነው:: በስደት ያሉት አባቶች ይህን አስረግጠው በመናገራቸው ሊስማሙ አልቻሉም:: ሁኔታው ይህ ነው:: ወንድሞቼ እህቶቼ እንዳንሳሳት:: መግለጫቸው ለምን እንዳልወጣ አልገባኝም::
ብጹእ አቡነ አብሳዲ ማረፋቸውን አልሰማችሁም? ያረፉትን አባቶችን ሳናስታውስ ስላሉት ለምን እንጨነቃለን?
http://dejebirhan.blogspot.com/2012/02/blog-post_20.html
አሁን እዚህ እርቅና ሰላምን ተቃውመው ,ጠብና መለያየትን ደግፈው የሚጽፉት ሰዎች ማናቸው? . … የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድ ብትሆን, የተጣሉ ቢታረቁ, ሰላም ቢወርድ , ቤተክርስቲያኗ አንድ ብትሆን የሚከፋቸው እነማን ናቸው? . . እዚህ መንፈሳዊ ወይም ኦርቶዶክሳዊ መስለው የሚጽፉት ሁሉ , የኢትዮጵያም ሆነ የቤተክርስቲያን አንድነት የማይጥማቸው .. በርግጠኝነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች የሆኑ አይደሉም:: ስለዚህ የሌላ ዕምነት ተከታዮች – አጉል ተቆርቋሪ በመምሰል ለምን ታረቃችሁ ብላችሁ መጻፋችሁን እናውቃለን:: የሚሰማችሁም የለም:: እናንተ ደስ እንዲላችሁ ተብሎ , እግዚአብሄርን ማሳዘን ማንም አይፈልግም:: እርቅ, ሰላም አንድነት የ እግዚአሔር ነው .. ጠብና መለያየት የሰይጣን ነው:: እኛ የ እግዚአብሔርን መርጠናል: .. እናንተ የፈለጋችሁትን ምረጡ .. ቤተክርስቲያናችንን ግን ለቀቅ አድርጉልን .. የኛ ሳትሆኑ .. የኛን ተለያይቶ መሞት ለምን መፈለጋችሁን እናውቃለን:: መቼም ቢሆን የሚያሸንፈው እውነት ነው:: የቀረችንን ጥቂት ዕድሜ እስቲ ለንስሃ እናድርጋት? የኦርቶዶክስን ጉዳይ ለኦርቶዶክስ ብቻ ተዉልን::
ወይ የሰላም ጠላቶች …. አሁን አንዳንድ ፖለቲካ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ፖለቲከና የሆኑ የድሮው የኢህ አፓ ሳይሆን , አሁን እንደ ንግድ ፈቃድ የያዙትን ስም ይዘው ምንም ሳይሰሩ .. ከኮምፒውተር ጀርባ ቁጭ ብለው በሌላው ኪሳራ ከበሮ የሚመቱ .. ለዛሬዋ ኢትዮጵያ መውደቅ ዋነኛ ተጠያቂ የሆኑት, ወያኔ እንዲህ ለሚጫወትባት አገራችን, ተባብረን እንኳን አንድ ነገር እንዳናደርግ, በፕሮፓጋንዳቸው የሚያደነቁሩን .. ሰላም እርቅ ሲባል ኡ ኡ የሚሉት የስመ ኢህ አፓዎች . ናቸው እንዲህ የቤተክርስቲያን አንድነት ያስደነገጣቸው::
እኛ እኮ የምናውራው ስለራሳችን ቤተክርስቲያን ነው:: ኢ ህ አ ፓ ደግሞ ኮሚኒስት ነው – ስለዚህ ቤተክርስቲያንን ቢቃወም አይደንቅም:: ያለ ምንም ስራ , አንድነት ሲፈጠር, ህብረት ሲፈጠር .. እንኳን በሃይማኖት መካከል ቀርቶ , የፖሊቲካ ድርጅቶች እንኳን አንድ ላይ ሆነን እንታገል ሲሉ .. ቀዳሚ ተቃዋሚ ኢህአፓ ነው:: [ቢያንስ ስሙን የያዙት ልበል እንጂ – ዋናው ኢህአፓ ማ በኛ ጊዜ ቀረ) …. ለመሆኑ እነዚህ ኢህ አ ፓ ነን ባዮች (በተለይ አውሮፓ አካባቢ ያሉት) እነሱ ሊቀመንበር ካልተባሉ, እነሱ ፕሬዚዳንት ካልተባሉ .. የሌላው መሰባሰብና መነጋገር ለምን ያስፈራቸዋል? መልሱ እንድ ነው:: ሌላው ከተጠናከረ .. ተዋዋሚው አንድ ከሆነ , ቤተክርስቲያን እንድ ከሆነች እነሱ ቦታ የላቸውም:: ቅንጅት እንዲፈርስ ሲታገሉ የነበሩ እኮ እነሱ ናቸው . ዛሬ ደግሞ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድ እንዳትሆን, አንድ ሆና በውስጧ ያለውን ችግር እንዳትፈታ እንቅፋት ለመሆን ሲዳክሩ ይታያሉ:: ኮሚኒስቶች .. ክርስትናን ለቀቅ አድርጉት:: ለምን ራሳችሁን አትችሉም?
ሳምሶን – ከሚኒሶታ!
አንድ የማወቀው ሰው በዚህ ር ዕስ ላይ እርቅ አያፈልግም, እያለ ሲጽፍ ቤቱ ሄጄ አገኘሁት:: እርቅ አያሰፈልግም, ታረቁ የሚል ሁሉ ወያኔ ነው እያለ ሲበሳጭ አግኘሁትና የጽፈውንም እዚሁ አስተያየት መስጫ ላይ እንደ ደህና ነገር አሳየኝ:: .. ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ባከብርም, እኔ እስከማወቀው ድረስ ግን ይህ ጓደኛዬ አሜሪካ ከመጣ 28 ዓመቱ ሲሆን, አንድም ቀን, እደግመዋለሁ. አንድም ቀን ቤተክርስቲያን ሄዶ አያውቅም, ጾምና ጼሎት የሚባል አያውቅም:: አባቶቻችን በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ውሃ ይጠጣል የሚሉት ለዚህ ነው:: ግን ለሰላም ና እርቅ የቆማችሁ ሁሉ ቀጥሉበት . ሰውን እናስደስት ብላችሁ እግዚአብሔርን ስታሳዝኑ እንዳትገኝ:: አምላካችን የፍቅር አምላክ ነው:: የአንድነት አምላክ ነው “ወንድሞች በህብረት ቢቆሙ መልካም ነው” አለ እንጂ “ተለያይተው ቢኖሩ መልካም ነው” አላለም:: ማንም ምንም ሊጽፍ ይችላል:: ሊፎክር , ስም ሊያጠፋ , ሊሳደብ ይችላል … ክርስቶስም ለ እውነት ተሰድቧል, ጳውሎስም ጺሙ ተነጭቷል .. ወይም ለወንጌል መከራ ደርሶበታል:: የሃይማኖት አባት የ እግዚአብሔርን ህግ ለማሳየት እንጂ ለመቃወም አይቆምም:: እርቅና ሰላምን የሚቃወሙ ሁሉ የቤተክርስቲያን ሰዎች አይደሉም .. ይህንን እወቁ .. ብዙዎቹ እምነት የላቸውም , ሌሎቹም የሌላ እምነት ተከታይ ናቸው:: እውነት አርነት ያወጣችኋል:: አስታራቂዎችም .. በዘመናችን የሰላም ሃዋሪያ ተብላችሁ ታሪክ ያስታውሳችኋል:: አትፍሩ, አትደንግጡ:: የፖሊቲካ ድርጅቶች እንኳን ለምሳሌ አንድነት ፓርቲ አንዱ አጀንዳው “ብሄራዊ እርቅ” ማድረግ ነው:: ለቤተክርስቲያናችን ሲሆን ብሄራዊ እርቅ ለምን ተጠላ? ይህ የሚያሳየው የኛ አንድ መሆን የሚጎዳቸው ሰዎች እንዳሉ ነው:: እናዝናለን:: አንድ ከመሆን የሚያግደን የለም:: የክርስቶስን እንጂ የሰውን ቃል አንሰማምና::
ዋሽንግተን ዲሲ
እኔ የሚገርመኝ, ከላይ ከጻፉት መካከል እርቅና ሰላምን በመጥላት የጻፉት ሰዎች, በአንድ በኩል የወያኔ ተቃዋሚ ነን ይላሉ:: ለመሆኑ እርቅና ሰላምን ከጠላችሁ እንዴት የወያኔ ተቃዋሚ ነን ትላላችሁ? ወያኔም እርቅና ሰላም አይፈልግም – እናንተም አትፈልጉም:: ወያኔ ቤተክርስቲያኗን ተቆጣጥሮ መኖር ይፈልጋል – በተለይ አገር ቤት ያለችውን, እናንተም ቤተክርስቲያኗን – በተለይ ውጭ አገር ያለችውን ተቆጣጥራችሁ መኖር ትፈልጋላችሁ, ወያኔ ከቅንጅት, ከአንድነት ከመኢ አድ ወዘተ. መሪዎች ጋር ሰላም አልፈልግም , እርቅ አልፈልግም ብሏል, .. እናንተም ውጭ አገር ካለ ከማንም ጋር እርቅ አትፈልጉም, ..ወያኔ የተለየ ሃሳብ ያለውን ያስራል ይገድላል .. እናንተም [የአሜሪካና የአውሮፓ ህግ ይዟችሁ እንጂ] ብትችሉ ከማሰርና ከመግደል አትመለሱም , በየድረገጹም በብዕራችሁ ከመግደል ያላነሰ ስድብ ታወርዳላችሁ:: ወያኔ እኔ ያልኩትን ያልተቀበለ ጉዱ ነው ይላል .. እናንተም እኛ ያልነውን ያልተቀበለ ጉዱ ነው ትላላችሁ:: ለመሆኑ እርቅና ሰላምን የምትጠሉ እናንተ – ከወያኔ በምን ትለያላችሁ? ባይገባችሁና የፖሊቲካ አስተሳሰብ ድህነት ስላለባችሁ እንጂ, ቤተክርስቲያን አንድ ስትሆን ሃይል ይኖራታል, መንግስትም በቤተክርስቲያን ጣልቃ እንዳይገባ ማድረግ ይችላል:: ከኮምፒውተር ጀርባ ተደብቆ እርቅና ሰላምን ለማደናቀፍ መሞከር ጀግናም አያሰኝም, አገር ወዳድም አያሰኝም, ታጋይም አያሰኝም … ይልቁኑ ፈሪና ከፋፋይ ያሰኛል: እንጠላዋለን ከምትሉት ወያኔ በምንም አትሻሉም:: እናም ሌሎች ጼሃፊዎች እንደጤቆሙት … ቤተክርስቲያናችንን ለቀቅ አድርጉ:: ከወያኔ ያላነሰ ለአገር ነቀርሳ የሆናችሁት እናንተ ናችሁ::
ከኖርዌይ
ለአቶ “ደሴ አያልሰው”
የታወቁና የተከበሩ ሰውን ስም አዟዝረው ለመጠቀም መፈልግዎ በጣም ያስዝናል። አልተረዱትም ይሆናል እንጅ በአንባቢ ዘንድ የሚያስመዝንዎት የመልዕክትዎ ጭብጥ እንጅ አስተያየት ለመስጠት ከሚጠቀሙበት ስም አይደለም። ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባና ሰሞኑን በአባ ገብረመድኅን ህገወጥ ሲኖዶስና በህጋዊው ውጭ በሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ መካከል የተደረገውን ውይይት በማስመልከት የተሰጡ የተቃውሞ አስተያየቶች ሆድዎን የጎረበጥዎት መሆኑን ከአስተያየትዎ ተረድቻለሁ። የተቃውሞ ሃሳቦችንና ስድቦችን ለይተው የማያውቁ ከሆነ ከመለስ ዜናዊ ምድብ እንጅ ከማንም ሊሆኑ አይችልም።የስድብ ሰዎች ወያኔዎች እንደሆኑ የማያውቅ የለም። ይህንን ድርድር ተብዬ የተቃወሙ ስዎች ሰላምና ዕርቅ ጠልተው እንዳልሆነ ያውቃሉ። ማንኛቸውም ሰላምን ዕርቅን የሚቃወም ሃሳብ አልሰነዘሩም። እነዚህ አስተያየት ሰጭዎችና እኔም ጭምር የምንለው ዕርቅና ሰላም መካሄድ ያለበት እንደ ፖለቲካ ድርድር “በመቻቻል” (compromise) ሳይሆን ወይም እንደ ባልና ሚስት ጸብ “አንተም ተው፣ አንችም ተይ” በማለት ሳይሆን ህገ ቤተክርስቲያንን ተከትሎ፣ እውነትን ጨብጦ ፣ አጥፊው ጥፋቱን ተቀብሎ፣ የተጣመው ተስተካክሎ፣ የጎበጠው ቀንቶ እንዲሁም ከመንግስትና ከሌሎች ዓላማዊ ነገሮች ርቆ ነው መካሄድ ያለበት። አቶ ደሴ አያልሰው በስመ ዕርቅና ሰላም የመጣውን በሙሉ መቀበል አለብን ነው የሚሉት። እርስዎ አገር ያወቀውን ጸሃይ የሞቀውን ሃቅ አልቀበልም ብለው ካልሆነ በስተቀር አባ ጳውሎስ በህገ ወጥ ሁኔታ መፈንቅለ ፓትርያርክ አድርገው እንደተቀመጡ እያወቁና የሚሰሯቸው ነገሮች በአብዛኛው ህግ ቤተክርስቲያንን የጣሱ መሆናቸውን በተለይም ሃውልታቸው እንዲፈርስ የተላለፈውን ውሳኔ አልቀበልም ብለው በወታደር ታጅበው እንደሚሄዱ እያወቁ ከእሳቸው የውሸት “ሲኖዶስ” ጋር የሚደረግ ድርድርን የሚቃወሙ ሰዎችን አለአግባብ ያወግዛሉ።በዚህም ምክንያት ሁኔታውን አጣመውና አወላግደው አንባቢን ያሳስታሉ። ያልሆነ ስም በመስጠት አባ ገብረመድህንን የሚቃወሙ ሰዎችን ዕርቅና ሰላምን የተቃወሙ አስመስለው አንባቢን ያወናብዳሉ። የአባ ገብረመድህን ደጋፊ ከሆኑ ያጠለቁትን ጭብል አውልቀው ለምን ድፍረትን ሸምተው በይፋ አይጎናበሱላቸውም? ወያኔንና አባ ገብረመድኅንን የምንቃወም ሰዎች ሰላምና ዕርቅ የማንወድ አድርገው አያቅርቡን። ሃሳባችን ካልተዋጠልዎት በምንም መንገድ ልንረዳዎ አንችልም በዲሞክራሲ አገር ስለምንኖር ሊያፍኑናና ሊያሳፍኑን አይችሉም። ማስተዋልን ይስጥዎት እያልኩ እሰናበትዎታለሁ።
በመጀመሪያ እነዚህ በጣም አሳፋሪ የሆኑ ቄሶች ለምንና ለማን እንደሚደራደሩ አላውቅም:: በሳኡድ አረቢያ ውስጥ ስለታሰሩት ክርስቲያኖች ምንም ስሜት ሳይሰጣቸው ተመልክቼአለሁ:: አሜሪካ የሚገኙ ክርስቲያኖች በነገሩ ተጨንቀው ወደ ሰልፉ ሲመጡ የኛዎቹ ቄስ ተብዬዎች ግን አልሰማንም ብለው ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ:: የራሳቸው ዜጋ የሆኑ ክርስቲያኖች ታስረው ምንም ስሜት አልሰጣቸውም:: ምንም አይነት ሆዳሞች እንደሆኑ አይታወቅም:: በጣም ያሳዝናል:: የሚደራደሩት ለራሳቸው ጥቅም ነው:: ለሥልጣን ለሹመትና ለገንዘብ ነው::
ክሕገ ወጥ ወንጀለኞች ጋር ድርድር አይገባኝም:: በተለይ ከሃያ አመታት በኋላ ሽር ጉዱ ለምን እንደሆነ መረዳት አያዳግትም:: ለመሆኑ አባ ገብረ መድህን ሥልጣኑን ለቆ ይወርዳል ብለው ነው ወይስ ምን እያሰቡ ነው? ቅዠት ውስጥ ነው ያሉት ወይስ ደደብነት ነው ወይስ ሆነ ብለው ኢትዮጵያ ለመመለስ ሰበብ ለማግኘት ነው?
እስኪ አስረዱኝ::
እሪ በይ አገሬ
Do you have evidence of their agreement?????????
Please Elias, show me!!!
ልብ አድክም ነፈዞች በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል:
“ዲፕሎማሲ” የሚባለው ነገር በእግዚአብሔር ቤት አይሰራም!”
የከበረ ሠላምታዬ ይድረስዎትና ሙያዬም አይደለም እንጂ እንደ ተከታይነቴ ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል በሥጋ ዲያቆን ይሁኑ እንጂ በእኔ ልቡና በእምነትዎ ፅናት ብቻ በልቤ-ፅላት ውስጥ ከጵጵስናም በላይ ባለ ሹመት መዝግቤዎታለሁ::እናም ይህን ተራ ሥነ-ግጥም ባቅሜ ለእርስዎና በክርስቶስ ፍቅር ለሚሰብኩ ኢትዮጵያን ወዳጅ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ ለሕሊና ክብርዎ ስል ልፅፈው ወደድኩ::
$$££££ ሥጋን ከታረቁ::$$$£££
ከአባቶች በዕምነት ባገር የታወቁ:-
ሕዝብን ተደብቀው እምነቱን ከናቁ:-
እኛ ምዕመናኑ በሰውነታችን
ምን እንበል ኩነኔን ምንድነው ፅድቃችን???
እነሱስ ቢሆኑ ለነብስ ምኑን በቁ?
የሰማዩን ትተው ሥጋን ከታረቁ???
ታርቀው ሰይጣኖችን ደም ከተበከሉ:
የባረኩት ፀበል ርኩስ ነው በሙሉ::
እኒያ የተከበሩ ሰይጣን ሆነው ስናይ:-
ለሥጋ ያደሩ በግልፅ ባደባባይ
ለሃሳዊ ሥራቸው ምንስ እንላለን?
እኛ እያወቅናቸው ማን ሌላ እናምናለን???
የሞተም ተጎዳ እያሉ እየሳቁ:-
የሰማዩን ትተው ሥጋን ከታረቁ::
እንደው ጉድ’ኮ ነው:-
ምኑንስ አመንነው???
ማድረግ እንደጥንቱ ሰውን ማመን ቀብሮ:-
ነው-ወይ ብልሃቱ ይሻላል ዘንድሮ???
ግና!ለነብስ ያደሩ ሥጋ ሲጎትቱ:-
ምንድነው ሚሥጥሩ?ምንድነው መተቱ???
ምን እንበል ይህን ጉድ:-
አንደዬን ላምንነው???…
በእርግጥ ተረግመናል ወይስ ለበጎ ነው???
የሞተ ተጎዳ እያሉ እየሳቁ:-
የሰማዩን ትተው ሥጋን ከታረቁ::
ሲያጠፉ እያየን እንዳልሰሙ ሰምተው:-
እንዳልተፈፀመ እኛም አይተን እንተው???
ግና ዕምነት ያሳጣል አባቶች ሲከዱ:-
ላይ ላዩን ተከብረው ውስጥ-ውስጡን ሲናዱ::
እናም ለነብሳቸው ለሐቅ ምኑን በቁ:-
ለኑሮ አድልተው ሥጋን ከታረቁ::
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን በታምሩ ይጠብቃት::አሜን!!!
Can any one tell me what was discussed when the two parties met in Arizona? I find it very difficult to support or oppose without knowing the process and the outcome.
አቡነ ጳውሎስ እኮ ህዝብ የሚጠራቸው “አባ ዲያብሎስ” ወይም “ታጋይ ጳውሎስ” እያለ ነው። ታዲያ ከእሳቸው ጋር ምን አይነት ድርድር ነው የሚካሄደው????
ከአባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስ)ጋር የሚደረግ ድርድር ምንም ፋይዳ የለውም። እኝህ ሰው በመልስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበር ላይ ሳይገባቸው ከተቀመጡበት ጊዜ አንስቶ ሌሎች ከአሳቸው በፊት የነበሩ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርኮች ያልፈጸሙትን ወንጀል ፈጽመዋል። ከአባ ገብረመድህን ጋር የሚደረጉ ስምምነቶች የማይሳኩባቸው 10 ምክንያቶች።
1) ከእሳቸው በፊት የነበሩት ፓትርያርክ በሕይወት እያሉ ተደርበው ተሰይመዋል
2) ባህታዊ ፈቃደሥላሴን በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ አስገድለዋል
3) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር መሆንና ለውሳኔዎች ተገዥ በመሆን ፋንታ እሳቸው ሲኖዶሱን ከሥራቸው ተቀባይ እንዲሆን አድርገዋል
4) ቤተክርስቲያናት ላይ ምዝበራና ዝርፊያ በግል ዘመዶቻቸው ጭምር እንዲካሄድ አድርገዋል
5) ለጳጳስነት ብቃት የሌላቸውን ሰዎች ሾመዋል
6) የቤተክርስቲያናትን ሃብት ዘርፈው ለግላቸው የወርቅና ውድ መኪና መግዣ አድርገዋል
7) በመላው የዓለም ኦርቶዶክስ ቤክርስቲያናት የተወገዘ ሃውልታቸውን (ጣኦታቸውን) ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ተክለዋል
8) ፍቶግራፋቸውን እንደዓለማዊ መሪዎች ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ውጭ እንዲለጠፍ አድርገዋል
9) ብዙ ዘርዝሮ ለመጻፍ የሚሰቀጥጥ ከፓትርያርክ ቀርቶ ከተራ ካህን የማይጠበቁ ህጸጾችንና የስነምግባር መተላለፎችን ፈጽመዋል
10) የማይመለከታቸውና ከቤተክርስቲያኑቷ ጋር ግንኙነት በሌላቸው ጉዳዮች ከዘፋኟ ቢዮንሲና ሌሎችም ጋር ጊዜያቸውን በማባከን ብዙዎችን አሳዝነዋል